Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ድርሰት የሌለው ሕዝብ ሕዝብ አይደለም››

ትኩስ ፅሁፎች

  (ቮልቴር)

የሀገርና የሕዝብ ጉዳይ ዕረፍት ከሚነሳቸው ዋነኞች አንዱ ከበደ ሚካኤል ናቸው። የኢትዮጵያ ኋላ ቀርነትና ድንቁርና በአያሌው አሳስቧቸዋል፡፡ ስለ ሥልጣኔ ከጻፉት አራት መጻሕፍት አንዱ ይኸ ነው። —-

‹‹ደራሲ የሌለው ሕዝብና ቃፊር የሌለው ወታደር አንድ ነው›› ሁለቱም መሸነፋቸው አይቀርም ይላሉ አስረስ የኔሰው፡፡ የአንድ ሕዝብ ዕድገትና ሥልጣኔ የሚታወቀው ኪነ ጥበቡም ሲያድግ ነው፡፡ ‹‹Art is the signature of civilizations.››  እንዲል Beverly Sills፡፡ የጥሩ ድርሰት ማደግ የሕዝብን ማደግን ያመለክታል፡፡  ከበደ ሚካኤል ግሪክ ሚጢጢዬ ሀገር ሆና ሳለ ኃያላን አገሮችን ሳይቀር በትንሽ ጦር ያንበረከከችው ሥልጣኔ ስላላት ነው ይላሉ። ሥልጣኔ ያለው ሕዝብ ከነፃነቱ ባሻገር በአሸናፊነት ይኖራል። ኋላቀርነት የባርነትና የድህነት ምንጭ ነው፡፡

ከበደ ሚካኤልም የግሪክ ሥነ ጽሑፍ ትሩፋትን በሆሜር በኩል እንዲህ ይገልጡታል። ‹‹ዓለም በድንቁርና ተንኮል ሲኖር ብቻዋን በሥልጣኔ ፀድቃ ትኖር የነበረችው ግሪክ ውበቷን የሚመሰክሩ ሕንጻዎቿ ዛሬ ፈርሰዋል፣ አርበኞቿም ረግፈዋል የሆሜር ቅኔ ግን እስካሁን ድረስ ቆይቶ ግሪክ ምን እንደነበረች ይገልጣል ያስተምራል  ይናገራል፤››

 ገጽ 24 ‹‹በማንኛውም ሕዝብና በማናቸውም አገር በማናቸውም ዘመን ከተነሱት ባለቅኔዎች ሁሉ ሆሜር ይበልጣል ከዚህም የተነሳ የባለቅኔዎች መሥፍን ተብሎ ይጠራል፤›› …ረናን የሚባለው የፈረንሳይ ሊቅ ከአንድ ሺሕ ዓመት ወደፊት ዕውቀት እየሰፋ ሲሄድ… አሁን በዓለም ላይ ያሉ መጻሕፍት ሁሉ ተንቀው የሚያነባቸው ይጠፋል፡፡ ሁለት መጻሕፍት ብቻ ምንጊዜም ቢሆን ስለማይረክሱ መታተማቸውና መነበባቸው ይቀጥላል እነዚሁም መጽሐፍ ቅዱስና የሆሜር ቅኔ ናቸው›› ገጽ 27። የሆሜር ድርሰት ለ3,000 ዘመን አዲስ ሆኖ ሊቀጥል የቻለው ምን አይነት ድርሰት ቢሆን ነው? ለምን ወደ እኛ ቋንቋ ተተርጉሞ አላነበብነውም?  ግሪኮች የፈነጠቁት የዕውቀት የብርሃን ጮራ ዛሬም በብዙ የምድራችን ሥፍራዎች ያበራሉ። ትልቁ ጥያቄ ለምን በእኛ ሀገር አላበሩም? የሚለው ነው፡፡…

‹‹ሰው ባሳቡ ካልተመራመረ በቀር ሕይዎት አለኝ ለማለት አይገባውም›› ይላሉ።  ይቀጥሉና ‹‹ሕዝብ በእንቁላል ሊመሰል ይችላል። እንቁላል ካላስታቀፉት በስተቀር አይፈለፈልም፣ ሕይዎትም አያገኝም። ሕዝብም እንደዚሁ በዕውቀት ካልቀሰቀሱት በቀር ዓይን አይከፍትም እንደ እንቁላል ተደፍኖ ይኖራል እንጅ ይህም ተደፍኖ የሚኖርበት ሁኔታ የአዕምሮ ሰመመን፣ የመንፈስ እንቅልፍ ድንቁርና ይባላል፤›› ይላሉ። ሕዝብ በድርሰትና በኪነ ጥበብ ካልተቀሰቀሰ በጽኑ የእንቅልፍ ድንዛዜ ውስጥ እንደሚኖር የዕውኑን ዓለም ምስክርነት ከግሪክ እየጠቀሱ ይነግሩናል። ማሰብ አንችልም ደንቆሮ ነን ስለዚህ ሕይዎትን እየኖርናት አይደለም የሚሉ ይመስላል። በዚህ ጉዳይስ ላይ መቼ ተነጋገርን?…

 ከበደ ሚካኤል በዚህ መጽሐፍ ላይ ስለ ባርነትና ነፃነት፣ ስለ ኪነ ጥበብና ሥልጣኔ፣ ስለ ኪነ ጥበብ ሰዎችና ሳይንቲስቶች ለጥበብና ሳይንስ ሁሉን ትተው እንዴት እንደ መነኑ በሚያስደንቅ ሁኔታ ይተርኩልናል። ክቡር ከበደ ሚካኤል ሆይ ስለ ብርቱ ጥረቶትና ቁጭቶት  ምሥጋና ይገባዎታል!

  • በፀጋው ማሞ
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች