Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርት ሰባ አምስት ቀናት የቀሩት የፓሪስ ኦሊምፒክ

 ሰባ አምስት ቀናት የቀሩት የፓሪስ ኦሊምፒክ

ቀን:

  • የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የት ጠፋ?

የመላውን ዓለም ኅብረተሰብ ካላንዳች ልዩነት የሚያስተሳስረው ታላቁ የኦሊምፒክ ጨዋታ ከአንድ ኦሊምፒያድ በኋላ ዳግም በፓሪስ ሊከሰት ሰባ አምስት ቀኖች ብቻ ቀርተውታል፡፡ የአውሮፓዋ ፈረንሣይ መዲና ፓሪስ 33ኛውን ኦሊምፒያድ ለማስተናገድ መሰናዶዋን እያጧጧፈች ነው፡፡ ፓሪስ ኦሊምፒክን ከ100 ዓመት በፊት አዘጋጅታ ነበር፡፡

 ሰባ አምስት ቀናት የቀሩት የፓሪስ ኦሊምፒክ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የኬንያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት
ፖል ቴርጋት ለፓሪስ ኦሊምፒክ
ዝግጅት አጋር ከሆነው ሳፋሪኮም
ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር ንጌዋ ጋር
ፎቶ፡ የኬንያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ

የኦሊምፒኩ አብሣሪ ችቦ ከኦሊምፒኩ መብቀያ ከግሪክ ኦሊምፒያ የተለኮሰው ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከወደብ ከተማዋ ማርሴይ መድረሱን የኦሊምፒክ ይፋዊ ድረ ገጽ አሳይቷል፡፡ ችቦው በፈረንሣይ ከተሞች ሲዘዋወር ቆይቶ ሐምሌ 19 በልዩ ሥነ ሥርዓት ‹‹የ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች›› ሲከፈት በስታዲየሙ ይለኮሳል፡፡ በጨዋታዎቹ ከሚካፈሉት አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያም እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡

የየአገሮቹ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ቅድመ ዝግጅቶቻቸውን እያቀላጠፉ መሆናቸውን ከሚያሳየው ነገር አንዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው በየዕለቱም ሆነ እያሠለሱ የሚያሠራጩት መረጃ ነው፡፡ ኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) እንደሚያደርገው ሁሉ የኦሊምፒኩ ጨዋታ ሊካሄድ ስንት ቀን እንደቀረው ‹100 ቀን›፣ ‹ሦስት ወር› ቀረው እያሉ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ባለፈ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና ከስፖርት ምክር ቤቶቻቸው/ከስፖርት ሚኒስቴር ጋር የሦስትዮሽ ስብሰባ እያዘጋጁ መግለጫ ሲሰጡ ይታያል፡፡

- Advertisement -

ከአፍሪካ ከግንባር ቀደም የአይኦሲ አባላት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምን እየሠራ እንደሆነ፣ እንደሌሎች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ንቁ አለመሆኑ በግልጽ እየታየ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ የሚመራው ብሔራዊ ኦሊምፒክ ስለ ዝግጅቱ፣ ምንስ እየተደረገ እንደሆነ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ምን እንደሚመስል፣ ጋዜጣዊ መግለጫው ቀርቶ እንደሌሎች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እስካሁን ድምፁን አላሰማም፡፡ ‹‹ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም›› ሆኗል፡፡

ለመሆኑ የኦሊምፒክ ኮሚቴው የፌስቡክ ገጽ በሥራ ላይ አለ ወይ ብሎ መጠየቅ ተገቢነት አለው፡፡

በ‹የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ› ስም ሁለት የፌስቡክ ገጾች አሉ፡፡ አንደኛው Ethiopian Olympic Committee ሲሆን፣ 10 ሺሕ ተከታዮች አሉት፡፡ ሎጎው የኦሊምፒክ ቀለበት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የታጀበበት ነው፡፡

የመጨረሻው ዘገባው/ፖስቱ ከአምስት ዓመት በፊት፣ ኖቨምበር 6 ቀን 2019 (ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም.) ነው፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አምባሳደር ሆቴል ማካሄዱን፣ ኮማንደር  ደራርቱ ቱሉ ወደ ሥራ አስፈጻሚ አባልነቷ መመለሷ የተዘገበበት ነው፡፡

ሁለተኛው የፌስቡክ ገጹ NOC- Ethiopia Olympic የሚል ሲሆን፣ 5.4 ሺሕ ተከታዮች አሉት፡፡ ሎጎ ሆኖ የተቀመጠው ‹‹1ኛ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ወጣቶች ጨዋታዎች 2014/1st Ethiopian Olympic youth games 2022›› በኦሊምፒክ ቀለበት ታጅቦ ነው፡፡

የመጨረሻው ዘገባው/ፖስቱ ከሁለት ዓመት በፊት ኦክቶበር 12 ቀን 2022 (ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም.) ሲሆን፣ እሱም የሐዘን መግለጫ መልዕክት ነው፡፡ ‹‹በስፖርት ጋዜጠኝነት አመራርነትና ደራሲነት የሚታወቁት አንጋፋው የስፖርት ሰው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለአድናቂዎቻቸው በሙሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ››፡፡

 የሚገርመው ነገር በዚህ ጽሑፍ እንደታየው የአሁኖቹ አመራሮች ወይም የጽሕፈት ቤቱ ባልደረቦች፣ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ እንደነበሩ አለማወቃቸው ነው፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በሌላ ስም አለኝ ካላለ በስተቀር በፊተኞቹና በአሁኖቹ አመራሮች የተከፈቱ ማኅበራዊ ገጾች ከአምስትና ከሁለት ዓመት በፊት ነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፡፡

 እንዴት ነው ነገሩ? ‹‹ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም›› ሆኗል፡፡

የመጽሔት ነገር

እዚህ ላይ አንድ ታላቅ ቁም ነገር ይነሳል፡፡ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በመጡ ቁጥር የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከልዑካኑ ጋር አብሮ የሚጓዝ መጽሔት ያዘጋጃል፣ ያሳትማል፣ ያሠራጫል፡፡ እንዳለ መታደል ሆኖ በሪዮ እና በቶኪዮ ኦሊምፒክ ወቅት በደቦ የተዘጋጁት መጽሔቶች በስሕተት የታጨቁ፣ ታሪክን ያፋለሱ፣ ተረትን ከታሪክ ጋር በሙጫ ፀያፍ ያጣበቁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

ዘንድሮም መጽሔት እየተዘጋጀ መሆኑ ይወሳል፡፡ ዘንድሮም እንዳለፉት ሁለት ኦሊምፒያዶች አንገት ያስደፋ ይሆን? ለነገሩ የኢትዮጵያ ስፖርት ተቋማት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ጨምሮ ታሪካቸውንና ጉዞአቸውን በተገቢው ባለሙያ ሰንዶ ለማስቀረት የታደሉ ላለመሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

የጎረቤት ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች የት ላይ ናቸው?

የሩቆቹን ትተን የጎረቤት አገሮች ብሔራዊ ኮሚቴዎች በሚያስደምም መልኩ ከሥር ከሥሩ መረጃን ለኅብረተሰባቸው እያሠራጩ ነው፡፡ የቅርብ ዘመኗ ጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የፓሪስ ኦሊምፒክ ሊካሄድ ሦስት ወር በቀረበት ሚያዝያ 16 ቀን ላይ ፕሬዚዳንቱ ኢንጂነር ጁማ ስቴፈን አገራቸው ፓሪስ እንደምትገኝና በኦሊም

ፒኩ እንደምትወዳደር ጠቁመዋል፡፡

 ከዚህም አልፎ ብሔራዊው ኦሊምፒክ ኮሚቴው ከብሔራዊ የወጣቶችና የስፖርት ምክር ቤት አባላት ጋር ሚያዝያ 17 በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አዳራሽ ተመካክሯል፡፡ ከተመካከረባቸው አጀንዳዎች አንዱ ለፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ዝግጅት ላይ የተደረገ ውይይት ነው፡፡ ተመካካሪዎቹም ዝግጅቱ የደረሰበትን ደረጃ ለማወቅ እንዳስቻላቸውም መናገራቸው ታውቋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 17 ቀን ሲያቀርብ፣ ስለ ፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅት እምን ላይ እንደደረሰ የቀረበ ነገር የለም፡፡ ከእንደራሴዎቹም በተለይ ከሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላትም ድምፅ አልተሰማም፡፡  በተመሳሳይ ዕለት ጁባ ላይ ደቡብ ሱዳኖቹ ስለ ኦሊምፒኩ ሲመካከሩ ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ስፖርት ባውራነት የሚመራው ተቋም መንግሥት ከወዲሁ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ሊያቀርብበት ይገባ ነበር ያሉ ተመልካቾች አልታጡም፡፡  

መሰናዷቸውን አጠናክረው ከቀጠሉ አንዱ የሆነው የዑጋንዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከኦሊምፒኩ በፊት በሰኔ አጋማሽ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኦሊምፒክ ቀንን በጋራ እናክብር ብሏል፡፡ ‹የኦሊምፒክ ቀን፣ የኦሊምፒክ መንፈስ፣ ስፖርት ለሁሉም› በሚል መሪ ቃላት የኦሊምፒክን እንቅስቃሴ የወዳጃዊነት፣ የመከባበርና የልህቀት እሴቶችን እናክብር ሲል አስተጋብቷል፡፡

የአትሌቲክስ በተለይ ከመካከለኛ እስከ ረዥም ርቀት ማራቶንን ጨምሮ የኢትዮጵያ ተፎካካሪ የሆነችው ኬንያ፣ ከኦሊምፒክ ቅድመ ዝግጅቷ ባሻገር በኮከቡ በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም አቀፍ ውድሮች ስኬታማ በነበረው ፖል ቴርጋት የሚመራው ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዋ፣ በኬንያ ግንባር ቀደም የቴሌኮሚኒኬሽን ብራንድ ከሆነው ሳፋሪኮም የአጋርነት ስምምነት ከሰሞኑ አድርጓል፡፡ ከቲምኬንያ ጋር አብሮ እንደሚሠራም ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...