Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሕገ መንግሥቱን የተመለከቱ አጀንዳዎችን ለአገራዊ የምክከር ኮሚሽን አቀረቡ

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሕገ መንግሥቱን የተመለከቱ አጀንዳዎችን ለአገራዊ የምክከር ኮሚሽን አቀረቡ

ቀን:

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሕገ መንግሥቱ የሰንደቅ ዓላማ፣ የወሰንና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠልን የሚመለከቱ አንቀጾች፣ ለአለመግባባት መንስዔዎች መሆናቸውን ገልጸው፣ የሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊነት ጉዳይ በአገራዊ ምክክር ሒደቱ አጀንዳ እንዲሆኑ አቀረቡ፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ከ367 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሰበሰባቸውን አጀንዳዎች፣ ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በይፋ አስረክቧል። 

‹‹መሠረታዊ የችግሮች መንስዔ፣ አሁናዊ መንስዔና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለ ግንኙነት›› በሚሉ ሦስት ጉዳዮች ላይ አጀንዳዎች መሰብሰባቸው ተገልጿል። በአገሪቱ ላለው የአለመግባባት ችግር መንስዔ የተባሉ ጉዳዮችን በሁለት ከፍለው ያስቀመጡት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሕግ የበላይነት አለመከበር፣ የፌዴራል ሥርዓቱ አወቃቀር፣ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የምርጫ ሥርዓቱ፣ የማንነት ጥያቄ፣ የወሰን ግጭት፣ የሰንደቅ ዓላማ፣ እንዲሁም ቋንቋ መሆናቸውን አስታውቀዋል። 

- Advertisement -

የአገራዊ ፕሮጀክቶች አካባቢንና ማኅበረሰብን ታሳቢ አለማድረጋቸው፣ የዜጎች መፈናቀልና ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አለመቻል፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ አካታች አለመሆን፣ የወንጀል መበራከትና የፍትሕ ዕጦት፣ እንዲሁም የሃይማኖት ግጭት ለአሁናዊ ችግሮች በምክንያትነት አስቀምጠዋቸዋል። በመንግሥትና በሕዝብ መካከል የተበላሹ ግንኙነቶች መኖራቸው አለመግባባቶችን እንዳባባሷቸው ያስታወቁት ድርጅቶቹ የሀብትና የሥልጣን ክፍፍል፣ የመሬት ሥሪትና አጠቃቀም፣ ዘለቄታዊ የተቋማት ግንባታ፣ የፖለቲካና የእምነት መስተጋብር፣ እንዲሁም የተጋላጭ ማኅበረሰብ ክፍሎች ጉዳይ በአጀንዳነት እንዲያዙ በአጀንዳቸው አካተው አቅርበዋል። 

‹‹ከ4,000 በላይ ድርጅቶች ተመዝግበው በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የ367 ድርጅቶች አጀንዳ በምክር ቤቱ ሲቀርብ ከሌሎች ድርጅቶች የወሰድነው ውክልና ሊዘነጋ አይገባም፤›› ያሉት የምክር ቤቱ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀና ወልደ ገብርኤል፣ አሁንም አጀንዳቸውን እየሰበሰቡ ያሉና ለመሰብሰብ ዕቅድ የያዙ ድርጅቶች መኖራቸውንም ጠቁመዋል። ግጭቶች ባሉባቸው የአማራና የኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአጀንዳ ማሰባሰቡ ሒደት መሳተፋቸውን የገለጹት ወ/ሮ ሀና፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ወደፊት በሚያከናውናቸው ተግባራትም እንደሚሳተፉ ገልጸዋል። 

 የሴቶች ሲቪል ማኅበረሰበ ድርጅቶች ጥምረት፣ የወጣቶች ሲቪል ማኅበረሰበ ድርጅቶች ጥምረት፣ የድሬዳዋ ሲቪል ሶሳይቲ ኔትወርክ የተሰኙ ሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ኮሚሽኑ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በጋራ ሲሠሩባቸው የቆዩ ጉዳዮችን ለውይይት አቅርበዋል። በዋናነትም ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች በሒደቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል፣ ስለሒደቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ማከናወንና ምክረ ሐሳቦችን ማቅረብ ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ በመነሳትም ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረንስ ፎር ዴሞክራሲን በመወከል የተገኙት አቶ ታደለ ደርሰህ ‹‹አሁን ከአዲስ አበባ ተነስተን ጋንቤላ፣ ወለጋ፣ አማራ፣ አፋር ወይም ትግራይ መሄድ አንችልም። ከፍተኛ ችግር ነው ያለው፡፡ ሰዎች መንገድ ላይ ይታገታሉ፤›› በማለት ገልጸው፣ ‹‹አገሪቱ ካለችበት ከዚህ ወቅታዊ ችግር ጋር አጀንዳችሁን እንዴት ታያይዙታላችሁ፤›› በማለት ጥያቄ አቅርበዋል።

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የድሬዳዋ ሲቪል ሶሳይቲ ኔትወርክን ወክለው ገለጻ ያደረጉት ነፃነት ተከስተ (ዶ/ር)፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም የዚህ ችግር ተጠቂ መሆናቸውን በመግለጽ በምክር ቤቱ ለአገራዊ ምክክሩ እንዲቀርቡ ከተደረጉት አጀንዳዎች መካከል እነዚህ ጉዳዮች በስፋት መኖራቸውን አስረድተዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...