Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹እኔን ኢያሱ በወርቁ መታኝ››

ትኩስ ፅሁፎች

በአፄ  ኢያሱ ዘመነ መንግሥት እንደሆነው፤ አንድ መምህር በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ጉባዔ ዘርግቶ ሲያስተምር ሳለ አፄ ኢያሱ እጅ ለመንሣት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይገባሉ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ንጉሡን አይተው ተነሥተው ሲያሳልፉ መምህሩ ሳይነሣ ይቀራል፡፡ እጅ ነሥተው ሲመለሱ አሁንም ተቀምጦ ያሳልፋቸዋል፤ ነገሩ ቢደንቃቸው መጨረሻውን ሊያዩ አልፈውት ተቀመጡ። በሙያው ያከብሩት ነበርና የወርቅ ዳረጎት ጣሉበት፡፡ እርሱ ለተማሪዎቹ አንዱን ቅኔ ቆጥሮ ተማሪዎቹ ያን የነገራቸውን እስኪያጠኑት ድረስ ሌላውን ቅኔ በኅሊናው እያዘጋጀ ነበርና የወርቅ ዳረጎቱ ድንገት ሲያርፍበት፣ አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ንጉሥ መሆናቸውን ዐውቆ ወዲያው ‹‹በእስጢፋኖስ አዕባን እንዘ የኀልቁ፤ ዘበጠኒ ኢያሱ በወርቁ›› (ደንጊያዎች በእስጢፋኖስ ላይ ሲያልቁ እኔን ኢያሱ በወርቁ መታኝ) ብሎ ተቀኝቷል።

 – ጃንደረባው

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች