Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየትዕግስት አሰፋ የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን ፀደቀ

የትዕግስት አሰፋ የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን ፀደቀ

ቀን:

ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ፣ ባለፈው መስከረም በበርሊን የተካሄደውን የሴቶች ማራቶን ውድድርን ያሸነፈችበት 2፡11፡53 ሰዓት፣ የዓለም ማራቶን ክብረ ወሰን ሆኖ በዓለም አትሌቲክስ ፀድቋል።

መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የተከናወነውን የቢኤምደብሊው የበርሊን ማራቶን፣ ትዕግስት ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ክብረ ወሰኑን ከሁለት ደቂቃ በላይ በመስበር የመጀመርያዋ ሴት እንድትሆን እንዳደረጋት፣ የዓለም አትሌቲክስ ግንቦት 15 ቀን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ነባሩ ክብረ ወሰን ኬንያዊቷ ብሪጊድ ኮስጌይ ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሄደው የቺካጎ ማራቶን በ2፡14፡04 በመፈጸም ያስመዘገበችው ነበር፡፡ 

- Advertisement -

ትዕግስት ከዘጠኝ ወራት በፊት ክብረ ወሰኑን የሰበረችበትን የውድድር ሒደትንም የዓለም አትሌቲክስ በአድናቆት እንዲህ አስታውሶታል፡፡

‹‹ትዕግስት በሚገርም ሁኔታ ዘና ብላ ከ25-35 ኪሎ ሜትር ያለውን ርቀት በ31፡02 ደቂቃ ሸፍናዋለች። የዓለም ክብረ ወሰን ውስጥ መግባቷን በማወቋም የመጨረሻዎቹን ኪሎ ሜትሮች በፍጥነት በመሮጥ 2፡11፡53 በሆነ ሰዓት የፍጻሜውን መስመር ማለፍ ችላለች።

‹‹የእኔ ብቃት በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ወጣት ሴት አትሌቶች አበረታች እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አንድ ዓመት ሲቀረው የዓለም ክብረ ወሰንን መስበሬ ለፓሪስ ኦሊምፒክ ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል፤›› ስትል በድሏ ዕለት መናገሯ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...