Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልደረጃቸውን ያልጠበቁ የሕዝብ መዝናኛ ፓርኮች  የማደሱ ሒደት

ደረጃቸውን ያልጠበቁ የሕዝብ መዝናኛ ፓርኮች  የማደሱ ሒደት

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን የማስተዳደርና የማሳደግ ሁለንተናዊ ኃላፊነት ተሰጥቶት ሃቻምና በአዋጅ ቁጥር 74/2014 መንግሥታዊ የልማት ድርጅት  ሆኖ የተቋቋመው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ነው።

ኮርፖሬሽኑ በመዲናዋ የሚገኙ መናፈሻዎችን ወይም ፓርኮችን፣ አደባባዮችን፣ ፕላዛዎችን ወይም  የፌስቲቫል ሜዳዎችን እንዲሁም  ዙ ፓርኮችን እንዲያስተዳድር ሥልጣን ተሰጥቶታል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ትኩረት ነባር የመዝናኛ ቦታዎችን በማስተዋወቅ ከሚሰጣቸው አገልግሎት ገቢ በማመንጨት የመዝናኛ ቦታዎችን ማሻሻል፣ ማስፋፋትና ማልማት እንደሆነ በሰነዱ ተጠቁሟል።

በኮርፖሬሽኑ ከታቀፉ አሥር ፓርኮች አምስቱ ከደረጃ በታችና አደጋ ላይ በመሆናቸው የመልሶ ማልማት ሥራ ሊደረግላቸው መሆኑ ተሰምቷል።

- Advertisement -

ፓርኮቹ ዕድሜ ጠገብ በመሆናቸው  የሚገባቸውን ደረጃ ባለማሟላታቸው ዕድሳት ሊደረግላቸው መሆኑን ኮርፖሬሽኑ  ቅዳሜ  ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።

ዕድሳት ይደረግላቸዋል የተባሉት ፓርኮች – ኢትዮ ኩባ የወዳጅነት ፓርክ፣ ሐምሌ 19፣ ብሔረ ጽጌ፣ ኢትዮ ኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያና  አዲስ ዙ (ፒኮክ) ናቸው፡፡

በዘውዳዊውና በደርግ ዘመኖች እንደተመሠረቱ የተነገረላቸው ፓርኮቹ  ባሉበት ደረጃቸውን ለማሻሻል  እንቅስቃሴ  መጀመሩንና የሦስቱ ፓርኮች ዲዛይናቸው መጠናቀቁን  በኮርፖሬሽኑ የኢኮ ቱሪዝም ዘርፍ   ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ተፈራ አስታውቀዋል።

መልሶ ለማልማት ከፍተኛ በጀት እንደሚጠይቁ የተናገሩት አቶ ሙሉጌታ  በአሁኑ ወቅት  የተበጀተው ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑንም አውስተዋል።

ፓርኮቹ  በሚታደሱበት ወቅት ቀደም ሲል የነበራቸውን ታሪካዊ  ይዘታቸውንና  ስያሜያቸውን እንደማይቀየርም ጠቁመዋል።

የአረንጓዴ ልማት ሥራ  ለአዲስ አበባ የህልውና ጉዳይ እንደሆነ የተናገሩት  የኮርፖሬሽኑ የምህንድስና ዘርፍ ምክትል ኃላፊ  አቶ ውብሸት በላይ፣ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ፓርኮች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በኮርፖሬሽኑ ከታቀፉት አሥር ፓርኮች መካከል እንጦጦ፣ አፍሪካ፣ አምባሳደር፣ ከንቲባ ወልደ ፃድቅ ፓርኮችና ልደታ መዋኛ ገንዳ ደረጃቸውን ያሟሉና እስከ ቀጣይ 15 ዓመታት  አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

አንድ ፓርክ ደረጃውን አሟልቷል ለማለት ውኃ፣ አረንጓዴ አካባቢና  የተለያዩ ግንባታዎችን መያዝ አለበት ያሉት አቶ ውብሸት፣  እነዚህንና ሌሎች መሟላት ያለባቸውን መሥፈርቶች እንዲይዙ ለማድረግም እየተሠራ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

አገራዊ ፓርኮችን ከምሥራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ለማድረግ  እየተሠራ ነው ያሉት ኃላፊው፣  እንደገና ለማልማት ከታቀዱት ፓርኮች ውስጥ ብሔረ ፅጌ፣ አዲስ ዙ (ፒኮክ መናፈሻ)፣ ኢትዮ ኩባና ኢትዮ ኮሪያ ፓርኮች እንዲሁም ሐምሌ 19 መናፈሻ  ዲዛይናቸው  ተጠናቋል ብለዋል፡፡

 ዘንድሮ ኢትዮ ኮሪያ ፓርክን በራስ አቅም በማደስ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁን፣ የሌሎችን ደግሞ  ከመንግሥትና ከግል አልሚዎች ጋር ለመሥራት መታቀዱን አብራርተዋል።

ከዚህ በፊት ፓርኮች ላይ ብዙ ትኩረት አይሰጥም ነበር ያሉት አቶ ውብሸት፣ የተሟላ ጥበቃ ከማድረግ ጀምሮ ኅብረተሰቡን ሊጎዱ የሚችሉ ማንኛውም  የአልኮል መጠጥን ጨምሮ ወጣቱን ለሱስ የሚጋብዙ ነገሮች እንዳይገቡ መከልከሉን ጠቁመዋል።

ፓርኮች ዘላቂና የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ፣  ለጥገናም ሆነ ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግም የመግቢያ ክፍያ  ማስከፈል ጠቀሜታውን ሳይገልጹ አላለፉም።

ኮርፖሬሽኑ ከመቋቋሙ በፊት በከተማዋ ያሉ ፓርኮች  የተበታተነ አስተዳደር  እንደነበራቸው ያስታወሱት አቶ ሙሉጌታ ተፈራ፣ በፓርኮች አጥር ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች በቀጣይ ተገቢው ቦታ ተመቻችቶላቸው  እንዲነሱና ፓርኮችም ይዞታቸውን እንዲያስከብሩ ይደረጋል ብለዋል።

በቀጣይም በኮሪደር ልማት ሥራ በርካታ ፓርኮችና መዝናኛ ቦታዎች እንደሚሠሩና  በቀጣይ የኅብረተሰቡን  የመዝናናትና በንጹህ ቦታ የመኖር ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሠራም ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...