Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ወገንህን ጠብቅ

ትኩስ ፅሁፎች

ወገንህን ጠብቅ የተባለበት ይህ በፍጥረት ሁሉ ዘንድ ያለ ነው እንጂ አንዳንድ ሰዎች እንደሚተረጉሙት አጭር ትርጓሜ አይደለም፡፡ ይህም ባጭሩ ሲገለጽ ለባዊት ነፍስ በሌላቸው ዘንድ እንኳ አንበሳ ጋብቻውም ኑሮውም ከአንበሳ ነው እንጂ ከቶ ከሌላ በፈቃዱ ተጋብቶ ተዋልዶ ተራብቶ አይገኝም፡፡ ያንኑ ወገኑን ፈልጎና ጠብቆ ይኖራል እንግዲህ ማናቸውም እንስሳት ሁሉ እንዲሁ ናቸው፡፡ ሰውም በኅብረ መልክእ የተለየ ስለሆነና ሁሉም የመልኩን ኅብር አይቶና ጠብቆ የሚኖር ስለሆነ ኢትዮጵያዊም የሆነ ሁሉ የጎሳ መለዮ ሳይሻ እርስ በርሱ መደጋገፍና መጠባበቅ አለበት፡፡

የኢትዮጵያም ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ ወሮታ አዋቂ አደራ ጠባቂ፤ ብድር ከፋይ ስለሆነ፤ ክፉ ላደረገበት፤ ክፋቱን በጎ ለሰራለትም በጎነቱን በደሙ ጭምር ለመመለስ የተዘጋጀ ነው፡፡

ከዚህም ሌላ ወገንህን ጠብቅ የተባለው በዱር በገደል ከጠላት የሚጋደሉት አርበኞች በከተማም ውስጥ የነበሩ በእምነት በሦስቱ ቃላት የተሳሰሩ ወንድማማቾች በየመንገዱ የተጠመዱትን ምስጢራዊ የሞት ወጥመዶች ሳይፈሩ የፋሽስትን ስብከት እየተቃወሙ ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ከአውሮፓ ወደ አርበኞች እንደ ርግበ ኖኅ የንጉሠ ነገሥታትን ሕይወት የኢትዮጵያን ደኅንነት እያመላለሱ ለወገናቸው ያተርፉ ነበርና በዚህ ምክንያት ወገንህን ጠብቅ ተባለ፡፡ ወደፊትም ይህ ማኅበር የሁሉም ማሰሪያ በሆኑት በሦስቱ ቃላት እየተመራ ሥራውን ያከናውናል፡፡ ይህም ማኅበር ሲመሰረት የቆመው የመጀመርያው የጦርነት ጊዜ ደንብና የመተማመኛውም ቃ የሚከተለው ነው፡፡

– ‹‹የአርበኞች ትግል ከፋሺስት ጋር›› (1936)

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች