Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየወጣቶች ተሰጥኦ የተገለጸበት ህዳሴ ግድብ

የወጣቶች ተሰጥኦ የተገለጸበት ህዳሴ ግድብ

ቀን:

ለኢትዮጵያውያን ልዩና ታሪካዊ ቀን ነበረች የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለልማት የተነሱበት ወቅትም ነበር፡፡ ቁጭት በተሞላበት እንጉርጉሮ  ሲዘፈንለትና  ሲዘመርለት የነበረው የዓባይ ወንዝ፣ ጉባ ተራራ ሥር ሊገደብ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሊገነባም የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት ቀን ነበር፡፡

ከዚያች ታሪካዊት ቀን ጀምሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ደሃውም ሀብታሙም ሁሉም እንደየአቅሙ በጉልበቱ፣ በሀብቱና በዕውቀቱ ርብርብ ሲያደርግ ቆይ~ል፡፡

የኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የውጭና የውስጥ ተግዳሮቶችን አስተናግዶ፣ ይጠናቀቃል ከተባለለት ጊዜና ከተመደበለት የገንዘብ መጠን ከእጥፍ በላይ ጨምሮ አሥራ ሦስት ዓመታትን በማስቆጠር የመጠናቀቂያ ምዕራፉ ላይ ደርgል፡፡

- Advertisement -

ግድቡ ብዙዎች ከገንዘብና ከጉልበት አልፈው እስከ ሞት ድረስ መስዋዕትነት ከፍለው  ለትውልድ የተከሉት ዘመን ተሻጋሪ  አሻራ ነው፡፡

ታዲያ ሁሉም በተቻለው አቅም የራሱን አሻራ ለማስቀመጥ በቦንድ ግዥ፣  በገንዘብ ልገሳና በመሳሰሉት ከመሳተፍ ባሻገር እንደየሙያቸው በግጥምና በዜማ፣ በሥነ ጽሑፍና በጭውውት ሲያሞግሱና ሲያበረታቱ ቆይተዋል፡፡

በየትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎች ቦንድ ገዝተዋል፣ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ያሉ ተማሪዎች ወጣት ገጣሚያንና ድምፃዊያን በሙያቸው ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ዛሬ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ምዕራፍ ቢደርስም፣  ወጣቶች የተለመደ ተሳትፏቸውን ከማድረግ አልተቆጠቡም፡፡

ዓባይ በታዳጊዎች አንደበት በሚልም የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በግጥሞች፣ በበልሃ ልበልሃ፣ በመነባንቦች፣ በክርክር፣ ጭውውትና በመሰል የኪነ ጥበብ ውድድሮች ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

የተሻለ ውጤትን ያስመዘገቡ የአሸናፊዎች አሸናፊ ተማሪዎች ደግሞ፣ የግድቡን 13ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ‹‹ዓባይ በታዳጊዎች አንደበት›› በሚል ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በተዘጋጀ መድረክ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

‹‹የህዳሴ ግድቡ ለወጣቶችና ለታዳጊዎች ይዞት የሚመጣው ፋይዳ ከሁሉም  የበለጠ ነው››፣ ሲልም በኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን የወጣቶች ተሳትፎና ንቅናቄ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወጣት አቤኔዘር ኤርሚያስ ተናግሯል፡፡  

 ወጣቶች በኪነ ጥበብ ታግዘው ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ባሻገር፣ በነበረው  የገንዘብ ማሰባሰብ ንቅናቄ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው  ከሚያገኙት ገቢ ቢያንስ አሥር በመቶ የሚሆን ለቦንድ ግዥ ተቆራጭ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የተናገረው ኤርሚያስ፣ ወጣቶች ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከዚህ የበለጠ ማወቅና መሥራት ይኖርባቸዋል ብሏል።

በግድቡ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠርም በጭውውትና በውይይት እንዲሁም በቀልድ እያዋዙ ስለዓባይ ችላ ያለን ሰው በመቀስቀስ ንቁ ተሳትፎን እንዳደረጉ ተናግሯል።

ከየካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. እስከ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ከዳያስፖራ፣ ከህዳሴው ግድብ ዋንጫና ከኅብረተሰቡ በተደረገ ተሳትፎ ከ19.2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የተናገሩት የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ከንግድ ባንክ፣ ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትና ከልማት ባንክ ጋር በጋራ በመሥራት ኅብረተሰቡ በተሳተፈባቸው 8100A፣ በቦንድ ግዥና በሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች ገንዘቡ መሰባሰቡን አክለዋል፡፡

በመድረኩ ለተማሪዎች ሽልማቱን የሰጡት አረጋዊ (ዶ/ር)፣ በተለይ የህዳሴው ግድብ ወደ መገባደጃው መድረሱን ተከትሎ የሕፃናትና የዳያስፖራዎች ድጋፍ መጨመሩን ገልጸዋል።

ድጋፉ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ ለአፍታም ተቋርጦ አያውቅም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ግድቡን ከደለል ሥጋት ነፃ ለማድረግ ከአንድ መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ሊገመት የሚችል የጉልበት ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ግድቡ ሲጠናቀቅ እራታቸውን በጨለማ የሚበሉ ሰዎች፣ በምሽት ለማጥናት የተቸገሩ ተማሪዎችና በአጠቃላይ በመብራት ችግር የተሰቃዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ፣ ፋብሪካዎችና ዘመናዊ ግብርና እንደሚስፋፋም አክለዋል፡፡

ዛሬ ላይ ግድቡ እየተገባደደ መሆኑን የተረዱትና በዲፕሎማሲ ትግል መሸነፋቸውን ያወቁት ግብፅና ሱዳን፣ ኢትዮጵያን በዓባይ የውኃ አጠቃቀም መጠን ላይ ወደ አስገዳጅና አሳሪ ውል ለማስገባት እየጣሩ እንደሆነ አክለዋል።

ኢትዮጵያ ከውኃ ሙሌት ሒደት በቀር በቀጣይ ትውልድ ዕጣ ፈንታ ላይ ምንም ዓይነት ውልም ሆነ ድርድር አታደርግም ሲሉ አረጋዊ (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የግድቡ ጠቅላላ አፈጻጸም 95.8 በመቶ መድረሱን የገለጹት አረጋዊ (ዶ/ር)፣ ሁሉም ሰው ግድቡ እስኪጠናቀቅ የተለመደውን ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ