Monday, May 20, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

 • በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ?
 • ለምን?
 • መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል።
 • የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው?
 • ‹‹ፅዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና›› የሚል ሕዝባዊ ንቅናቄ ነው ያስጀመረው።
 • ለምን ጉዳይ? 
 • በአዲስ አበባ መፀዳጃ ቤት ለመገንባት።
 • ምን ለመገንባት? 
 • መፀዳጃ ቤት። ምነው፣ አልሰማሽም ነበር?
 • ፈጽሞ አልሰማሁም … ብቻ ይገርማል! 
 • ምኑ ነው የሚገርመው?
 • የእውነት ግን መንግሥት ሽንት ቤት ለመገንባት የገንዘብ ድጋፍ ጠየቀ ነው የምትለኝ?
 • ምነው ስነግርሽ?
 • መንግሥት አፍ አውጥቶ ሽንት ቤት ለመገንባት ድጋፍ ጠየቀ? ለማመን ይከብዳል! 
 • እንዲያውም ዓላማውንም በግልጽ ተናግሯል።
 • ዓለማው ምንድነው አለ?
 • ባህልን ለማዳበር ነው ብሏል።
 • የምን ባህል?
 • ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት።
 • ወይ ጉድ …! 
 • ምነው ይህን ያህል ተገረምሽ? 
 • ሽንት ቤት ለመገንባት ከነዋሪው የገንዘብ ድጋፍ የሚጠይቅ መንግሥት አይቼም፣ ሰምቼም አላውቅ። በዚያ ላይ ደግሞ …
 • በዚያ ላይ ምን?
 • በልቶ ማደር የከበደውን ነዋሪ ለሽንት ቤት አዋጣ ማለት መሳለቅ አይሆንም?
 • ነዋሪውን ብቻ መስሎሽ ነው?
 • እና?
 • ዳያስፖራውም ዶላር እንዲልክ የዶላር አካውንት ተከፍቷል።
 • እኔ ይኼን ለማመን ይከብደኛል?
 • ለምን? 
 • ሽንት ቤት ለመገንባት ዲያስፖራው ድረስ? 
 • ዳያስፖራውስ ቢሆን ለአገሩ አስተዋጽኦ ማድረግ የለበትም?
 • እኔ እንደዚያ ማለቴ አይደለም።
 • እና ምን እያልሽ ነው?
 • መንግሥት ሽንት ቤት ለመገንባት የሚያስችል ገንዘብ ከሌለው ለምን ፕሮጀክት ቀርፆ አይጠይቅም?
 • ምንድነው የሚጠይቀው?
 • ለምን ከዓለም ባንክ ሶፍት ብድር አይጠይቅም?
 • የመንግሥት ዓላማ ሶፍት ማቅረብ አይደለማ።
 • እኔም ለሶፍት ማለቴ አይደለም።
 • እና ምንድነው ያልሽው?
 • ለምን ቀላል ብድር አይጠይቅም ማለቴ ነው።
 • እንደዚያም ታስቦ ነበር።
 • እና …?
 • ለሽንት ቤት ግንበታ ዓለም ባንክን መጠየቅ ለገጽታ ግንባታ ጥሩ አይደለም በሚል ተትቶ ነው።
 • ሕዝቡንም ቢሆን ለሽንት ቤት አዋጣ ማለት ለገጽታ ጥሩ አይመስለኝም። 
 • ታዲያ መንግሥት ምን ማድረግ ነበረበት? ሌላ ምን አማራጭ አለው? 
 • ሌላ አማራጭ ከሌለው ደግሞ ይህንንም እንደ ኮንዶሚኒየሙ ከባንኮች ጋር ማስተሳሰር ነዋ።
 • አስተሳስሮስ?
 • የሽንት ቤት ማስጀመር ነዋ።
 • የሽንት ቤት ምን?
 • 40/60!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...

በስድስተኛው ዙር ጠቅላላና ድጋሚ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በገዥው ፓርቲ ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ ነው

በ2013 ዓ.ም. ስድስተኛው ምርጫ ባልተካሄደባቸው ክልሎች በጠቅላላና በድጋሚ ምርጫ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን የእጅ ስልካቸውን ተመለከቱና ደዋዩ አንድ ወዳጃቸው ባለሀብት መሆናቸውን ሲያውቁ አነሱት]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? እንዴት ነህ ወዳጄ? ሰሞኑን በተደጋጋሚ ብደውልም ስልኩ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው እያለ አስቸገረኝ። አዎ፣ ወጣ ብዬ ነበር። ከአገር ውጭ ነበሩ? አይ... እዚሁ ነው። ምነው በሰላም? በሰላም...