Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየባህል ትሩፋትን የሚያከብረው የአፍሪካ የዓለም ቅርስ ቀን

የባህል ትሩፋትን የሚያከብረው የአፍሪካ የዓለም ቅርስ ቀን

ቀን:

በጎርጎርዮሳዊው ቀመር ሜይ 5፣ በኢትዮጵያ (ሚያዝያ 27) ፀሐይ በወጣችበት ዕለት ዓለም ትኩረቱን ወደ ሰፊውና የልዩ ልዩ የባህል፣ የወግ እና የታሪክ ጓዝ ባለቤት በሆነው የአፍሪካ አህጉር አድርጎ ነበር፡፡ ምክንያቱም የአህጉሪቱ የበለጸገ የጥበብና የባህል ውርስ ትሩፋት በዓል የሆነው ዘጠነኛው የአፍሪካ የዓለም ቅርስ ቀን ይከበርበት ነበርና፡፡

ይህን ቅርስን የመጠበቅ አስፈላጊነት በየጊዜው እንዲታወስ የሚያደርገው የአፍሪካ የዓለም ቅርስ ቀን የዘንድሮው መሪ ቃል ‹‹ትምህርት ለአፍሪካ ቅርሶች ጥበቃ›› (Safeguarding Africa`s Heritage through Education) የሚል ነው፡፡ ዕለቱን የተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በዩኔስኮ በተመደበው ቀን ሚያዝያ 27 (ሜይ 5) በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ያከበሩት ሲሆን በዕለቱ ያልሆነላቸው እንደ ኢትዮጵያ ያሉት አገሮች ሰሞኑን አክብረዋል፡፡

በዩኔስኮ ከተመዘገቡ 147 ቅርሶች መካከል 11 በማስመዝገብ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አማካይነት ቀኑን ለሁለተኛ ጊዜ የዘከረችው ለሦስት ሳምንት ያህል ከቆየች በኋላ ነው፡፡

- Advertisement -

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የጢያ አርኪዮሎጂካል መካነ ቅርስን በመጎብኘትና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን፣ በቡታጅራ ከተማ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ የቅርስ ቀኑን አስቦታል፡፡

የአፍሪካ አህጉር በኪነ ጥበብና በባህል ቅርስ ሀብታም ነው።  ከአክሱም እስከ ላሊበላ፣ ከጎንደር እስከ ሐረር፣ ከግብፅ ፒራሚዶች እስከ ጥንታዊቷ የቲምቡክቱ ከተማ የአፍሪካ ተምሳሌት የሆኑ ቦታዎች የሕዝቦቿን ብልሃት፣ፈጠራና ፅናት እንደ ምስክር ሆነው ቆመዋል።  በዚህ ልዩ ቀን፣ የአፍሪካ የዓለም ቅርስ ቀን ጥቂቶቹን እንገልጻለን፡፡

ከአፍሪካ ታዋቂ የዓለም ቅርስ ቦታዎች መካከል

በዩኔስኮ አገላለጽ፣  አፍሪካ የበርካታ ታዋቂ የዓለም ቅርስ ስፍራዎች መኖሪያ ናት፡፡ እያንዳንዱም የራሱ የሆነ ታሪክ አለው።  ከነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ላሊበላ፣ የግብፅ ፒራሚዶች፣ ታላቁ የዚምባብዌ ብሔራዊ ሐውልት፣ የማሊ ቲምቡክቱ የአፍሪካን ታሪክና ባህል ልዕልና የሚያጎሉ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው።

በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የምትገኘው ላሊበላ ከተማ፣ ከአንድ አለት በተፈለፈሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ትታወቃለች። በ12ኛውና በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከምድር ላይ የተፈለፈሉት እነዚህ አስደናቂ ሕንፃዎች እስከ ዛሬ ድረስ የሥርዓተ አምልኮ ስፍራዎች ሆነው እያገለገሉ ናቸው። የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያ ሕዝብ የጥበብና የምህንድስና ክህሎት ምስክር ከመሆናቸውም በላይ ለአፍሪካ የክርስቲያን ቅርስ ምልክቶች ሆነው ያገለግላሉ፡፡

የግብፅ ፒራሚዶች የጥንታዊ የሰው ልጅ ሥልጣኔ ስኬት ማሳያ ናቸው። ከሦስቱ ፒራሚዶች ውስጥ ትልቁ የጊዛ ፒራሚድ የጥንታዊው ዓለም ብቸኛው አስደናቂ ነገር መሆኑን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡ እነዚህ ግዙፍ ሕንፃዎች የጥንት ግብፃውያን የነበራቸውን ግዙፍ ዕውቀትና ክህሎት በማስታወስና በማድነቅ ጭምር።

በዛሬዋ ማሊ ውስጥ የምትገኘው ቲምቡክቱ፣ ከአንድ ሺሕ ዓመታት በላይ የቆየ ታሪክ አላት። በአንድ ወቅት የንግድ፣ የዕውቀትና የባህል ማዕከል ነበረች።  በከተማዋ የታወቀው ቤተ መጻሕፍት ከሳይንስ እስከ ፍልስፍና ያሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚሸፍኑ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የብራና ጽሑፎችን ያቀፈ ሲሆን፣ በርካታ መስጊዶችም የእስላማዊው ዓለም ድንቅ ኪነ ሕንፃ የሚያንፀባርቁ ናቸው።

ታላቁ የዚምባብዌ ብሔራዊ ሐውልት፣ በአንድ ወቅት የዚምባብዌ መንግሥት ዋና ከተማ የነበረ፣ የሾና ሕዝቦችን የኪነ ሕንፃ ግንባታ ችሎታ የሚያሳይ ነው ተብሎለታል።  በ11ኛው እና በ15ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተገነባው ሐውልት ከሰሃራ በስተደቡብ በአፍሪካ ትልቁ የፍርስራሾች ስብስብ ሆኖ ዘልቋል። የድንጋይ ሥራውና አስደናቂው አወቃቀሩ የትውልዶችን ቀልብ በመግዛት የአፍሪካ ባህላዊ ቅርስ ምልክት ሆኖ ያገለግላል።

የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ሚሲስ ኦድሪ አዙላይ የአፍሪካ የዓለም ቅርስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ሚያዝያ 27 ቀን ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከአፍሪካ የሚመዘገቡ ቅርሶችን  ለመጨመር በተለይ በዓለም ላይ ምንም ዓይነት የተመዘገበ ቅርስ ለሌላቸው 11 አገሮች በትኩረት እንሠራለን ብለዋል፡፡

 በሚቀጥሉት ወራት በአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063 መሠረት፣ የአፍሪካ አገሮችን አቅም ለማሳደግም ጥረቱ እንደሚቀጥል፣ ዕውን ለማድረግም ተጨማሪ የአፍሪካ የቅርስ ባለሙያዎችን እንዲሠለጥኑና የቅርስ ትምህርት ማዕከላት እንዲቋቋሙ እንደሚደረግም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...