Monday, May 20, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን የእጅ ስልካቸውን ተመለከቱና ደዋዩ አንድ ወዳጃቸው ባለሀብት መሆናቸውን ሲያውቁ አነሱት]

 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት ነህ ወዳጄ?
 • ሰሞኑን በተደጋጋሚ ብደውልም ስልኩ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው እያለ አስቸገረኝ።
 • አዎ፣ ወጣ ብዬ ነበር።
 • ከአገር ውጭ ነበሩ?
 • አይ… እዚሁ ነው።
 • ምነው በሰላም?
 • በሰላም ነው፣ የካቢኔ አባላት አንድ ላይ ሆነን የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እያደረግን ነበር።
 • አዎ… እርስዎም እዚያ ነበሩ እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • የት ማለትህ ነው?
 • ፍለጋ መሰለኝ፣ ብቻ በቴሌቪዥን ተመልክቼ ነበር።
 • ምን ፍለጋ?
 • ያው አንድ በጫካ የተከበበ ወንዝ ነዋ የሚሆነው።
 • ለምን? ምን ያደርግልናል?
 • ለማስፋፋት አስባችሁ መሰለኝ።
 • ምኑን?
 • ፕሮጀክቱን።
 • የትኛውን ፕሮጀክት?
 • የገበታውን ነዋ፡፡
 • የምን ገበታ ነው የምትለው?
 • አንዴ ለአገር አንዴ ለትውልድ የምትሉትን ገበታ ማለቴ ነው።
 • እህ… ገባኝ ገባኝ፣ የጉብኝቱ ዋና ዓላማው ለዚያ ባይሆንም አንድ ቦታ ግን አግኝተናል።
 • የፈራሁት ሊመጣ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምንድነው የምትፈራው?
 • አዋጡ የምትሉትን ነዋ ክቡር ሚኒስትር።
 • ለምንድን ነው የምትፈራው? ለአገር የሚደረግ አስተዋጽኦ አይደል እንዴ?
 • ቢሆንም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት?
 • ምክንያቱም እኛ እናዋጣለን እንጂ ከገበታው ተቋድሰን አናውቅም፡፡
 • አልገባኝም?
 • እኛ እናዋጠላን፣ ከገበታው የሚበሉት ግን ሌሎች ናቸዋ።
 • እንዴት?
 • እኔ ለገበታ አዋጣ በተባልኩ ቁጥር አዋጣለሁ።
 • እሺ?
 • የጀመርኩትን ፕሮጀክት ለማስፋፋት ላቀረብኩት የመሬት ጥያቄ ግን መልስ የሚሰጠኝ አላገኘሁም፣ ከእኔ በኋላ ጥያቄ ያቀረቡ ሌሎች ባለሀብቶች ግን ያለ ችግር ያገኛሉ።
 • አንተስ ለገበታ አዋጥቻለሁ ብለህ ብቻ መሬት ትጠይቃለህ እንዴ?
 • ሌላ ምን ማድረግ ነበረብኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ቢያንስ ለአንድ ሚኒስትር ሌላ ተጨማሪ ነገር ማድረግ ነበረብህ።
 • ምን ክቡር ሚኒስትር?
 • ሚኒስትሩ የሚያስገነባውን ሕንፃ ማገዝ ሊሆን ይችላል ወይም ሌላ ነገር።
 • ሌላ ነገር ምን?
 • እሱ እንደምትመርጠው ሚኒስትር ይለያያል።
 • ስለዚህ አለብኝ ማለት ነዋ?
 • ምን?
 • ሌላ ገበታ።
 • የምን ገበታ?
 • ገበታ ለሚኒስትር!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

 • አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላናግርዎት የፈለግኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት?
 • እኔማ ምን ይገጥመኛል እርስዎን ልጠይቅዎት እንጂ?
 • ምን?
 • እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡
 • ይንገሩኝ ምንድነው ያሳሰበዎት?
 • ሌት ተቀን የሚሠራው ነጋዴ እየከሰረ ነው።
 • መቼም የውጭ ኃይሎች የፈጠሩብንን ችግር ያውቁታል።
 • ከእሱ ጋር አይገናኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት?
 • ሌት ተቀን የሚሠራ ታታሪ ነጋዴ ችግር እሱ አይደለም።
 • ምንድነው?
 • ታታሪ ነጋዴ እየመነመነ ሳለ በተቃራኒው ግን ሌላ…
 • በተቃራኒው ምን?
 • መሽቶ ሲነጋ ሀብት አፍርተው የሚታዩ ሰዎች እንደ አሸን እየፈሉ ነው።
 • ምን ማለትዎ ነው?
 • ጠንክሮ መሥራት ሀብት የሚፈጠርበት መንገድ መሆኑ ቀርቶ ሌላ ዓውድ ተፈጥሯል እያልኩ ነው።
 • የምን ዓውድ?
 • ሲነጋ ሀብታም መሆን የሚቻልበት ዓውድ።
 • አልገባኝም?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው?
 • ሁሉን ነገር አስረዳ እያሉኝ እኮ ነው።
 • እውነት አልገባኝም? እንዴት ያለ ዓውድ ነው በብርሃን ፍጥነት ሀብት የሚያስገኘው?
 • አልገባኝም ካሉማ እነግርዎታለሁ።
 • ይንገሩኝ፡፡
 • ሲነጋ ሀብት የሚፈጠርበት ሥልት አንድና አንድ ነው።
 • ምንድነው?
 • ከከፍተኛ ባለሥልጣን ጋር ግንኙነት የመፍጠር ሥልት ነው፣ ወንድም ወይም ዘመድ አዝማድ የመሆን ሥልት፡፡
 • እሱን ነው እንዴ? ይህንንማ እኛም ገምግመናል።
 • ምን ብላችሁ ገመገማችሁት?
 • በዝተዋል ብለን ገምግመናል።
 • እነማን ናቸው የበዙት?
 • አካም አካም የሚሉ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...

በስድስተኛው ዙር ጠቅላላና ድጋሚ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በገዥው ፓርቲ ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ ነው

በ2013 ዓ.ም. ስድስተኛው ምርጫ ባልተካሄደባቸው ክልሎች በጠቅላላና በድጋሚ ምርጫ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ? ለምን? መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል። የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው? ‹‹ፅዱ...