Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየፓሪስ ኦሊምፒክ የማራቶን ተወዳዳሪዎችን ፌዴሬሽኑ በዚህ ሳምንት አሳውቃለሁ አለ

የፓሪስ ኦሊምፒክ የማራቶን ተወዳዳሪዎችን ፌዴሬሽኑ በዚህ ሳምንት አሳውቃለሁ አለ

ቀን:

ዓለም የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክን በጉጉት እየጠበቀ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በርከት ያሉ አገሮች፣ በተለያዩ ስፖርቶችና ውድድሮች የሚወክሏቸውን ብሔራዊ አትሌቶች ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአትሌቲክሱ ጠንካራ ተወዳዳሪዎችን በማሳተፍ የምትታወቀው ኬንያ በሁለቱም ጾታ የማራቶን ተወካዮቿን ይፋ አድርጋለች፡፡ ከመካከለኛ እስከ ረዥም ርቀት ማራቶንን ጨምሮ የምትጠበቀው ኢትዮጵያ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ በተለይም በማራቶን የተወካዮቿን ዝርዝር አለማሳወቋ እያነጋገረ ይገኛል፡፡

በተለያዩ ዓለማት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን ሲወዳደሩ ይታያሉ፡፡ እንደሚታወቀው ፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ በተለይም በአሁኑ ወቅት የቀረው ሁለት ወር ከመንፈቅ  መሆኑ ደግሞ፣ ብሔራዊ አትሌቶችን በመምረጥም ሆነ በማሳወቅ ረገድ ሙሉ መብትና ግዴታ ያለበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ምን እየጠበቀ ይሆን የሚሉ ጠያቂዎች በርክተዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ በበኩሉ እንዳለፉት ጊዜያት ስህተቶችን ላለመድገም ሲባል ነገሮችን በጥንቃቄ መመልከትና መወስንም ስለሚገባ ትኩረት ሰጥቼ እየሠራሁ ነኝ እያለ ነው፡፡

- Advertisement -

የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ አሁን ባለው ሁኔታ አገሮች እንደተባለው የተወካዮቻቸውን ዝርዝር በማሳወቅ ላይ መሆናቸው ግልጽ ቢሆንም፣ እንደ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዚህ ኦሊምፒክ በተለይም ከምርጫና መሰል ሥራዎች ጋር የተያያዘ ምንም ዓይነት ክፍተትም ሆነ ቅሬታ ተፈጥሮ መመልከት አይጠበቅም ይላሉ፡፡

በዚህ ረገድ ምንም እንኳ አትሌቶችን መምረጥ የፌዴሬሽኑ ኃላፊነት እንደሆነ ቢታመንም፣ ነገር ግን ደግሞ ክፍተት ላለመፍጠር በጉዳዩ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲሳተፍበት በማድረግ ምርጫውን ጨምሮ ሥራዎች በጥንቃቄ እየተሠሩ ስለመሆኑ ጭምር ኃላፊው ያስረዳሉ፡፡

ከማራቶን አትሌቶች ምርጫ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮች ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ወደ ፓሪስ የሚያቀኑት የማራቶን አትሌቶች ዝርዝር በይፋ ይታወቃል፡፡ እስከዚያው አትሌቶች የተወዳደሩባቸው የውድድር ቦታዎች፣ ያስመዘገቧቸው ሰዓቶች፣ ውድድሩ የተከናወነባቸው ሥፍራዎችና መሰል መሥፈርቶች በዓለም አትሌቲክስ ያላቸው ዕውቅና ማለትም የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ደረጃ ጭምር በብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴው አማካይነት እየተፈተሸ ግልጽና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል፡፡

በርካታ አትሌቶች በውድድር ዓመቱ ባደረጓቸው ውድድሮች፣ ለኦሊምፒክ ተሳትፎ የሚያበቃቸውን ሰዓት (ሚኒማ) ያሟሉ በመሆኑም ምርጫውን በጥንቃቄ መመልከት ማስፈለጉንም ተናግረዋል፡፡

በአትሌቲክሱ በተለይም በማራቶን ተወካዮቻቸውን ካሳወቁ አገሮች መካከል አትሌቲክስ ኬንያ  ይጠቀሳል፡፡ በዚሁ መሠረት በፓሪስ ኦሊምፒክ በማራቶን ኬንያን እንዲወክሉ የተመረጡት በወንዶች ያለፈው ኦሊምፒክ አሸናፊ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ፣ ቤንሰን ኪፕሩቶና አሌክሳድራ ሙትሴይ፣ ተጠባባቂ ቲሞቲ ኪፕላጋት ናቸው፡፡ በሴቶች ደግሞ ያለፈው ኦሊምፒክ አሸናፊዋ ፔሬስ ጄፕቺርቺር፣ ሔለን ኦበሪና ብሪግድ ጎስኬ ሲሆኑ፣ በተጠባባቂነት ደግሞ ሻሮን ሎክዲ ተካታለች፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...