Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልወግ እና ባህል በዮድ አቢሲኒያ

ወግ እና ባህል በዮድ አቢሲኒያ

ቀን:

የአገርን ወግና ባህል ለሌሎች ለማስተዋወቅና ሳይከለሱ ሳይበረዙ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ማኅበረሰብ ኃላፊነት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ትልልቅ ሆቴሎችና የእንግዳ ማረፊያዎች፣ የባህል ምግብ ቤቶችና ተቋማት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡

የባህል ምግብ አዳራሾች ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች በማዘጋጀት ለአገር ውስጥና ለውጭ እንግዶች፣ ባህል ባህል የሚሸቱ አለባበሶች በማጎልበት ለሌሎች አርዓያና ምሳሌ ሲሆኑ ይታያል፡፡

በርካታ የአገሮች መሪዎች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና ቱሪስቶች በብዛት ከሚያርፉባቸው የባህል ምግብ ቤት አዳራሾች አንዱ ዮድ አቢሲኒያ ነው፡፡

- Advertisement -

ዮድ አቢሲኒያ ላለፉት ሃያ ዓመታት የኢትዮጵያን ባህል ከቤት አሠራር እስከ ምግብ አዘገጃጀት፣ ከአለባበስ እስከ ጭፈራና ሌሎች ባህላዊና አገራዊ ሁነቶችን በማዘጋጀት  ለውጭ ዲፕሎማቶችና ቱሪስቶች ሲያስተዋውቅ ቆይቷል፡፡

በሁለት አሠርታት ጉዞው በዘርፉ በርካታ ውጣ ውረዶችና ፈተናዎችን ተጋፍጠው አሁን ላሉበት ደረጃ መድረሳቸውን የተናገሩት የዮድ አቢሲኒያ ባህል አዳራሽ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ትዕዛዙ ኮሬ ናቸው፡፡

ለማንኛውም ድርጅት ስኬትም ሆነ ውድቀት የሠራተኞች መስተጋብር ቀላል አይደለም የሚሉት አቶ ትዕዛዙ፣ ከሠራተኞቻቸው ጋር ያላቸው ጥሩ ግንኙነትና ቅርርብ ለስኬታቸው አንዱ በር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በጉዞአቸው አብረዋቸው የተጓዙትን ሠራተኞች በማሰባሰብ ሃያኛ የምሥረታ በዓላቸውን ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በጋራ አክብረዋል፡፡

በዮድ አቢሲኒያ 350 የሚደርሱ ሠራተኞች እንዳሏቸው የተናገሩት አቶ ትዕዛዙ፣ ‹‹ሠራተኞች ሳይሆኑ አባሎቻችን ነው የምንላቸው›› ሲሉ ለሠራተኞቻቸው ያላቸውን አክብሮት ያስረዳሉ፡፡

ሁሉም አባሎች ከፀጉር አሠራር ጀምሮ አለባበስና መልካም ሥነ ምግባርን የተላበሱ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ትዕዛዙ፣ አባሎቻችን በቅድሚያ ይህንን ካላሟሉና የአገራችንን ባህል ካላንፀባረቁ ባህላችንን እንጠብቃለን እናስተዋውቃለን ማለቱ ውሸት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሥረኛ የምሥረታ ዓመታቸውን ሲያከብሩ ለሠራተኞቻቸው ሽልማት አልባሳትና ሌሎች ሽልማቶችን በማበርከት እንዳከበሩ የሚያስታወሱት አቶ ትዕዛዙ፣ ወደ ውጭ ሄደው እንዲዝናኑ ጭምር ዕድል የሰጧቸው እንደነበሩ ያስታውሳሉ፡፡ ዘንድሮ ግን ማለትም ሃያኛ የምሥረታ በዓላቸውን ቀለል ባለ ሁኔታ ዝም ብሎ ከማለፍ በሚል ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዓላቸውን በድምቀት ድል ባለ ድግስ ለምን ማክበር እንዳልቻሉ አቶ ትዕዛዙ ሲናገሩ፣ ብዙ ወገኖች በጦርነት፣ በረሃብና በልዩ ልዩ ችግሮች ውስጥ መሆናቸው በእጅጉ እንደሚያሳስባቸውና የተለየ ደስታን ለመፍጠር ስለሚያስችላቸው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ይሁን እንጂ በቀጣይ አሁን ላይ ያለው ሰላምና ደኅንነት ተረጋግጦ ሕዝባችን ካለበት ረሃብና ችግር ተላቆ የአገራችን ትንሳዔ ሲመጣ በቀጣይ 25ኛ ዓመታችንን ከዚህ በተሻለና ከአባሎቻችን ባሻገር ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ በደማቅ ሁኔታ እንደሚያከብሩ ከወዲሁ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ