Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትቅዱስ ጊዮርጊስ ዘሪሁን ሸንገታን አገደ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘሪሁን ሸንገታን አገደ

ቀን:

‹‹ስትራቴጂካዊ ውሳኔ እንጂ ዕገዳ አይደለም››

አቶ ዳዊት ውብሸት፣ የክለቡ ቦርድ አባል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ሥራ አመራር ቦርድ ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ ሆነው ሲያገልግሉ የቆዩት ዘሪሁን ሸንገታና የበረኞች አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ ተለዋጭ መመርያ እስኪደርሳቸው ድረስ ከማሠልጠን ተግባራቸው ታግደው እንዲቆዩ ወሰነ፡፡

- Advertisement -

የስፖርት ማኅበሩ ቦርድ ለዚህ ውሳኔ የበቃው የዋናውን ቡድን ወቅታዊ ብቃትና ቁመና በጥልቀት ከገመገመ በኋላ፣ የዋናው ቡድን አሠልጣኝና የበረኞች አሠልጣኝ ላይ የወሰደው ስትራቴጂካዊ ውሳኔ እንጂ ዕገዳ አለመሆኑን ጭምር ይፋ አድርጓል፡፡

ቦርዱ በምትካቸው የዋናው ቡድን ምክትል አሠልጣኝ የነበረው ደረጀ ተስፋዬ ዋና አሠልጣኝ፣ የወጣት ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ የነበረው ሳምሶን ሙሉጌታ ወደ ዋናው ቡድን አምርቶ ምክትል አሠልጣኝ ሆነው እንዲሠሩ ከማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን ጀምሮ በጊዜያዊነት እንዲያሠለጥኑ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከቦርዱ ውሳኔ ጋር ተያይዞ በተለይም የዋናው ቡድን አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የዕገዳ ጉዳይ ለስፖርት ቤተሰቡ መነጋገሪያ መሆኑ አልቀረም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አሠልጣኙ የቅዱስ ጊዮርጊስን ቡድን በዋና አሠልጣኝነት ከተረከቡ በኋላ ከሳቸው በፊት በተለያዩ የውጭ አሠልጣኞች ያልተሳካውን ውጤት፣ ያውም ለሁለት ተከታታይ ዓመት ያሳኩ ከመሆኑ አንፃር በመመልከት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የቦርድ አባልና የማርኬቲንግ ባለሙያ አቶ ዳዊት ውብሸት በበኩላቸው፣ ‹‹በዋናው ቡድን አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የቅዱስ ጊዮርጊስን ክብር ከማስጠበቅ አኳያ የተወሰደ ስትራቴጂካዊ ውሳኔ እንጂ እንደሚባለው ዕገዳ አይደለም፤›› ይላሉ፡፡

ሆኖም ግን በዚህ ወቅት የክለቡ ወቅታዊ አቋምና ብቃት ከሚጠበቀው በታች እየወረደ መምጣቱ የስፖርት ማኅበሩ ሥራ አመራር ቦርድ ባደረገው ግምገማ ማረጋገጡን የሚናገሩት አቶ ዳዊት፣ ‹‹ውሳኔው እንደ ክለብ አስተዳዳሪ በሁሉም አቅጣጫ መመልከት ያለብንን ሁሉ ተመልክተን፣ በተለይም የቅዱስ ጊዮርጊስን ክብርና ጥቅም ማስቀደምም ስላለብን ማድረግ ያለብንን ነው ያደረግነው፤›› ብለው፣ ይህንኑ ዘሪሁንን ጨምሮ ሁሉም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ቤተሰብ የሚጋራው ትክክለኛ አካሄድ ስለመሆኑ ጭምር ይናገራሉ፡፡

አሠልጣኝ ዘሪሁን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ካሳካው ውጤት አንፃር ብቻም ሳይሆን፣ ቡድኑ በውድድር ዓመቱ ከሚገኝበት ደረጃ አንፃርም ለስንብት የሚያበቃው እንዳልሆነ የሚናገሩም አልጠፉም፡፡

ለዚህ አቶ ዳዊት፣ ‹‹ለውጤቱ ምንም እንኳን የአሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ስም ከፊት መቅደሙ የተለመደና የሚታወቅ ቢሆንም፣ የሥራ አመራር ቦርዱ የዕለት ዕለት ክትትልና ቁጥጥር ደግሞ ለሰከንድም ቢሆን ሊዘነጋ እንደማይገባ ሊታወቅ ይገባል፤›› ብለው፣ ይህ ማለት ግን ቡድኑ በተለይም በዚህ ወቅት በግልጽ  የሚታይና የሚዳሰስ ችግር ሲገጥመው አመራሩ፣ ነገሮችን ሁሉ በዝምታና በቸልተኝነት እንዲያልፍ አይጠበቅበትም ሲሉ የውሳኔውን ትክክለኛነት ያጠናክሩታል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የዋንጫ ባለቤት እንዲሆን ያስቻሉት አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በበኩላቸው፣ ከውሳኔው ጋር ተያይዞ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ፣ ይሁንና በክለቡ የቦርድ አባል አቶ ነዋይ በየነ አማካይነት ስልክ ተደውሎ ከማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን ጀምሮ በነበራቸው ኃላፊነት መቀጠል እንደማይችሉ የተነገራቸው ስለመሆኑ ብቻ ነው የሚናገሩት፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሁኑ ላይ የስድስት ሳምንታት ቀሪ መርሐ ግብር ቀርቶታል፡፡ ሊጉ የድሬዳዋ ቆይታውን አጠናቆ ወደ ሐዋሳ ያመራ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ በ47 ነጥብ ይመራል፡፡ በ44 ነጥብ የሚከተለው ደግሞ የመቻል እግር ኳስ ክለብ ሲሆን፣ ባህር ዳር ከተማ 40 ነጥብ ይዞ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከውጤት ጋር ተያይዞ የቡድኑን ዋና አሠልጣኝ ያገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በበኩሉ 39 ነጥብ ይዞ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...