Sunday, May 19, 2024
Homeስፖንሰር የተደረጉወንድማማቾቹን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረገው ብሔር ተኮር ግጭት

ወንድማማቾቹን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረገው ብሔር ተኮር ግጭት

Published on

- Advertisment -

ኢትዮጵያን በርካቶች የብዙኃን እናት፣ የብዙኃን አገር፣ ሲሉ ይጠሯታል፡፡ ለዚህም የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህሎችና ሃይማኖቶች መኖሪያ መሆኗ እንደ አብነት ይነሳል፡፡ በአገሪቱ የሚገኙ ከ83 የሚበልጡ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በክፉም ሆነ በደጉ ጊዜ ተከባብረውና ተደጋግፈው የመኖር ዘመናትን የዘለቀ ባህል አዳብረዋል፡፡ መልከ ብዙዋ ኢትዮጵያ በዘመናት ጉዞዋ የተለያዩ የታሪክ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡

በእነዚህ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ክስተቶች ሕዝብ አብሮነትን እያስቀደመ በጋራ ሲኖር ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ በአገሪቱ በተለያየ ጊዜያት በሚፈጠሩ ፖለቲካዊ ሁነቶች እንዲሁም የብሔር መልክ የተላበሱ ግጭቶች መፈጠራቸው አልቀረም፡፡ በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት በአገሪቱ የተካሄደውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ በኦሮሞና አማራ ቡድኖች መካከል የብሔር መልክ የተላበሱ ግጭቶች ሲከሰቱ ቆይተዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል ከአርቲስት ድምፃዊ አጫሉ ሁንዴሳ ጋር የተያያዘው ክስተት አንዱ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. የዝነኛው አርቲስት አጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተፈጠረው ሁከት እና የደቦ ጥቃት ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰላም ውሎ አለማደር ምክንያት ሆነ፡፡

በአርቲስቱ ግድያ የተቆጩ ወጣቶች ሐዘናቸውን በሠልፉ ለመግለጽ ወደ አደባባዮችና መንገዶች ተመሙ፡፡ ሠልፉ ቀስ በቀስ ወደ ሁከት በመቀየሩ ሰላማዊ የከተማዋ ነዋሪዎችን ኢላማ ያደረገ እና ብሔር ተኮር ጥቃቶችን ተስተናግደዋል፡፡

በሻሸመኔ ከተማ መልካሲባር አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሽብሬ ራሚዮ ሰዎች በማንነታቸው ጉዳት ሲደርስባቸው ማየት ህሊናዋ አልፈቀደም ነበር፡፡ ሰዎች በማንነታቸው ጉዳት ሲደርስባቸው በማናለብኝነት ለማለፍ ስላልቻለች ለሰዎች ከለላ ለመሆን መሰዋዕትነት ለመክፈል ቆርጣ ተነሳች፡፡

በወቅቱም ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጠረው ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ አራት ሰዓት ነበር የምትለው ወ/ሮ ሽብሬ በጊዜው ከተማዋ በበርካታ ሰዎች መወረሯን ታስታውሳለች፡፡ ከአካባቢው ከኦሮሞ ብሔረሰብ ውጭ ሌሎች ብሔረሰቦች የሚኖሩበት ሲሆን በእነዚህም ሰዎች ላይ አስከፊ ድብደባና ስቃይ ሊደርስባቸው ችሏል፡፡ በዚህ አስጨናቂ ቀንና ሌሊት ጥቂት ወራትን ባስቆጠረው የአራስነት ጊዜዋ ባልጠነከረ ሰውነቷ እንዲሁም በአልፀና ወገቧ አራስ ልጇን ታቅፋ ሰዎችን ከአጥቂዎች በመታደግ ሌሊቱን አሳልፋለች፡፡

ወ/ሮ ሽብሬ ራሚዮ ብሔርና ዘር ሳይቆጥሩ ሕይወት ከመታደግ ባለፈ የተጎጂዎችን ሀብትና ንብረታቸው እንዳይወድም ወጣቶችን እየተማፀነች ለሳምንታት ንብረታቸውን በመጠበቅ ለባለቤቶቹ አስረክባለች፡፡ ሰዎች በማንነታቸው ጉዳት እንዳይደርስባቸው በብዙ የደከመችው ወ/ሮ ሽብሬ ጥረቷ ፍሬ አፍርቶ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት መታደግ ብትችልም በሌላ በኩል ትችት ደርሶባታል፡፡ ይህን መልካም ተግባር በማድረጓ ተገቢ ያልሆኑ ንግግርን ጨምሮ ሞራል የሚነኩ ትችቶችን ተቀብላለች፡፡

ዛሬ ላይ በእኔ ጥረት ሕይወታቸው የተረፈ ሰዎችን ማየቴ ፍጹም ደስተኛ እንድሆን አድርጎኛል የምትለው ወ/ሮ ሽብሬ በቀጣይ በሕዝቦች መካከል የሚፈጠረውን ግጭት ለማስወገድ ትውልድ ላይ መሠራት አለበት ትላለች፡፡

በሰሜን ሸዋ የምትገኘው አጣዬ ከተማ በዋናነት የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ በጋራ በአብሮነት የሚኖርባት ከተማ ነች፡፡ ሕዝብ በአርሶ አደርነትና በከፊል አርብቶ አደርነት ይተዳደራል፡፡ ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም. ድረስ የአጣዬ ከተማ በሃይማኖትና በብሔር ግጭት ስትናጥ ቆይታለች፡፡ መምህር ኤርሚያስ ይመር በአጣዬ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ከመምህርነት ባለፈ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ናቸው፡፡

ለተከታታይ ዓመታት በግጭት አዙሪት ስትናጥ የከረመች አጣዬ በ2015 ዓ.ም. ሌላ የሰላም ዕጦት ተደቀነባት፡፡ የብሔር መልክ ይዞ የመጣው ይህ ግጭት በመምህር ኤርሚያስ የግል ሕይወትና ቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ቢያደርስም የራሳቸውን ጉዳትና ቂም በቀል በመተው እንደ ሃይማኖት አባትም ሆነ እንደ አገር ሽማግሌ በመሆን ከባልደረቦቻቸው ጋር የሰዎችን ሕይወትና ንብረት እንዳይጠፋ በብዙ ደክመዋል፡፡

በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በትግራይ የነበረው ጦርነት ተከፋፍቶ በ2013 ዓ.ም. አጣዬ ከተማ ሲደርስ ሌላ መከራና ፈተና አስተናግዳለች፡፡ በጦርነቱ በከተማም የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የሕወሓት ተባባሪ ናቸው በሚል ምክንያት የተገፉበት ወቅት ነበር፡፡ በወቅቱም ወደ ከፋ ጉዳት እንዳያመራ በርካታ ሰዎች ጥረት ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ መምህር ኤርሚያስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ መምህር ኤርሚያስ በምክራቸውና በአስታራቂነታቸው ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተቀባይነትን አግኝተዋል፡፡

በሻሸመኔ ከተማ ኩሩፉ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ዊልቤካ ለሚ ብዙ ንብረት ያወደሙና ጥቂት ለማይባል የሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውን ግጭት በቁጭት ያስታውሰዋል፡፡ ከብሔሬ አይወለዱ ከዘሬ አይመዘዙ ሳይሉ በሁከትና በብጥብጥ ቤቶች እንዳይቃጠሉ ቀኑን ሙሉ ከባለቤታቸው ጋር ሲጠብቁ መዋላቸውን ይናገራሉ፡፡ ጉዳት አድራሾችን በመማፀን ብቻ ሁኔታውን መቆጣጠር እንዳልቻሉ በመረዳታቸው የወላጆች ጭንቀት እፎይታ የነሳቸው አቶ ዌልቤካ በእሱና በባለቤቱ ሰብዓዊ ዕርዳታ ከመቶ በላይ ሕፃናት ከሞት ማዳን ችለዋል፡፡

ይህ መልካም ተግባር የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዘመናት በመተሳሰብ ተደጋግፈው መኖራቸውን ከማሳየትም በተጨማሪም ከብሄርና የፖለቲካ ልዩነቶች በላይ ሰብዓዊነት እንደሚቀድም ያሳያል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አንዱ የሌላው ስጋት ሳይሆን መከታ እና መሸሸጊያ እንደሆነ በችግሩም በደስታውም በሃዘኑም ጊዜ በጋራ ተካፋይ ሆኖ የኖረ እና ትስስሩም ጥብቅና ጠንካራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በተለይ የሃይማኖት አባቶች፤ ሴቶች እና አረጋውያን ግጭትን በማረጋጋት ላይ ያለቸውን ጉልህ ሚና ያሳየ ነው በቀጣይም የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም ማጎልበት ቢቻልና ቢደገፉ ከዚህ የበለጠ ስራ መስራት እንደሚችሉም ማሳያ ነው፡፡

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎች የሚደረጉባቸው የተለያዩ አጋጣሚዎችና ሰበቦች...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት ብትችል፣ ከበርካታ ታዳጊ አገሮች የተሻለ...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር የሥልጣን መንበር...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣ እንደነገሩም ሆነ ለአንደበት ወግ ያህል...

ተመሳሳይ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

ኦርቶፔዲክስ

በጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት ህመሞች ላይ የላቀ ጥበብ፡- የአጥንት ጉዳትን ችግር ከመመርመርም ያለፈ የአጥንትና መገጣጠሚያ...

የአየርላንድ እና የኢትዮጵያ የ30 ዓመታት ግንኙነት ስናከብር

ዘንድሮ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት የጀመረችበት 30ኛ ዓመት ቢሆንም ግንኙነቱ ግን ከዚያም በበለጠ...