Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊስለመንገድ ደኅንነት የተዋቀረው ‹‹ቀና መንገድ››

ስለመንገድ ደኅንነት የተዋቀረው ‹‹ቀና መንገድ››

ቀን:

በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋ ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢነቱ እየጨመረ ይገኛል፡፡ በየቀኑ የሚሰሙ የትራፊክ አደጋዎች ለጆሮ የሚከብዱ ናቸው፡፡ በየዓመቱ በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚሞቱ፣ የአካል ጉዳት የሚደርስባቸውና የሚወድሙ ንብረቶችን በተመለከተ የሚወጡ ሪፖርቶች የችግሩን አሳሳቢነት ያሳያሉ፡፡

ስለመንገድ ደኅንነት የተዋቀረው ‹‹ቀና መንገድ›› | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ወ/ሪት ኤልሳቤጥ ወልደማርያም

ለአደጋዎቹ መበራከት እንደ ምክንያት ከተቀመጡት አንዱ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ የመንገድ ሥርዓት ነው፡፡ በአሽከርካሪዎች ዕውቀትና ልምድ ማነስ፣ በተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ጉድለትና ወጥ የሆነ የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት አለመዘርጋትም ይጠቀሳሉ፡፡

በአገርና በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመግታትና የመንገድ ደኅንነትን ለማረጋገጥ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ድጋፍ ‹‹ቀና መንገድ›› የተሰኘ በጎ አድራጎት ድርጅት ተቋቁሟል፡፡

- Advertisement -

ድርጅቱ የተመሠረተበትን ዓላማና የድርጊት መርሃ ግብር ለማስተዋወቅ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. በተዘጋጀ መድረክ፣ የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ውቤ እንደተናገሩት፣ ኅብረተሰቡ ስለመንገድ ደኅንነት ሰፊ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል፡፡

ስለመንገድ ደኅንነት የተዋቀረው ‹‹ቀና መንገድ›› | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
አቶ ተስፋዬ ውቤ

የመንገድ ደኅንነትን እያንዳንዱ እግረኛና በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ ሾፌሮች ሊተገብሩት የሚገባም ነው፡፡ ድርጅታቸውም ለዜጎች ሕይወት ማጣት በቀዳሚነት የተቀመጠውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት ፈጥሮ የአመለካከት ለውጥ ላይ የሚሠራ ይሆናል፡፡

ለመንገድ ትራፊክ አደጋ የአሽከርካሪው የብቃት ማነስ፣ የተሽከርካሪው የቴክኒክ ደኅንነት፣ የመንገድና የአየር ሁኔታ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ የሚሉት አቶ ተስፋዬ፣ በአገሪቱ በየዓመቱ ከአራት ሺሕ በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን እንደሚያጡና በቢሊዮን የሚቆጠር የአገር ሀብት እንደሚወድምም ገልጸዋል፡፡

በትራፊክ አደጋ የተጎዱ ዜጎችን በመደገፍ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ የሚገኘው የ‹‹ኪዲ ፋውንዴሽን›› መሥራችና ዳይሬክተር ወ/ሪት ኤልሳቤጥ ወልደማርያም በበኩላቸው፣ የመንገድ ትራፊክ አደጋ እንደ አገር አሳሳቢ ነው፡፡ ከትራፊክ አደጋ ሰለባዎች መካከልም አንዷ እህታቸው መሆኗን ይናገራሉ፡፡

ድርጅታቸው የትራፊክ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ አራት ዓመታት ሆኖታል፡፡ ከጥቁር አንበሳና ከአቤት ሆስፒታል ጋር በፈጠረው የሥራ ግንኙነት፣ አደጋ ለደረሰባቸው ዜጎች የሕክምና ዕርዳታ በሚያገኙበት ደረጃ ይሠራል፡፡ የዊልቸር፣ የክራንች፣ የጓንትና የመሳሰሉ ግብዓቶችን ለተጎጂዎችና ለሕክምና ተቋማት ያቀርባል፡፡

እንደ ወ/ሪት ኤልሳቤጥ፣ ለፖሊሶች፣ ለትራፊኮችና ለሾፌሮች የመጀመርያ ዕርዳታን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ በተጨማሪም አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ያላቸው ሥነ ልቦናና አኗኗራቸውን በተመለከተ ‹‹የተጎጂዎች ድምፅ›› በሚል ሕይወታቸውን የሚዳስስ ፕሮግራም በማዘጋጀት የትምህርትና ግንዛቤ የማስረፅ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አውቶሞቶቭ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሰለሞን ጥዑመልሳን በበኩሉ፣ በአዲስ አበባ ከተማም ሆነ እንደ አጠቃላይ በአገሪቱ የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የመንገድ ትራፊክ አደጋ የሚከሰተው በአሽከርካሪው፣ በእግረኛው፣ በመንገድ ዲዛይንና በመሳሰሉ ችግሮች ነው፡፡ በመሆኑም ችግሮችን በመፈተሽና አባባሽ ጉዳዮችን በመለየት የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ይገባል፡፡

ዘመኑን የዋጁ ደንቦችን፣ መመርያዎችንና አዋጆችን በማውጣት የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓቱን ማጠናከርና የግንዛቤ ሥራውን የበለጠ ማስፋት ከተቻለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡

‹‹በአዲስ አበባ ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ ምንም እንኳን ውስን መኪኖች ያሉ ቢሆንም፣ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ በቀን ቢያንስ አንድ ሰው የሚሞትበት ሁኔታ አለ›› የሚለው ጋዜጠኛ ሰለሞን አንድ ሰው ለአገርና ለቤተሰብ ብዙ ስለሆነ፣ የአንድ ሰው በትራፊክ አደጋ መታጣት ግድ ሊለንና በዚህ ዙሪያ መንግሥትና ባለድርሻ አካላት የተለየ ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል  ብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...