Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምቻይና በሩሲያና በኢራን ላይ እንድትፈጥር የሚፈለገው ተፅዕኖ

ቻይና በሩሲያና በኢራን ላይ እንድትፈጥር የሚፈለገው ተፅዕኖ

ቀን:

ከሩሲያና ኢራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው የቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ከአምስት ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ሰኞ ሚያዝያ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምረዋል፡፡

ቻይና በሩሲያና በኢራን ላይ እንድትፈጥር የሚፈለገው ተፅዕኖ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሊየን ከቻይና
ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር መክረዋል (ሮይተርስ)

መነሻቸውን ፈረንሣይ ያደረጉት ጂንፒንግ፣ ከአውሮፓ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር የጀመሩት ጉበኝት፣ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም ኢራን የጦር መሣሪያ ክምችቷን እንድትገድብ ውይይት ማድረግንም አካቷል፡፡

በአውሮፓና በቻይና መካከል በችግር እየተከበበ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ማስተካከልም አንዱ አጀንዳ እንደሆነ አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

- Advertisement -

የአትላንቲክ ካውንስል ግሎባል ቻይና ሃብ መረጃ እንሚያሳየውም፣ ጂንፒንግ ሦስት ግቦችን ይዘው የአውሮፓ ጉብኝታቸውን እያደረጉ ነው፡፡ ሩሲያና ዩክሬን ለገቡበት ጦርነት እልባት መስጠትና ቻይና ለሩሲያ ወግናለች በሚል የአውሮፓውያኑና የቻይና ግንኙነት በመሻከሩ ይህንን መጠገን፣ ከዚህ ጎን ለጎን የአውሮፓንና የቻይናን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ማስጠበቅ እንዲሁም ቻይና ለሰርቢያና ሃንጋሪ ያላትን ጠንካራ ግንኙነት ለማሳየት ያለመ ነው፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በበኩሉ፣ ቻይና በሩሲያና ኢራን ላይ ተፅዕኖ እንድትፈጥር ይፈልጋል፡፡

ከ ጂንፒንግ ጋር የተወያዩት የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሲላ ቮን ደር ሊየን የጠየቁትም፣ ቻይና ከሩሲያ ጋር ባላት ግንኙነት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት እንድታቆም እንድታሳምን ነው፡፡

ኢራን ለጦር መሣሪያ ምርቷ ገደብ እንድታበጅም ጂንፒንግ እንዲያግባቡ አደራ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በፈረንሣይ ፓሪስ ከ ጂንፒንግ ጋር የመከሩት ሊየን፣ የንግድ ጉዳዮችን ቢያነሱም፣ አፅንኦት የሰጡት ለሩሲያ ዩክሬን ጦርነትና ለኢራን የመሣሪያ ክምችት  ነው፡፡

ቻይና አጋሯ ሩሲያ ጦርነት እንድታቆም እንደምታሳምን፣ የሚሳኤልና የድሮን ምርቷን እያስፋፋች ያለችው ኢራንም የጦር መሣሪያ ምርቷ ላይ ገደብ እንድታደርግ ቻይና ትልቁን ሚና እንደምትጫወት የአውሮፓ ኅብረት ተስፋ አድርጓል፡፡

‹‹የሩሲያን የኑክሌር ሥጋትነት ለማርገብ ቻይና ወሳኝ ሚና አላት ›› ሲሉም ሊየን ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ አገራቸው የኑክሌር ጦር ልምምድ እንድታደርግ ትዕዛዝ ከሰጡበት ዕለት የገጠመው የቻይናና የአውሮፓ ውይይት፣ የኑክሌር ጉዳይ አጀንዳ እንዲሆንም ዕድል ፈጥሯል፡፡

የምዕራባውያን አገሮች ወደ ዩክሬን ወታደር እንልካለን ማለታቸውን ተከትሎ፣ ሩሲያ የኑክሌር ጦር ልምምድ እንዲደረግ ትዕዛዝ መስጠቷ ለአውሮፓውያኑ ሥጋት ነው፡፡ ሊየን እንደሚሉትም፣ ጂንፒንግ ሩሲያ የኑክሌር ሥጋትነቷ እንዲቀንስ ዋና ሚና መጫወት ይችላሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ማክሮን ባለፈው ሳምንት ዩክሬን የደጀን ድጋፍ ከጠየቀች የምድር ተዋጊ ወታደሮችን ሊልኩ እንደሚችሉ አሳውቀው ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት ማክሮን፣ ኮሚሽነሯ ሊየን እንዲሁም ጂንፒንግ በንግድ ዙሪያም ተወያይተዋል፡፡

በቻይናና በአውሮፓ መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት የተመጣጠነ እንዳልሆነ፣ ግንኙታቸው ባልተመጣጠነ የገበያ ተደራሽነት እየተጎዳ እንደሚገኝና ቻይና ለኢንዱስትሪዎቿ የምታደርገው ድጎማ ግንዱን እንዳዛባው ተነስቷል፡፡

ውይይቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ሊየን፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች በቻይና የኢንዱስትሪ ምርቶች እንደማይጥለቀለቁ ገልጸዋል፡፡

ጂንፒንግ በበኩላቸው፣ ቻይና ከአውሮፓ ጋር ያላትን ግንኙነት የቻይና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ  ቅድሚያ እንደሚሰጠው፣ ሁለቱም ወገኖች ለትብብሩ አፅንኦት ሊሰጡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...