Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናአስተዳደሩ በአምስት የልማት ኮሪደሮች 5135 ቤቶችን ማፍረሱን አስታወቀ

አስተዳደሩ በአምስት የልማት ኮሪደሮች 5135 ቤቶችን ማፍረሱን አስታወቀ

ቀን:

  • ለ307 የግል ይዞታዎች 2.8 ቢሊዮን ብር በጀት ይዣለሁ ብሏል
  • ለምን በማጣደፍ ማስነሳትና በዘመቻ መሥራት አስፈለገ የሚል ጥያቄም ቀርቧል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለይ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ከቀበና እስከ አያት አደባባይ በአጠቃላይ በአምስት የልማት ኮሪደሮች ላይ የነበሩ 5135 ቤቶችን አፍርሶ የልማት ሥራዎችን እያጣደፈ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳስታወቁት፣ በተለይ እንደ ፒያሳ ባሉ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ላይ የነበረውን የአኗኗር ሁኔታ፣ ዜጎች የተጎሳቆሉበት፣ ለመኖር የማያመች፣ ለእሳት አደጋና ለሌሎች አደጋዎች የተጋለጡበት ሁኔታ ነበር ብለዋል፡፡

አስተዳደሩ ከነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት፣ የኮሪደሩን ልማት ሁሉም መደገፍ እንደሚፈልግ የገለጸ ቢሆንም፣ ቀጣዩ ሁኔታው ያስፈራቸውና የተሻለ ነገር ይገኛል የሚል ተስፋ ያልነበራቸው፣ ለጊዜው የተቃወሙ ቢሆንም፣ በተደረገው ምክክር ንፁህ የመኖሪያ ቤት ማግኘታቸውንና ወደ ምቹ አካባቢ መሄዳቸውን ሲያውቁ ግን ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

በመሆኑም 5135 ቤቶች ለልማት የፈረሱ ሲሆን፣ ለ4000 ተነሺዎች ካሳ፣ ተለዋጭ ቤትና ምትክ ቦታ እንደተሰጣቸው በሪፖርታቸው አቅርበዋል፡፡

ከፈረሱት ቤቶች ውስጥ 307ቱ የግል ይዞታዎች መሆናቸውን የተናገሩት ከንቲባዋ፣ 2.8 ቢሊዮን ብር ለካሳ ክፍያ የተመደበ መሆኑንና 1.5 ቢሊዮን ብር ተከፍሎ ቀሪው በሒደት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በቀበሌና በመንግሥት ኪራይ ቤቶች ውስጥ የንግድ ሥራ ይሠሩ ለነበሩ 1117 ነጋዴዎችም ከ30 ሔክታር በላይ ምትክ መሬት መዘጋጀቱንና ነጋዴዎችም ከኪራይ ተላቀው የግል የንግድ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት አሠራር መፈጠሩን ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

‹‹በዚህ የኑሮ ውድነት በተጣደፈና በዘመቻ ሁኔታ የነዋሪዎችን መኖሪያና መሥሪያ ማፍረስ ለምን አስፈለገ?›› በማለት ለምክር ቤቱና ለከንቲባዋ ጥያቄ ያቀረቡት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩና የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አባል ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግ እንደነበረ በከንቲባዋ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳይ አስታውሰው፣ በቂ ጊዜ እንዳልተሰጠና ሁሉም ነገር የግድ በሦስት ወራት ውስጥ መሠራት እንደሌለበትም በመግለጽ ጥያቄና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በሰጡት ምላሽ፣ አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው እንዲነሳ የተደረገ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ በማንኛውም ጊዜ ተደርጎ የማያውቅ ለቀበሌና ለመንግሥት ቤቶች ተከራዮች ጭምር ተለዋጭ ቤትና ቦታ በመስጠት እንዲነሱ እንደተደረገ በመናገር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የሥራ ዕድልን በሚመለከት ለ1485 ቋሚና ለ13784 ጊዜያዊ ሠራተኞች በኮሪደር ልማት፣ በመልሶ ማልማትና በአረንጓዴ ውበት ዘርፎች ማሰማራት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...