Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየትግራይ ክለቦችን ለማጠናከር የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነው

የትግራይ ክለቦችን ለማጠናከር የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነው

ቀን:

  • በዝግጅቱ 700 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዷል

የትግራይ ክለቦች በሚቀጥለው የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለሱ መወሰኑን ተከትሎ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሊዘጋጅ መሆኑ ታወቀ፡፡ በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እስከ 700 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት ጥቅምት 2013 ዓ.ም. በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ነበር በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፉ የነበሩት ሦስቱ የትግራይ ክለቦች ማለትም መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓዲግራትና ስሑል ሽረ የእግር ኳስ ክለቦች ከውድድር ውጪ ሆነው የቆዩት፡፡

በክልሉ እግር ኳሱን ጨምሮ በርካታ ስፖርቶች ከሚከናወንባቸው ክልሎች የትግራይ ክልል አንዱ የነበረ ቢሆንም፣ ግጭቱን ተከትሎ አሁን ላይ ሁሉም ነገር በነበር ካልሆነ እንቅስቃሴው እምብዛም ነው፡፡ በትግራይ ከእግር ኳሱም በላይ በብስክሌት እጅግ ባለተሰጥኦ ወጣቶች የሚፈሩበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በዚሁ ስፖርት በኦሊምፒክ ደረጃ የአገር ውክልና የተመዘገበበት መሆኑ በዓለም በታላቅ ዓለም አቀፋዊ ውድድርነቱ የሚጠቀሰውን ቱር ዲፍራንስን ጨምሮ የሪዮ ኦሊምፒክና የቶኪዮ ኦሊምፒክ ምስክሮች ናቸው፡፡ በሪዮ ኦሌምፒክ ጽጋቡ ገብረ ሥላሴ፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ደግሞ ሰላም አምሃ ተካፋዮች ነበሩ፡፡

- Advertisement -

እነዚህ ሁሉ ስፖርቶች በከፍተኛ ደረጃ የሚዘወተርበት ትግራይ፣ በተለይም ግጭቱ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን በዝምታ መቆየቱ ለብዙዎች መነጋገሪያ መሆኑ አልቀረም፡፡ ይሁንና አሁን ላይ ችግሩ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ዕልባት ያገኘ ቢመስልም፣ ነገር ግን ነገሮች እየተጓተቱ መሆኑን ተከትሎ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴው እንደሚመለስ ሲጠበቅ በነበረው፣ በተለይም ታዳጊ ወጣቶች እንደየዝንባሌያቸው የሚያዘወትሯቸው እግር ኳስ፣ ብስክሌትና ሌሎችም ስፖርቶች መጀመራቸውን የሚናፍቁ ብዙዎች ናቸው፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦችን ተሳትፎ በተመለተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግጭቱ እንደተከሰተ፣ በተለይም በፕሪሚየር ሊጉ ሲሳተፉ የነበሩት ሦስቱ ክለቦች የተፈጠረው አለመግባባት በአንድና በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መፍትሔ የሚያገኝ ከሆነ፣ በነበሩበት አግባብ እንደሚቀጥሉ በወቅቱ ውሳኔ አሳልፎ የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከዓመታት በኋላ፣ ቀድሞ በነበሩበት ሊግ እንዲቀጥሉ አሳልፎት የነበረውን ውሳኔ እንደገና በማጤን አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው እንዲወዳደሩ በሚል ለሁለተኛ ጊዜ ውሳኔ እንዲወስን የተገደደበት አጋጣሚም ተፈጥሮ ነበር፡፡

የክልሉ ክለቦችና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ፣ ከሰሞኑ ሦስቱ ክለቦች በቀጣዩ የውድድር ዓመት ቀድሞ በነበሩበት ፕሪሚየር ሊግ ለመወዳደር የሚያስችልቸውን ቁመና መያዝ ይችሉ ዘንድ፣ በተለይም በፋይናንስ ረገድ ሊገጥማቸው የሚችለውን ክፍተት ሊቀርፍ የሚችል ትልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡ ፕሮግራሙም በዚህ ወር መጨረሻ በሸራተን አዲስ ይካሄዳል ብሎ ይጠበቃል፡፡

በመሆኑም በክለቦቹ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ቀደም ሲል የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉ እንደተጠበቀ ቢሆንም፣ አሁን ለደረሰበት ውሳኔ ምክንያቱ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንደሆነ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ  አቶ ባህሩ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ ሁሉም ነገር ቀድሞ በነበረበት እንዲቀጥል የሚያስገድድ መሆኑ ቢታወቅም፣ ይህንኑ ስምምነት ተከትሎ በቅርቡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለፌዴሬሽኑ በጻፈው ደብዳቤ፣ ቀደም ሲል ክለቦቹ አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው ይወዳደሩ የሚለውን ውሳኔ እንደገና ማጤን እንዳለበት መጠየቁን ዋና ጸሐፊው ያስታውሳሉ፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...