Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከውጭ ከሚመጡ ግብዓቶች ጥገኝነት እንዲላቀቅ ተጠየቀ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከውጭ ከሚመጡ ግብዓቶች ጥገኝነት እንዲላቀቅ ተጠየቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከውጭ ከሚመጡ ግብዓቶች ጥገኝነት እንዲላቀቅ የዘርፉ ባለሙያዎች ጠየቁ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ‹‹የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተግዳሮት፣ መውጫ መንገዶችና የሕግ አውጭው ሚና›› በሚል ርዕስ ሐሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚመለከታቸው የዘርፉና የመንግሥት አካላት በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ የኮንስትራክሽን ባለሙያውና የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማኅበር የቦርድ ሊቀመንበር ውብሸት ዠቅአለ (ዶ/ር)፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በተመለከተ ባቀረቡት የመነሻ ጹሑፍ፣ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች በአመዛኙ በገቢ ንግድ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው በአማካይ ከ30 በመቶ በላይ የውጭ ምንዛሪ እንደሚጠይቁ አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በገቢ ምርቶችና በውጭ ምንዛሪ ላይ ጥገኛ መሆኑና ዓለም አቀፍ ገበያውም በበቂ ደረጃ ተገማች ባለመሆኑ፣ የገበያ ዋጋ ሲንር፣ አለመግባባት ሲከሰት፣ የውጭ ምንዛሪና የፀጥታ ችግር ሲፈጠር በቀላሉ የሚጎዳ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡

ተቋማዊ ያልሆነና በግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ የኮንስትራክሽን ኩባንያና አሠራር ችግር አለመቀረፉ፣ ፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠኑ፣ በመንግሥት የገንዘብ ምንጭ ላይ ጥገኛ መሆኑ፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪው ዋና ዋና ባለድርሻዎች አለመቀናጀትና የአቅም ውስንነት መኖሩ፣ ያልተገባ የአሠሪ ጣልቃ ገብነት የሚበዛበት መሆኑ በዘርፉ ላይ አደጋ ተደቅኖበታል በማለት ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ የአማካሪ መሐንዲሶችና አርክቴክቶች ማኅበር የቦርድ ፕሬዚዳንት ዳዊት ኡርጌቾ (ዶ/ር)፣ ‹‹የኢንዱስትሪው ቀጥተኛ ባለድርሻዎች ምልከታ›› በሚል ባቀረቡት የጥናት ጹሑፍ፣ ከውጭ በሚገቡ የግንባታ ግብዓቶች ላይ ጥገኛ መሆንና የምንዛሪ እጥረት፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪው የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከጊዜና ከዋጋ አንፃር ከታለመው በላይ መሆን የዘርፉ ትልቁ ማነቆ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ ጥናቶችንና ምርምሮችን በተቀናጀ መንገድ በማካሄድ ምርጥ ተሞክሮዎችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ለማስረፅ  ውስንነት መኖሩ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቅ የሰው ኃይል በብዛት ቢኖርም የሚታየውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት አለመቻልና የመሳሰሉትን ችግሮች ጠቅሰዋል፡፡

ዘርፉ እንዲሻሻል ለግንባታ ዕቃዎች፣ ግብዓቶችና ምርቶች ከዓለም አቀፍ ደንቦች ጋር የሚስማማ የኢንዱስትሪ አቀፍ ወጥ ብሔራዊ ደረጃ ማዘጋጀት፣ የአገር ውስጥ ምርቶችን በዓይነትም ሆነ በጥራት ለማስፋፋት የቴክኖሎጂ ሽግግርን፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ልዩ መብቶችንና የፋይናንስ አቅርቦትን በጥናት ላይ በመመረኮዝ ማመቻቸትና የአገር ውስጥ ምርቶችን/ግብዓቶችን ለማሻሻልና ለማስፋፋት ለምርምርና ለልማት ፈንድ መመደብ እንደሚስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ውብሸት (ዶ/ር) በሰጡት አስተያየት ትላልቅ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን በማቋቋም ከአገር አቀፍ እስከ ዓለም አቀፍ የዕድገት አቅጣጫዎችን መተለይም፣ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ ተወዳዳሪነትንና ምርታማነትን ያማከሉ የዕድገት አቅጣጫዎች ማካተት፣ የመንግሥት ቀጥተኛ ተሳትፎ ማጠናከር፣ የመንግሥትና የግል ትብብርና ድርሻ እያደገ የሚመጣበት ከቁጥጥር ወደ ማስቻል ተኮር የሚሸጋገርና ከአገር ወደ ዓለም አቀፍ ውድድር የሚያድግ ሥርዓት እንዲፈጠር ጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...