Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየሴት ልጅ ግርዛት አሁንም ድረስ እየቀጠለ መሆኑ ተገለጸ

የሴት ልጅ ግርዛት አሁንም ድረስ እየቀጠለ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

የጤና ማኅበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባደረገው የመስክ ምልከታ የሴት ልጅ ግርዛት አሁንም ድረስ እየቀጠለ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2016 በጀት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ወቅት በአንድ ክልል የአንድ ሙሉ ቀበሌ ነዋሪዎች ግርዛት ትክክል መሆኑን ብቻ እንደሚረዱ ልጆቹን ያልስገረዘ ቤተሰብ ነውር ተግባር እንደፈጸመ የሚታይ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንድ አባል የተነሳው ጥያቄ መካከል፣ የሴት ልጅ ግርዛት አሁንም ድረስ ያለመሆኑን ሲሆን፣ በሲዳማ ክልል አዋቂዎችን ጨምሮ ግርዛት እንሚፈጸምባቸውና ለዚህ ተግባር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ምን እየሠራ እንደሆነ ተጠይቋል፡፡

- Advertisement -

የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ ይህንን ድርጊት ለመከላከልና የኅብረሰተቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች መሥራት ይገባዋል ብለዋል፡፡

በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ በተዋረድ የተቋቋሙ አዲስ ግብረ ኃይሎችን በክልል፣ በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ በማቋቋምና 818 ነባር ግብረ ኃይሎችን የማጠናከር ሥራ መሠራቱን ሪፖርቱን ያቀረቡት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ነፃ የሆኑ የቀበሌዎች ሽፋን ውስጥ 540 ቀበሌዎችን ነፃ በማድረግ ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ነፃ እንዲሆኑ መደረጉን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሕክምና፣ የፍትሕ፣ የሥነ ልቦናና ማኅበራዊ እንዲሁም ሌሎችድጋፎችን የሚሰጡ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተደራሽነት ሽፋንን ወደ 2,875 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ 25 ነባር የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከላትን ማጠናከር የተቻለ ሲሆን የተለያዩ ጥቃት የደረሰባቸው 5,150 ሴቶችን የተለያዩ አገልግሎቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሴቶች በጥቃት ተጎጂ ከመሆናቸው በፊት እንዲሁም ጥቃት ሲደርስባቸው የሚያሳውቁበት ነፃ የስልክ ጥሪ አገልግሎትን በማስፋፋት ለሴቶችና ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠርና በማዳበር 1,210 ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ሕፃናት የተሃድሶ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን ለማሳደግ 6 አዳዲስ የተሀድሶ ማዕከላትን በማቋቋም 17 ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ጥቃት ደርሶባቸው በተሃድሶ መስጫ አገልግሎት ማዕከላት ተጠቃሚ የሚሆኑ ሴቶች 1,839 ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል የሆነው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን መከላከልና ከስደት ተመላሽ ዜጎችን መደገፍን በተመለከተ በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው ከሆነ በሕገወጥ መንገድ ከአገር ሊወጡ ለሚሞክሩ በድንበር አካባቢ ለተያዙ ዜጎች በሙሉ የሥነ ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ በሞያሌ፣ ጋላፊ፣ መተማና ቶጎጫሌ ኬላዎች ተይዘው ለተመለሱ 887 ተመላሽ ዜጎች ተገቢው የሥነ ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ መደረጉ አንዱ ነው።

መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ አገሮች ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ሁሉንም በመቀበል የሥነ ልቦናና የማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙና ወደ ማኅበረሱ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ ታቅዶ በሱዳን የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ተመላሽ ዜጎች 47,746 የደረሱ ሲሆን ከሳዑዲ፣ ከየመንና ከኦማን እንደሚገኙ ሲሆን ሁሉም ተመላሾች የሥነ ልቦናና የማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ መደረጉን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ተመላሽ ዜጎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ የሌላቸው በመሆኑ በአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ እየተፈጠረባቸው ያለውን ችግር ለመቅረፍ እንዲቻል ለ8,830 ተመላሾች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 512 የዲጂታል መታወቂያ እንዲያገኙና ልዩ የሚሆኑ ተመላሾች ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ የኢኮኖሚና የመጠለያ አገልግሎት እንዲያገኙ ድጋፍ መደረጉ ተገልቷል፡፡

የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ችግር ጎልቶ በሚታይባቸው ክልሎች (አማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያና ኦሮሚያ) ውስጥ ለሚገኙ ቀበሌዎች መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት፣ በሰዎች መነገድና ሰውን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሦስቱ ክልሎች ከሚገኙ 13,019 ቀበሌዎች ውስጥ በ2,248 ቀበሌዎች ላይ የማኅበረሰብ ውይይት መደረጉን እንዲሁም ግንዛቤ መፍጠርና ማዳበር መቻሉ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...