Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየትግራይ ክልልን በዘጠኝ ወራት ሪፖርቱ ማካተት ባለመቻሉ ጫና እንደፈጠረበት ጤና ሚኒስቴር ገለጸ

የትግራይ ክልልን በዘጠኝ ወራት ሪፖርቱ ማካተት ባለመቻሉ ጫና እንደፈጠረበት ጤና ሚኒስቴር ገለጸ

ቀን:

በትግራይ ክልል በነበረው ግጭት ኮምፒዩተሮችና የኢንተርኔት ዝርጋታዎች በመበላሸታቸው የትግራይ ክልል ሪፖርት አለመላኩን፣ በዚህም ምክንያት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ውስጥ ባለመካተቱ ጫና እንደተፈጠረበት የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የክልሉ ሪፖርት ባለመላኩ ምክንያት በሥራዎቹ ላይ ጫና ማሳደሩን፣ ወደፊት ለሚከናወኑ ተግባራት እንቅፋት እንደሚሆን የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ደረጀ ዱጉማ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሐሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የጤና ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሟል።

- Advertisement -

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ  ደረጀ ዱጉማ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል በነበረው ግጭት ብዙ የጤና ጣቢያዎች፣ የጤና ኬላዎች፣ ኮምፒዩተሮችና የኢንተርኔት ዝርጋታዎች መበላሸታቸውን፣ እንዲሁም አብዛኞቹ የጤና ባለሙያዎች በሥራ ላይ ስላልነበሩ የሪፖርት ማቅረብ ሒደቱ ተቋርጦ መቆየቱን ገልጸዋል።

በ2016 ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ ሪፖርቶችን ለመላክ የተወሰነ ሙክራ እንደነበር ለሪፖርተር የገለጹት ደረጀ (ዶ/ር)፣ ግጭቱ ከተከሰተ ጀምሮ በክልሉ ያለውን የጤና ዘርፍ የሚመለከት ሪፖርት ተልኮ እንደማያውቅ አስረድተዋል። ‹‹ይህ ማለት ግን በስልክና በተለያዩ መንገዶች ሪፖርቶችን አንወስድም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ትክክለኛውና በሚኒስቴሩ የዕቅድ አፈጻጸም መካተት የሚገባው ሪፖርት የሚላክበት የመረጃ ሥርዓት በኢንተርኔት ብቻ ስለሆነ ለማካተት አልተቻለም፤›› ብለዋል።

ከሁለት ወራት በኋላ ክልሉ ሪፖርቱን ለመላክ መዘጋጀቱን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፣ የሚላከው ሪፖርት ከ2016 ዓ.ም. በፊት የነበረውን አፈጻጸም ጭምር እንደሚካተትበት፣ በዋናነት እየተሠራበት ያለው ግን ከሐምሌ ጀምሮ የ2017 ዓ.ም. ሪፖርት በተሟላ መልኩ እንዲላክ ለማስቻል ነው በማለት አስረድተዋል።

በትግራይ ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማትን ለመደገፍ ሚኒስቴሩ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን የሰጡት ደረጀ (ዶ/ር)፣ ከ400 በላይ የሚሆኑ ኮምፒዩተሮች መዘጋጀታቸውንና ሰሞኑን እንደሚሠራጩ ተናግረዋል፡፡ በወረቀት የተላኩ መረጃዎችን በማሳተም መቀሌ ከተማ መድረሳቸውንና፣ ወደ ወረዳዎቹ ለመላክ የፋይናንስ ድጋፍ መደረጉንም አስታውቀዋል።

ከትግራይ ክልል ውጪ አሁንም በግጭት ዓውድ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ሪፖርቶች በወቅቱ እየተላኩ አለመሆናቸውን፣ ለዚህ ማሳያም በአማራ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት 65 በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ብቻ ሪፖርት እንደላኩ አስረድተዋል። ‹‹ሆኖም በአፈጻጸም ወደኋላ ከቀሩና ግጭት ካለባቸው አካባቢዎች ጋር በተለየ መንገድ በየሁለት ወራት እንገናኛለን፤›› ብለዋል።

ድጋፍ የሚደረገው ሪፖርቶቹን መሠረት አድርጎ በመሆኑ፣ ሚኒስቴሩም ሆነ አጋር ድርጅቶች የሚያስፈልገውን ዕገዛ እንዳያደርጉ እንቅፋት እንደሚሆንባቸው፣ ግብዓቶችን ለመላክና በአጋር ድርጅቶች የሚደገፉ ፕሮጀክቶችን ለማንቀሳቀስ፣ የሪፖርቶች በወቅቱ አለመቅረብ ችግር መሆኑን  ደረጀ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...