Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበሴቶች ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶችን በገንዘብና በአቅም የሚደግፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

በሴቶች ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶችን በገንዘብና በአቅም የሚደግፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ቀን:

በሴቶች ዙሪያ የሚሠሩና በሴቶች የሚመሩ፣ በተለይ በሴቶች ትምህርት ዙሪያ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችን የሚያከናውኑ የሴት ድርጅቶች በገንዘብና በአቅም ለመደገፍ ኢግናይት የተባለ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡

በኢንተርናሽናል ሪስኪዩ ኮሚቴ፣ በኧርጀንት አክሽን ፈንድ አፍሪካ እንዲሁም በፓርትነርሽፕ ፎር አፍሪካ ሶሻል ኤንድ ጋቨርነንስ ሪሰርች የሚደገፈው ኢግናይት ፕሮጀክት፣ በሴቶች ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግና በአቅም ማጎልበት ዙሪያ የሚሠራ ነው፡፡

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት፣ ሴቶችን ከመማር ወደ ኋላ የጎተቱ፣ በሴቶችና ልጃ ገረዶች ላይ ጫና የሚያደርሱ ማኅበራዊ ልማዶችን ለመከላከልና ለማስቀረት ያለመ ነው፡፡

- Advertisement -

በኢትዮጵያ፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በናይጄሪያ፣ በቡርኪናፋሶ፣ በካሜሩን፣ በዮርዳኖስና በሊባኖስ ውስጥ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው የኧርጀንት አክሽን ፈንድ አፍሪካ የለርኒንግ፣ ሞኒተሪንግና ኢቫሉዌሽን ኦፊሰር ሕይወት ተድላ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ድርጅቱ ፓን አፍሪካን ሆኖ ለሴቶች ሰብዓዊ መብት የሚታገልና የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥ የሚሠራ ነው፡፡

ሴቶችንና ሴቶች የሚመሯቸውን ድርጅቶች የሚደግፍ ሲሆን፣ በኢግናይት ፕሮጀክት በኩል መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ የማድረግና አቅም የማጎልበት ሥራ ያከናውናል፡፡

ኢትዮጵያ ከኢግናይት ፕሮጀክቱ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደምትሆን ያነሱት ሕይወት፣ በኢትዮጵያ ሥር የሰደደው የሴቶች ትምህርት የማግኘት ችግር ሊሠራበት የሚገባ በመሆኑ፣ ፕሮጀክቱ ይህንን እንደሚደግፍ ጠቁመዋል፡፡

የሴቶች ትምህርት የማግኘት ችግር ከተለያዩ ማኅበራዊ ጫናዎች እንደሚመነጭ በማስታወስም፣ በዚህና በሌሎች ሴቶችን ከማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ያገዷቸውን ችግሮች ለማቃለል በሴቶች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች በሚፈለገው መጠን መሥራት ባለመቻላቸው፣ ችግሩን ተባብሮ ለመቅረፍ እንዳዳገተ ገልጸዋል፡፡

በሴቶች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች በቀላሉ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት አለመቻላቸው፣ የተንዛዛ አሠራርና ድርጅቶቹ በቀጥታ ትምህርት ላይ እንዲሠሩ የሚያደርግ የገንዘብ ድጋፍ (ፈንድ) ለማግኘት መቸገርም የሴት ድርጅቶች በሚፈለገው ልክ እንዳይሠሩ ማድረጉን፣ በመሆኑም ድርጅቱ በኢትዮጵያ ከታች ጀምሮ በሴቶች ላይ የሚሠሩና በሴቶች የሚመሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እንደሚረዳ አክለዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማም በሴቶች የሚመሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ማብቃትና መደገፍ ሲሆን፣ አቅማቸው እንዲጎለብትም ድጋፍና ክትትል ይደረግላቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች ራሳቸው መብቃት ስላለባቸውም፣ ድርጅቶቹ ራሳቸውን በሚያበቁበት ሁኔታ እንደሚሠራ፣ ሲጠናከሩ ደግሞ የልጃገረዶችን  ትምህርት እንዲደግፉ የሚደረግበት አካሄድ እንደሚኖር ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ይፋ ከመሆኑ አስቀድሞ፣ ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው አገሮች 86 የፕሮጀክት ገንዘብ ጥያቄ ማመልከቻዎችን የተቀበለ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 20ዎቹ ከኢትዮጵያ ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ከሚሠራባቸው አገሮች ኢትዮጵያን ለምርምርና ጥናት መምረጡን፣ በሴቶች ዙሪያ ጥልቅ ጥናቶች ተሠርተው ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት እንዲሆኑ እንደሚደረግ፣ ጥናቱ የሚሠራውም ፖሊሲ የሚጽፉ፣ የሚያወጡና የሚተገብሩ ሰዎች ተሳትፈውበት እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

በሴት ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች ለልጃገረዶች ትምህርት ድምፅ እንዲሆኑ  አስተዋጽኦ ይኖረዋል የተባለው ፕሮጀክት፣ ፕሮጀክት ቀርፀው ለሚመጡ ብቻ ሳይሆን በሴት ላይ የሚሠሩ ሆነው የራሳቸውን አቅም መገንባት ለሚፈልጉም እስከ 20 ሺሕ ዶላር ይሰጣል፡፡

እንደ ሕይወት፣ ይህ በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ ለሚሠሩ ድርጅቶች ትልቅ ዕድል ነው፡፡ የሰው ኃይላቸውን ለማሠልጠን፣ ቢሮዋቸውን ለማሟላትና ለሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ገንዘብ የሚረዳ በመሆኑም፣ በሴቶች ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

አሁን ላይ ማመልከቻዎችን ተቀብለው እየገመገሙ ቢሆንም፣ ኧርጀንት አክሽን ፈንድ አፍሪካ ሁሌም ማመልከቻ እንደሚቀበል፣ በኢግናይት ፕሮጀክት ባይሆንም በሌሎች ፕሮጀክቶች ማመልከቻዎች እንደሚታዩና የሴቶችን መብት ለማስከበር የሚሠሩና በሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኧርጀንት አክሽን ፈንድ አፍሪካ፣ ድንገት በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ችግሮችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ የአድቮኬሲ/የውትወታ፣ የግንዛቤና ለችግሩ ምላሽ የሚሆን ሥራ ለሚሠራ ድርጅትም የድንገተኛ ጊዜ ፈንድ ይሰጣል፡፡

ያልታሰቡ ነገሮች ሲከሰቱ ችግሩን ለማረምም ሆነ ለመቃወም የሚፈልጉ ድርጅቶችም የድጋፍ ጥያቄ ቢጠይቁ የድርጅቱ በር ክፍት ነው ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...