Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

እርመኛዋ አርበኛ ልክየለሽ በያን

ትኩስ ፅሁፎች

ወደ ማይጨው በመዝመት የመሬት ይገባኛልን ለማስረፅ የፈለገችው ዝነኛ አርበኛ ልክየለሽ በያን ናት። በስሜን ደግሞ ሸዋነሽ አብርሃ ትገኛለች። በመጨረሻዎቹ ሁለት ዓመታት የጣልያንን ወረራ ተቃውሞ በሙሉ ኃይሏ ተቀላቅላ የነበረችው ሸዋረገድ ገድሌም አለች።

ልክየለሽ በያን እንዲህ ብላ ተናግራለች ታሪኳን፡- «አባቴን ማሳፈር አልፈልግም። ንጉሠ ነገሥቱ ቤተ ክርስቲያን የሚያወድምና መሬታችንን የሚወስድ ጠላት መቶብናል እንዳሉ የአባቴን ጠበመንጃ ይዤ፣ የአራት ወር ሴት ልጄን በጀርባዬ አዝዬ የደጃዝማች መሸሻ ወንዴን የከምባታ ጦር ተቀላቀልኩ። የወንድ ልብስም ለበስኩ።»

ግንቦት 30 ቀን 1931 ዓ.ም. ልክየለሽ፣ ኃይለ ማርያም ማሞ ሊሞት ሲል ትደርስበታለች። ከሁለት ዓመታት በፊት ነበር የአርበኞች ቡድኑን የተቀላቀለችው።

«በጣም ፈርቼ እና ደንግጬ ነበር። ባንዲራውን ተቀብዬ ሄጄ ጦርነቱን እንድቀጥል አዘዘኝ። ባንዲራ ያዡ ሞቷል። ተክሌ (ባንዲራውን የመያዝ ኃላፊነት የነበረበት ሌላ ሰው) አልወስድም ስላለ እኔ ባንዲራውን በአንገቴ ዙሪያ ጠቀለልኩት። ልሄድ ስነሳ ሞቷል። ሞተሃል እኮ ብለው ምንም አላለኝ። ከዚያ ዙሪያዬን ሳየው ሰው ሁሉ ሸሽቷል። ወንዙን ስሻገር በሁሉም አቅጣጫ የጠላት ጦር ከቦኛል። ሳያዩኝ ቶሎ ብዬ ዛፍ ላይ ወጣሁ። እዛች ዛፍ ላይ ለአምስት ቀን ተቀመጥኩ። በጣም ርቦኛል። ምንም የሚቀመስ አልነበረኝም። የሜዳ መነጽር ስለያዝኩኝ አንድ ቀን ሁለት ሰዎች ጆንያ እና የሆነ ነገር ይዘው ሲመጡ አየሁ። አስቁሜ የያዙትን በላሁ። በአምስተኛው ቀን ጠላት ወደ አንኮበር ሄደ። ከዛ በኋላ ነው ከቡድኔ ጋር የተቀላቀልኩት።»

– ፀሐይ ብርሃነሥላሴ ‹‹ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት››

*****

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች