Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየገበያ ትስስር የሚያሻቸው አካል ጉዳተኛ አምራቾች

የገበያ ትስስር የሚያሻቸው አካል ጉዳተኛ አምራቾች

ቀን:

በተፈጥሮም ሆነ በድንገት በሚፈጠሩ አደጋዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ራሳቸውን ለማስተዳደር ሲቸገሩና  በሌሎች  ጥገኛ ሆነው አልያም ጎዳና ላይ ወጥተው  እጃቸውን ለልመና ሲዘረጉ ማየት የተለመደ ነው፡፡

በማኅበረሰቡ ዘንድ አካል ጉዳተኞች ሥራ መሥራት አይችሉም፣ አካል ጉዳት የደረሰባቸው በእርግማን ወይም ከቤተሰብ በመጣ ርኩስ መንፈስ ነው የሚሉ አስተሳሰቦች በአካል ጉዳተኞችና ቤተሰቦቻቸው የሚያደርሰው  አሉታዊ  ተፅዕኖ፣ ሥራ ሠርተው እንዳይኖሩ፣ መሥራት አንችልም ብለው እንዲያምኑና ከሌሎች ሰዎች እኩል አይደለንም እንዲሉ ሲያደርጋቸው ቆይቷል፡፡

የገበያ ትስስር የሚያሻቸው አካል ጉዳተኛ አምራቾች | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

- Advertisement -

በሌላ በኩል አካል ጉደተኞች መረዳት እንጂ በራሳቸው ሥራ መሥራትና ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር አይችሉም የሚሉትን አሉታዊ አስተሳሰቦች ሰብረው በመውጣት፣ ሙሉ አካል ካላቸው ጋር የተሰጣቸውን ወይም የተሠለፉበትን ሥራ እኩል ሲሠሩና አንዳንዶቹም በልጠው ሲገኙ ይስተዋላሉ፡፡

አካል ጉዳተኞች በማኅበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በማኅበራት ተደራጀተውም ሆነ በግላቸው በሚያደርጉት የነቃ ተሳትፎ ውጤታማ በመሆን ለሌሎችም አርዓያና ምሳሌ ሲሆኑም ታይቷል፡፡

አካል ጉዳተኞች በሞራል፣ በገንዘብም ሆነ በጉልበት እገዛ በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ከጎናቸው በመሆን ሊያበረታታቸው የሚችል ሥርአት ካገኙ ሙሉ አካል ያለው ሰው የሚያከናውናቸውን ሥራዎች መሥራት እንደሚችሉ  የሚያሳዩ  ተሞክሮዎችም አሉ።

‹‹ብራይት ወርልድ ፎር ብላይንድ ውሜን አሶሴሽን›› በሚል ተደራጅተውና  በተለያዩ ተግባራት ተሰማርተው ራሳቸውን ከልመና ቤተሰባቸውንም ከረሃብና  ከችግር የታደጉ ዓይነ ሥውራን ሴቶች ለዚህ ማሳያ ናቸው።

አባላቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሥልጠና የወሰዱ ሲሆን፣ በሠለጠኑበት ሙያ ተሰማርተው ራሳቸውን ከልመና እንዳወጡና ኑሮአቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ።

ዓይነ ሥውራኑ ከሚሠለጥኑባቸው ሙያዎች የእደ ጥበብና የብሬል ላይ ጽሑፍ  ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ ከክር የሚሠራ ሹራብ፣ ኮፍያ፣ ቦርሳና የመሳሰሉትን  የእጅ ሥራ ውጤቶች በመሥራት ለገበያ እያቀረቡ መሆኑን የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘነበች በላቸው ይናገራሉ፡፡

 አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ሰው ሠርተው መለወጥና ራሳቸውን መምራት ይችላሉ የሚሉት ወ/ሮ ዘነበች፣ የሚሠሯቸውን የዕደ ጥበብ ውጤቶች መሸጫና መሥሪያ ቦታ እንዲሁም የገበያ ትስስር ዋነኛ ችግራቸው እንደሆነ ይገልጻሉ።

የገበያ ትስስር፣ የሥልጠና መውሰጃ ቦታ፣ የጥሬ ዕቃዎች መሸጫ፣ ገንዘብና የመሳሰሉ ችግሮች ቢቀረፉ አሁን ካሉት ሴቶች በላይ ቁጥራቸውን በመጨመር ብዙ ሴቶች ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ወ/ሮ ዘነበች ያነሳሉ፡፡

ምንም እንኳን አባላቱ እርስ በርሳቸው በመማማርና ሥልጠና በመውሰድ ራሳቸውን ማሻሻል ቢችሉም፣ የመሥሪያ ቦታ ባለመኖሩ ወደ ሥራ የገቡ ሴቶች ቁጥራቸው አናሳ ነው፡፡

ሥልጠናዎችን ወስደው ሙያውን ከያዙ በኋላ በተለያዩ ችግሮች ሙያቸውን ተጠቅመው ገቢ ማመንጨት ያልቻሉ ሴቶች ስለመኖራቸው የተናገሩት ሥራ አስኪያጇ፣ የሚሠሩበትን ጥሬ ዕቃ (ክር) ማጣት፣ ሲሸጡ የሚያገኙት ገቢ በቂ አለመሆን፣ የገበያ ትስስር ማጣት ሥራውን በአግባቡ እንዳይሠሩ የሚያደርጉ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም ሙያውን ከያዙ በኋላ ሠርተው ለገበያ ከማቅረብ ይልቅ ለዕለት ጉርስ የሚሆን ምግብን ፍለጋ ወደ ጎዳና እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

እነዚህንና መሰል ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የተናገረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣  ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለተሰማሩ አካል ጉዳተኞች ምርታቸውን እንዲሸጡና እንዲያስተዋውቁ የሚረዱ ባዛሮችን በማዘጋጀት እንዲሳተፉ እገዛ ማድረጉን   አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ አካል ጉዳተኞች መሥራት የይችላሉ በሚል ከግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለአካል ጉዳተኞች ብቻ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ባዛር አራት ኪሎ አካባቢ አዘጋጅቶ ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ እያደረገ ይገኛል፡፡

በባዛሩ 50 የአካል ጉዳተኞች መሳተፋቸውን የተናገሩት በቢሮው የአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ አየሁ ደመቀ ናቸው፡፡

ከእነዚህ ውስጥ አሥራ አራቱ በማኅበሩ የተደራጁ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በግላቸው ንግድ ፈቃድ አውጥተው በመሥራት ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ተሳታፊዎቹ ወደ ባዛሩ ይዘዋቸው ከመጡ ዕቃዎች ውስጥ የዕደ ጥበብ ውጤቶች፣ ከቆዳ የተሠሩ ቁሳቁሶች፣ የተለያዩ የባልትና ውጤቶችና የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ይገኙበታል፡፡

በባዛሩ የሚሸጡ ዕቃዎች አካል ጉዳተኞቹ በማኅበርም ሆነ በግላቸው የሚያመርቱትን  እንጂ ከሌላ ገዝተው ማምጣት አይችሉም ያሉት ወ/ሮ አየሁ፣ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና አካል ጉዳተኛ ስለመሆናቸው ከሚኖሩበት ቀበሌ ያስመሰከሩ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ባዛሩ የተዘጋጀበትን ቦታ ከመፍቀድ ጀምሮ የድንኳን፣ የጥበቃ፣ የፅዳትና ሌሎች ጉዳዮችን በመፈጸም እንዳገዛቸው ተናግረዋል፡፡

አካል ጉዳተኞችን በተግባር ለማገዝና ለማጠናከር መሰል ባዛሮችና የበያ ትስስሮች እንዲፈጠሩላቸው ወ/ሮ ዘነበች ጠይቀዋል፡፡

በባዛሩም በዕደ ጥበብ ሥራዎች  የተሰማሩ  ዓይነ ሥውራን ሴቶች የሠሯቸውን ምርቶች ይዘው ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ ዓይነ ሥውራን ሴቶች በብዙ ውጣ ውረድ አልፈው  ያቀረቡትን ልብስ ከሸጡ በኋላ ገንዘቡን ክሩን ገዝቶ ከሰጣቸው ሰው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ የቆዳ ውጤቶችን በማምረት በባዛሩ ከተገኙት አንዱ መሱድ መስከረምና ጓደኞቻቸው ማኅበር ነው፡፡ የማኅበሩ ተወካይ አቶ አክሊሉ ዋሩዳ ተመሳሳይ ችግሮችን አንስተዋል፡፡ የገበያ ትስስር ማጣት፣ የገንዘብ እጥረትና ተያያዥ ችግሮች እንዳሉባቸው ተናግረዋል፡፡

በተለይ የገበያ ትስስር ካልተፈጠረና ያመረቱትን ዕቃ በወቅቱ ካልሸጡ ገንዘብ ይዞ ለረዥም ጊዜ ስለሚቀመጥ የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንደሚያስከትልባቸው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...