Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን 1846 ድርጅቶችን ሊሰርዝ ነው

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን 1846 ድርጅቶችን ሊሰርዝ ነው

ቀን:

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ሪፖርት ያላቀረቡ 293 ድርጅቶችንና በአዲሱ አዋጅ 1113/2011 መሠረት ዳግም ያለተመዘገቡ 1553 ድርጅቶችን ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ህልውናቸው እንዲከስም መወሰኑን ገለጸ፡፡

ባለሥልጣኑ ውሳኔውን ያሳለፈው ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ካካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ በኋላ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በአዋጁ አንቀፅ 70 ድርጅቶች ህልውናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው መቀመጡንና ህልውናቸውን የሚያረጋግጡትም በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሰሞን ሪፖርት በማቅረብ መሆኑን የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ መኮንን ግርማ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ላለፉት ሦስት ዓመታት ማለትም ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ ድጋሚ ላልተመዘገቡና ሪፖርት ላላቀረቡ ድርጅቶች ጥሪ ሲያደረግላቸው የነበር መሆኑን ገልጸው፣ ህልውናቸው አንዲከስም የተደረጉ ድርጅቶች ጥሪውን ተቀብለው ያልመጡት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የበጎ አድራጎት ሥራ በግዴታ የሚሠራ አይደለም ያሉት አቶ መኮንን ‹‹ሥራ ላይ ሆነው የገንዘብ እጥረት አጋጥሟቸው ቢሆን እንኳን ይህን ቢገልጹ ሪፖርት እንደማቅረብ ይወሰድላቸው ነበር፤›› ብለዋል፡፡

- Advertisement -

ነገር ግን ባለሥልጣኑ እነዚህ ድርጅቶች መኖራቸውንም እንደማያውቅ ገልጸዋል፡፡ ድርጅቶቹ ከሚያቀርቡት ሪፖርት ባለፈ ባለሥልጣኑ በሚያደርገው ክትትል ድርጅቶቹ ሥራ ላይ አለመሆናቸውን ማረጋገጡን አስመልክቶ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው ባለሙያው፣ የመስክ ክትትል መኖሩንና ባስመዘገቡት አድራሻ ጭምር ለማግኘት ጥረት ተደርጎ ምንም ዓይነት ምላሽ አለማግኘታቸውን አብራርተዋል፡፡ 

293 ድርጅቶች ከሐማሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በፊት ባሉት ቀናት ወደ ባለሥልጣኑ ቀርበው ምክንያታቸውን በመግለጽ ሪፖርታቸውን ማቅረብ የሚችሉበት አማራጭ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ከተደረገው የለውጥ ሥራ በፊት በሥራ ላይ የነበረው አዋጅ መሻሻሉን ተከትሎ ዳግም ምዝገባ ያላካሄዱ 1553 ድርጅቶችም የቅጣት ክፍያቸውን በመክፈል ዳግም የሚመዘገቡበት ዕድል መኖሩንም አስረድተዋል፡፡

ይህ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ድርጅቶቹ ይወክለኛል ብለው ካቋቋሙት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር መነጋገራቸውንም አክለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ዳግም ያልተመዘገቡ ድርጅቶችን እንዲሁም ህልውናቸውን ማረጋገጥ ያልቻሉ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...