Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምየእስራኤል ጋዛ ጦርነት እንዲቆም የተጠራው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ

የእስራኤል ጋዛ ጦርነት እንዲቆም የተጠራው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ

ቀን:

‹‹ፍትሕ ለፍልስጤማውያን›› ያሉ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ፣ አሁን ላይ በተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ተስፋፍቷል፡፡ የተማሪዎቹ ተቃውሞም በአሜሪካ፣ በ22 ግዛቶች ተዳርሷል፡፡

የእስራኤል ጋዛ ጦርነት እንዲቆም የተጠራው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ዩኒቨርሲቲዎች ከእስራኤል ጋር ያላቸውን የፋይናንስ ግንኙነት እንዲያቋርጡ በአሜሪካ በ22
ግዛቶች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ጠይቀዋል
(ጌቲ ኢሜጅ

ተቃውሞው የተጠነሰሰበትን ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ፣ የአብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሟቸውን አቁመው ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ቢጠየቁም፣ ይህ ተፈጻሚ ሊሆን አልቻለም፡፡

ሊገባደድ ወር እንኳን ያልሞላው ትምህርት እንዲጠናቀቅና የተመራቂዎች ሥነ ሥርዓት እንዲከናወን ጥያቄ ቢቀርብም ተማሪዎች ምላሽ አልሰጡም፡፡ ይልቁንም በፍልስጤም ደጋፊዎችና በእስራኤል ደጋፊዎች፣ በተማሪዎችና በፀጥታ አካላት መካከል የተፈጠሩ ልዩነቶች ተማሪዎች እንዲታሰሩ፣ ከትምህርት እንዲታገዱ ምክንያት ሆኗል፡፡

- Advertisement -

ሲኤንኤን እንደሚለውም፣ በ16 ግዛቶች በሚገኙ ከ20 በሚልቁ ካምፓሶች ለተቃውሞ ከወጡ ተማሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል፡፡

የእስራኤል ጋዛ ጦርነት እንዲቆም የተጠራው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ውጭ እስራኤልን የሚደግፉ ድምፃቸውን አሰምተዋል
(አሶሽየትድ ፕሬስ)

የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለምን ተቃውሞ ወጡ?

በፍልስጤም ጋዛ ውስጥ እስራኤል የምታካሂደውን ጦርነት እንድታቆም በአይሁድ ማኅበረሰብ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮችና በተለያዩ ተቋማት ሲጠየቅ የነበረውን ‹‹የጦርነት ይብቃ፣ ተኩስ አቁም ስምምነት ይደረሳል›› ጥያቄ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቀላቅለዋል፡፡

በጥቅምት መጀመሪያ ሃማስ በእስራኤል ላይ የወሰደውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ውጥረት መስፈኑን ያስታወሰው ቢቢሲ፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ደግሞ ውጥረቱ ወደተቃውሞ መቀየሩን፣ የተቃውሞው ዓይነትም በ1980ዎቹ እንደተደረገው በዩኒቨርሲቲዎች የፀረ አፓርታይድ ንቅናቄንና የቬትናም ጦርነት ተቃውሞ ሰልፍን እንደሚያስታውስ ጠቁሟል፡፡

ሃማስ በእስራኤል 1,200 ሰዎችን የገደለበትና፣ በአፈጸፋው እስራኤል ከ34ሺሕ በላይ ፍልስጤማውያን ገድላ ጦርነቱን የቀጠለችበት አካሄድ ለተቃውሞው ምክንያት ነው፡፡

አገር አቀፍ በሚባል ደረጃ እየተካሄደ ያለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጭና የ24 ሰዓት የዜና ሽፋን ማግኘቱ ደግሞ፣ ተቃውሞው እንዲስፋፋ አድርጓል፡፡

ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ቁጭ በማለትና የረሃብ አድማ በማድረግ ሲገልጹ የነበረውን ተቃውሞ፣ አሁን ላይ ትናንሽ ድንኳኖችና መጠለያዎች በመሥራት ተቃውሞዋቸውን እያሳዩ ነው፡፡

ተማሪዎች ምን ጠየቁ?

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ጦርነት እንድታቆም ከመጠየቅ ባለፈም፣ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ከእስራኤል ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያላቸውን ገንዘብ ነክ ግንኙት እንዲያቋርጡ ጠይቀዋል፡፡ ይህ መገበያየትን ጨምሮ ማናቸውም ገንዘብ ነክ ግንኙነት እንዲቋረጥ የሚጠይቅ ነው፡፡

የተማሪ ወትዋቾች እንደሚሉት፣ ከእስራኤል ጋር የሚሠሩ ኩባንያዎች እስራኤል በጋዛ በምታካሂደው ጦርነት በተዘዋዋሪ እየተሳተፉ ነው፡፡ ከእዚህ ኩባንያዎች ጋር የሚሠሩና ኢንቨስት የሚያደርጉ ኮሌጆችም በተዘዋዋሪ ይሳተፋሉ፡፡ በመሆኑም የዩኒቨርሲቲዎች ከምርምር ላቦራቶሪ እስከ ስኮላርሺፕ ፈንድ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች፣ ከአማዞን፣ ከማይክሮሶትፍ፣ ከግለሰቦች የሚመጣ ፈንድ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች ከሌላ አካል ጋር በመጣመር በሚሠሩ ሥራዎች የሚኖር የገንዘብ ግንኙነት ባጠቃላይ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ጋር የሚደረግ የፋይናንስ ግንኙነት እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግም ተማሪዎች ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ከእስራኤል ጋር ያላቸውን የፋይናንስ ግንኙነት እንደሚያቋርጡ ተነግሯል፡፡

ጆርጅ ዋሽግንተን፣ ሃርቫርድ፣ ኤመርሰን፣ ኒውዮርክ፣ ካሊፎርኒያ፣ ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በአማሪካ ሰሜን ምሥራቅ፣ ምዕራብ ዳርቻ፣ ማዕከላዊ ምዕራብ፣ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ የሚገኙ የግልና የመንግሥት ዩኒቨርቲዎች ናቸው በሰልፉ የተሳተፉት፡፡ ባለፈው ሳምንት በአውስትራሊያ፣ በካናዳ፣ በፈረንሣይ፣ በጣሊያንና በእንግሊዝ በሚገኙ ካምፓሶች የሚገኙ ተማሪዎችም ፍልስጤምን ደግፈው ሰልፍ አድርገዋል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉ ዓላማ ተሳክቷል

ቢሲሲ እንዳሰፈረው፣ የፍልስጤም ደጋፊዎች ያሉባቸው ካምፓሶች ተቋማቸው ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ፣ ራስን የማግለል፣ የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲቋረጥና ማዕቀብ እንዲጣል እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ለዓመታት ቆይተዋል፡፡ ሆኖም አንዳንዶች ውስን በሆኑ ጉዳዮች ላይ የገንዘብ ግንኙነታቸውን ቢያቋርጡም፣ በአሜሪካ አንድም ዩኒቨርሲቲ ይህንን አጠቃሎ አልተገበረም፡፡

እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድን በመቃወም ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቀርቦ የነበረው ‹‹ከአፓርታይድ አስተዳደር ጋር ማንኛውም የገንዘብ ግንኙነት አለማድረግ››፣ የሚል ጥያቄ 150 ትምህርት ቤቶች ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ ቢያስችልም በእስራኤል ጋዛ ጦርነት ምክንያት ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ እስከ ትናንት ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ መልስ አላገኘም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...