Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትዘጠና ቀን በቀረው የፓሪስ ኦሊምፒክ ጉዳፍ ፀጋይ በሦስት ውድድሮች ትካፈል ይሆን?

ዘጠና ቀን በቀረው የፓሪስ ኦሊምፒክ ጉዳፍ ፀጋይ በሦስት ውድድሮች ትካፈል ይሆን?

ቀን:

  • ከኦሊምፒክ በፊት የዓለም የ10ሺ ሜትር ክብረ ወሰንን ለመስበር አልማለች

ፓሪስ ተናፋቂውን የኦሊምፒክ ጨዋታ ልታስተናግድ ከሦስት ወር ያነሰ ጊዜ ቀርቷታል፡፡ ጨዋታዎቹ የሚከናወኑት ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ከወዲሁ እየተዘጋጁ ሲሆን፣ ተወዳዳሪዎቻቸውን በመለየት ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ባለፈው ሰሞን በመካከለኛና በረዥም ርቀት እንዲሁም በዕርምጃ የሚወዳደሩ ከሁለቱ ጾታዎች የተወሰኑ ዕጩዎችን አሳውቋል፡፡ የማራቶንና የሌሎች ርቀቶችን ዕጩዎች በቅርብ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡

ዘጠና ቀን በቀረው የፓሪስ ኦሊምፒክ ጉዳፍ ፀጋይ በሦስት ውድድሮች ትካፈል ይሆን? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ለክብረ ወሰን የምትጠበቀው ጉዳፍ ፀጋይ

የኦሊምፒክ ትራክ መርሐ ግብሩ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ርቀት ውድድሮችን፣ እንዲሁም መሰናክሎችን እና የወንዶችና የሴቶች ዱላ ቅብብሎሽን ያካትታል። እነዚህ ውድድሮች በኦሊምፒክ ስታዲየም ውስጥ ባለ400 ሜትር ሞላላ ትራክ ላይ (ከሁለት ቀጥ ያሉና ሁለት ጠመዝማዛ መታጠፊያዎች የተሠሩ) የሚከናወኑ ናቸው። የማራቶንና የዕርምጃ ውድድሮችም በፓሪስ መንገዶች ላይ ይካሄዳሉ፡፡

- Advertisement -

ጉዳፍ ፀጋይ በፓሪስ ኦሊምፒክ በየትኞቹ ትወዳደራለች?

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ5,000ሜ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ የነበረችው ጉዳፍ፣ ከኦሊምፒኩ በኋላ በተከታታይ ዓመታት ባደረገቻቸው ከ1,500ሜ እስከ 10,000ሜ ርቀት ባደረገቻቸው ውድድሮች (የቤት ውስጥን ጨምሮ) ስኬታማ ሆናለች፡፡

‹ሲቲየስ ማግ› የተሰኘ ድረ ገጽ፣ ጉዳፍ በፓሪስ ኦሊምፒክ በየትኞቹ ርቀቶች ላይ ልትወዳደር እንደምትችል አማራጮችም እንዳሏት አትቷል። የሷ ርቀቶች የሆኑት 1,500ሜ፣ 5,000ሜ እና 10,000ሜ በመርሐ ግብሩ ተቀምጠዋል። የራስዋ ምርጫዎች ቢኖሯትም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቡድኑን እንዴት እንደሚመርጥ ይወስናል።

በዚያመን ዳይመንድ ሊግ ካሸነፈች በኋላ በፓሪስ ኦሊምፒክ ስለምትወዳደርባቸው ርቀቶች ተጠይቃ፣ ‹‹በየትኛው? እንደምወዳደር አላውቅም፣ ከአሠልጣኜ [ሕሉፍ ይኸደጎ] ጋር እመካከራለሁ፣ ምናልባት ሦስት ወይም ሁለት ሊሆን ይችላል፤›› በማለት ለሲቲየስ ተናግራለች፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሲፋን ሀሰን በሦስት ውድድሮች ተወዳድራ በ5,000ሜ እና በ10,000ሜ የወርቅ ሜዳሊያ፣ በ1,500ሜ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።

ጉዳፍ እንደ ሲፋን በሦስት ለመወዳደር ከመረጠች የኦሊምፒክ መርሐ ግብሩ ቀጥሎ የተመለከተውን ይመስላል፡፡

ሐምሌ 26- 5000ሜ ማጣሪያ በ6:10 ድኅረ ቀትር (ሞቃታማ)፣ ሐምሌ 29- 5,000ሜ ፍጻሜ በ9፡10 ድኅረ ቀትር (ድ.ቀ.)፣ ሐምሌ 30- 1,500ሜ በ10:05 (ሞቃታማ)፣ ነሐሴ 1- 1,500ሜ ማጣሪያ በ12፡35 ድ.ቀ.  (አስፈላጊ ከሆነ)፣ ነሐሴ 2 – 1,500ሜ ግማሽ ፍፃሜ በ7፡35 ድ.ቀ.፣ ነሐሴ 3 – 10,000ሜ ፍጻሜ በ8፡55 ድ.ቀ.፣ ነሐሴ 4 – 1,500ሜ ፍጻሜ በ8፡25 ድ.ቀ.፡፡ ‹‹የማይቻል አይደለም፣ ይቻላል፤›› ይላል ተንታኙ ክሪስ ቻቬዝ፡፡

10,000 የዓለም ክብረወሰንን ለመስበር ያለመችው ጉዳፍ

በፕሪፎንቴይን ክላሲክ (አሜሪካ ዩጂን) ግንቦት 17 በሚካሄደው ቀጣይ የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ የዓለም የ10,000ሜ ሻምፒዮኗ ጉዳፍ ፀጋይ፣ በለተሰንበት ግደይ ከሦስት ዓመት በፊት (ሰኔ 2013) በ29:01.03 የተያዘውን የዓለም የ10,000ሜ ክብረ ወሰንን ለመስበር አቅዳለች፡፡

ዓምና በ2015 በቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረችው ጉዳፍ፣ ዘንድሮ ሚያዝያ 12 ላይ በዚይመን ዳይመንድ ሊግ ከፌይዝ ኪፕዬጎን የ1,500ሜ የዓለም ክብረ ወሰን ጋር የሚቀራርብና የምንጊዜም ምርጥ ሦስተኛ ጊዜን 3፡50.30 በማስመዝገብ የውድድር ዘመኗን በድል ከፍታለች።

ጉዳፍ የዓምና (2023) የውድድር ዘመኗን በኛ መስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም. የዘጋችው በፕሪፎንቴይን ክላሲክ፣ በ5,000ሜ የዓለም ክብረ ወሰንን በ14፡00፡21 በመስበር እንደነበር ሁሉ፣ ዘንድሮስ በተመሳሳይ ቦታ ግንቦት 17 ቀን የ10,000ሜ ክብረ ወሰን ትሰብር ይሆን?

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...