Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትፈተና ያልተለየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ፈተና ያልተለየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቀን:

የሊጉ አስተዳዳሪ የአዲስ አበባ አስተዳደርን ይሁንታ እየጠበቀ ነው

በብዙ አገሮች ዘንድ ብዙም ያልተለመደ የውድድር መርሐ ግብር አካሄድን እንደሚከተል የሚነገርለት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ የ2016 የውድድር ዓመትን  በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጀምሮ በቀጣይ ያስተናገደው ድሬዳዋ ነው፡፡ ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት ያለውን መርሐ ግብር በሐዋሳ ከተማ ለማከናወን ጉዞውን ጀምሯል፡፡

ባለፈው 2015 የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊግ ባደገው ንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ በ45 ነጥብ መሪነት የድሬዳዋ ቆይታውን ያጠናቀቀው ሊጉ፣ በተለይም በአሁኑ ወቅት የክለብ አመራሮችንም ሆነ ደጋፊዎችን እንዲሁም የተጨዋች ኤጀንቶችን ትኩረት ያገኘው፣ በቀጣዩ የውድድር ዓመት የትኛው ተጨዋች ወደ የትኛው ክለብ በስንት ብር ወርኃዊ ክፍያና የፊርማ ገንዘብ የሚለው ሆኗል፡፡

- Advertisement -

በተለይ የክለብ አንዳንድ አመራሮች የዝውውር ገበያውን ካልሆነ፣ ማነው ዓመቱን በበላይነት የሚያጠናቅቀው፣ አልያም ወደ ታችኛው ሊግ የሚወርደው ክለብ ማንነት ብዙም እንደማያስጨንቃቸው ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡

ችግሩ እያሳሰበው እንደሆነ የሚናገረው ብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በበኩሉ፣ የክለብ አመራሮችም ሆኑ የተጨዋቾች ኤጀንቶች እንዲሁም አሠልጣኞችና ደጋፊዎች ከዚህ እግር ኳሱን እየጎዳ ካለ አካሄድ መቆጠብ ይችሉ ዘንድ፣ በ2017 የውድድር ዘመን ከተጨዋቾች ወርኃዊ ክፍያ ጨምሮ የክለቦችን የገንዘብ አወጣጥ ሥርዓት መቆጣጠር የሚያስችል አስገዳጅ መመርያ ለመተግበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሕገወጥ በሆነው አካሄድ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙ ባለድርሻዎች ሁሉ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባም ለክለቦች አሳውቋል፡፡

ሊጉ በአንድ የውድድር ዓመት እስከ አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የፋይናንስ እንቅስቃሴ እንዳለው ይነገራል፡፡ በጀቱና ውጤቱ ፍፁም የተራራቀ እንደሆነ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በሚመለከተው አካል መፍትሔ ካልተበጀለት፣ ከመንግሥትና ከከተማ አስተዳደር ምንም የበጀት ድጎማ የማይደረግላቸው ጥቂት ክለቦች ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ቀውስ እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ባይ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ምክትል አሠልጣኝና የቡድኑ አውቶቡስ የሆቴል ዕዳ ባለመክፈል እንግልትና እስራት እንደገጠማቸው ተሰምቷል፡፡

ክለቡ በድሬዳዋ ቆይታው ለሆቴል የተጠቀመበት አራት ሚሊዮን ብር መክፈል ባለመቻሉ ነው፡፡ በዚህም የክለቡ ምክትል አሠልጣኝና የክለቡ አውቶቡስ ወደ ሐዋሳ ከሚያደርጉት ጉዞ መስተጓጎላቸው ተገልጿል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የክለቡን አመራሮች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ለተጨዋች ዝውውር መቶ ሺዎችን ሲያፈሱ የነበሩ ክለቦች በዚህ ልክ ዕዳ ውስጥ መግባታቸው እንዴት ሊታመን ይችላል? የሚሉም አልጠፉም፡፡

የሊጉ አክሲዮን ማኅበር የመጨረሻዎቹን ሦስት ሳምንታት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማድረግ ከፀጥታና መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር እየተወያየ እንደሚገኝ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በአዳማና በድሬዳዋ ለ22 ሳምንታት በውድድር የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 45 ነጥብ ይዞ ይመራል፡፡ መቻል 41 ነጥብ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ 39 ነጥብ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ባህር ዳር ከተማና አዳማ ከተማ በእኩል 34 ነጥብ በጎል ተበላልጠው ከ4ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ፋሲል ከነማና ድሬዳዋ ከተማ በእኩል 33 ነጥብ በግብ ተበላልጠው 7ኛ እና 8ኛ ሲሆኑ፣ ሀድያ ሆሳዕና 31 ነጥብ፣ ሐዋሳ ከተማ 29 ነጥብ፣ ወላይታ ድቻ 28 ነጥብ፣ ሲዳማ ቡና 27 ነጥብ፣ ኢትዮጵያ መድን 22 ነጥብ እስከ 13ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ፣ ሻሸመኔ ከተማ በ13 ነጥብ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ በ8 ነጥብ በመያዝ ወራጅ ቀጣናው ላይ ተቀምጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...