Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ማህሌተ ገንቦ

ትኩስ ፅሁፎች

ባጭር ቀረን ስንል – እድሜ ላበደሩን

ቀርፀው ላሳመሩን

ለኩሰው ላበሩን

ቺርስ!!

ፊታችንን  ዐይተው -እንደተቸገርነ- ካይናችን  ላወቁ

ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው-ቆመው ላልጠበቁ

ቺርስ!!!

ወድቀው ለማይጥሉ – ነግሠው ለሚያነግሡ

ነውራችንን  ዐይተው

ልክ እንደ ድመት ኩስ ለሚያለባብሱ

ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ

ቺርስ!!!!

ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን

ቀልደው ላሳቁን-ተጫውተው ላከሙን

በቸከ ዘመን ላይ-

ሥጋ ለበስ ትንግርት – ሆነው ላስደመሙን

ቺርስ!!!!!

– ከበዕውቀቱ ሥዩም ገጽ የተገኘ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች