Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበድርቅና በጦርነት ተጎድተዋል ለተባሉ የአርብቶ አደር ክልሎች የ38 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ...

በድርቅና በጦርነት ተጎድተዋል ለተባሉ የአርብቶ አደር ክልሎች የ38 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ቀን:

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ለተፈጠሩ የድርቅ፣ ረሃብ፣ የአንበጣ ወረርሽኝ፣ እንዲሁም በተከሰቱ የእርስ በርስ ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው የአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ ማኅበረሰቦችን የጤና ፍላጎት ምላሽ ይሰጣል የተባለ ፕሮጀክት በ38 ሚሊዮን ዶላር ይፋ ተደረገ።

 ከተያዘው የ38 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ አሥር በመቶ ወይም 3.5 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው የሚሸፈነው በኅብረተሰቡ ሲሆን ቀሪው 35 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ነው ተብሏል።

ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚቆየው ፕሮጀክቱ፣ በአፋር በሶማሌ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞንና በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን አካባቢዎች ውስጥ  በሚገኙ የአርብቶ አደር አካባቢዎች እንደሚተገበር በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ኤሌኖር ታፕዬንጎ ተናግረዋል።

- Advertisement -

በየአካባቢው የሚፈጠሩ ግጭቶች በየወቅቱ ለሚከሰቱ በሽታዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት መሰናክል ከመሆናቸው በላይ መደበኛ የጤና አገልግሎት አቅርቦቶችን ተደራሽ እንዳይሆኑ አድርገዋል ያሉት ዳይሬክተሯ፣ በእነዚህ አካባቢዎች በግጭት ምክንያት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ከማቋቋም ጀምሮ ሌሎች የጤና አገልግሎቶችን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መልሶ ለመገንባት መታቀዱን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ በአራቱ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ 35 የአርብቶ አደር ወረዳዎችን ያቀፈ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የሥነ ተዋልዶ ጤና፣ በሥርዓተ ምግብ፣ የእናቶችና የሕፃናት፣ የአፍላ ወጣቶች፣ የጨቅላ ሕፃናት ጤና እንዲሁም የቤተሰብ ዕቅድን ማዕከል ያደረገ ፕሮጀክት መሆኑን ሚኒስትሯ አክለዋል፡፡

በአርብቶ አደር አካባቢ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የአኗኗር ዘይቤ፣ ሃይማኖት፣ ወግና ባህል በጠበቀ መልኩ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻልና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እየተሠራ እንደሆነ የገለጹት መቅደስ (ዶ/ር)፣ የአርብቶ አደር አካባቢዎች በመልካ ምድራዊ አቀማመጣቸው፣ የመንገድና የአሰፋፈር ሁኔታቸው እንዲሁም ሌሎች መሰል ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ማኅበረሰቡ ጤናው ተጠብቆ እንዲኖር  በስፋት ይሠራል ብለዋል።

ፍትሐዊነት ከጂኦግራፊክ ልዩነት ባለፈ የሥርዓተ ፆታ፣ የኢኮኖሚ፣ የአኗኗር ሁኔታ፣ የዕውቀት ደረጃዎችና የመሠረተ ልማት ፍትሐዊነት ላይ ያተኮረ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋልም ተብሏል።

የየክልሎቹ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው የተጠቀሱት ችግሮች በስፋት እንዳሉ ተናግረው፣ ፕሮጀክቱ የተሻለ ነገር እንደሚያመጣላቸው ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

በተለይ በወባ በሽታ፣ በጎርፍ አደጋና በድርቅ የተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ያለባቸውን የምግብና የመድኃኒት እጥረት ለማቃለል እንደሚረዳቸው አብራርተዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...