Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኢዜማ ያቀረበውን ቅሬታ ለመቀበል እንደሚቸገር አስታወቀ

አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኢዜማ ያቀረበውን ቅሬታ ለመቀበል እንደሚቸገር አስታወቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በቅርቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ያቀረበውን ጥያቄ ለመቀበል እንደሚቸገር አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ፓርቲው በወረዳ ደረጃ የተካሄዱ ምክክሮች ከገዢው ፓርቲ አደረጃጀቶች በመጡ ተሳታፊዎች የተሞሉ ናቸው ብሎ ያቀረበውን ቅሬታ እንደማይቀበለው ነው የገለጸው፡፡

አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሚያካሂዳቸው የምክክር መድረኮች የሁሉንም ወገን ውክልና ያካተቱ መሆናቸውን በመግለጽ ተከራክሯል፡፡ አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ረቡዕ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚዲያ ስለተከወኑ የሥራ እንቅስቃሴዎች የሚገመግም መድረክ በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል አዘጋጅቶ ነበር፡፡

- Advertisement -

በዚሁ ዕለት ለተገኙት ለኮሚሽኑ ኮሚሽነር ማሕሙድ ድሪር (አምባሳደር) ሪፖርተር ኢዜማ ስላነሳው ቅሬታ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ በወረዳ የተካሄዱ ምክክሮች በአንድ ፓርቲ አደረጃጀት ተሳታፊዎች የተሞሉ ነበር የሚለውን ወቀሳ ለመቀበል ኮሚሽኑ እንደሚቸገር ገልጸዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሠራሩ ተቃዋሚዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን ወዘተ ሁሉንም ወገን የሚያሳትፍ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የአንድ ፓርቲ አደረጃጀት ተወካዮች ናቸው ብሎ ለመናገር እኔ በግሌ አያስደፍርም እላለሁ፡፡ ጥቂትና እዚህም እዚያም የአንድ ፓርቲ አደረጃጀቶች በዛ ሊሉ ይችሉ ይሆናል፡፡ ሆኖም በወረዳ የተካሄዱ ውይይቶች በአደረጃጀት የተሞሉ ናቸው ብሎ መደምደሙ ከእውነታው ያፈነገጠ ይመስላል፤›› በማለት ነበር ኮሚሽነሩ ምላሽ የሰጡት፡፡

ሪፖርተር ከዚህ በተጨማሪም እንደ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች የፓርቲ ሊቀመንበራቸውና አባሎቻቸው ከእስር ሳይፈቱ በውይይቱ ለመቀጠል እንደሚቸገሩ ስለመግለጻቸው ለኮሚሽነሩ ጥያቄ አንስቶ ነበር፡፡

‹‹የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ ስላለ በዚያው መድረክ በሚካሄድ ውይይት ይህን የመሳሰሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል፤›› በማለት ነበር ማሕሙድ (አምባሳደር) ምላሽ የሰጡት፡፡

አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በዚሁ መድረክ ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠሩ ተነስቷል፡፡ በተለይ በጥቅምት ወር በአዳማ ከተካሄደው የውይይት መድረክ ወዲህ በሚዲያ አጠቃቀምና በመረጃ ሥርጭት የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡ ተመልክቷል፡፡

በዚሁ ጊዜ ኮሚሽናቸው ሁሉንም ወገን የታጠቁ ኃይሎችን ጭምር የሚያሳትፍ ውይይት ለማድረግ ጥረት መቀጠሉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ ለታጠቁ ኃይሎች ዋስትና በመስጠት በውይይቱ እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረት መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...