Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ተረት ሰፈር

ትኩስ ፅሁፎች

ተረት ሰፈር ስንኖር ሴቶቹ እማሆይ ጣዲቄ የሚሏቸው ባልቴት ነበሩ፡፡ “ያጋፋሪ እንደሻው” ምንጭ እሳቸው ናቸው፡፡  በበኩላቸው ከተራው ሰው ለየት ያሉ ናቸው፣ እንደ ገጸ ባህሪያችን፡፡ ገና ስንነሳ፣ እማሆይ ቢሉዋቸውም መነኩሲት አይደሉም፣ ለማኝ ናቸው፡፡ ነብሳቸው እንደ አጋፋሪነታቸው ተጓዥ በመሆኗ፣ ለልመና ጧት (ለማኝ ሳያራ ሊሆን ይችላል) ኦቶቡስ ተሳፍረው እስከ መጨረሻ ፌርማታ ተጉዘው ይወርዳሉ፡፡

ቀኑን ሲለምኑ ውለው (ትዕዛዙ “በግንባርሽ ላብ ትበያለሽ” ስለሆነባቸው) በኦቶቡሳቸው ወደ ተረት ሰፈራችን ይመለሳሉ፡፡ ሴቶች በተለያየ አጋጣሚ ለቡና ይጠሩዋቸዋል (ባልተቤቴ ስትልክባቸው “ጣት የምታስቆረጥም” ቁርስ ታዘጋጃለች)

ጀበናም ሲወርድ እማሆይ ጣዲቄ የራሳቸውን ሲኒ አውጥተው (ከየት እንዳወጡት አላየሁም) እጃቸውን ሲዘረጉላት፣ ካዳሚዋ ረኮቦቱ ላይ ከመሰሎቹ ሲኒዎች ትደረድረዋለች…

…. አንድ ከሰዓት በኋላ፣ እማሆይ ጣዲቄ ከሚስቴ ጋር ከቀብር ተመልሰው፣ እጣኑ እየጤሰ ቡናው እየተጠጣ፣ ለረዥም ጊዜ ሳውቃት ሞት በጭራሽ የማያስፈራት ሚስቴ

“ውይ ሲያሳዝኑ መሞት እንደዚያ ሲፈሩ መሞታቸው!” ስትል በቁጭት

“ምን ለሳቸው ታዝኛለሽ አሉ እማሆይ “ቀኛዝማች ሳህለ ጆርጊስ አሉልሽ አይደለም?”

(ይኸውላችሁ እንግዲህ አንባብያን ሆይ! አጋፋሪን ፃፋቸው ሲለኝ ይመስላል፣ በዚያች ደቂቃ “ጆሮዬ ቆመ” – ባህላዊ ጥቅሶቼን እያስተዋላችሁልኝ አደራ)

“ቀኛዝማች ሳህለ ጆርጊስ?” በጉጉት እማሆይ ጣዲቄን ጠየቅኳቸው

“ይኸውላችሁ፣ ዛሬ እዚህ ሊሴ ፈረንሳይ ተማሪ ቤት ያለበት ቦታ፣ በዘበኑ ዙሪያውን የቀኛዝማች ሳህለ ጆርጊስ ቤተሰቦች ነበረ፡፡ እና እሳቸው ከዘመዶቻቸው ሁሉ የተለየ ሞትን የመፍራት አባዜ ተጠናውቷቸው ነበር

“የትም ሄደው ይመለሱ፣ ከበቅሎዋቸው ሳይወርዱ አሽከሮቹን

“ሰፈር ደህና ነው?” ይሉዋቸዋል…”

…እንግዲህ ወጣት ደራሲያን “ሞትና አጋፋሪ እንደሻው” እማሆይ ጣዲቄ እንደነገሩኝ ሆኖ (ያውም ቃል በቃል)

የመጀመሪያዋ አረፍተ ነገር ብቻ የኔ ነች (ለትረካው እንዲያመች) ከዚያ የሚቀጥሉት ምዕራፎች (“ቆሪጥና አጋፋሪ…”) እማሆይ የነገሩኝ እንደ እርሾ እየሆነ፣ እኔ እያቦካሁ እየጋገርኩ፣ ይህ መድበል እንደ አገልግል ተከድኖ ተለጉሞ ደርሷችኋል፣ ለሚቀጥለው የራሳችሁ የፈጠራ ጉዞ እንደ ማደፋፈሪያ እንደ “አይዞን!” ሊሆናችሁ ይችላል በሚል ተስፋ፣ በሄዳችሁበት ይቅናችሁ!

  • ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ‹‹አምስት ስድስት ሰባት›› (2004)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች