Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየመጀመሪያዎቹ ዕጩ የኦሊምፒክ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ

የመጀመሪያዎቹ ዕጩ የኦሊምፒክ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ

ቀን:

  • ተቋሙ ጠንካራ የሥነ ምግባር መመርያም ሥራ ላይ አውላለሁ ብሏል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ከማራቶን ውጪ የመጀመሪያዎቹን ዕጩ ብሔራዊ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡ ብሔራዊ አትሌቶቹ ከማክሰኞ ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በሆቴል ተሰባስበው ዝግጅት እንደሚጀምሩ ቀደም ሲል ቢነገርም፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ‹‹ቀኑና የት ሆቴል› የሚለው  ውሳኔ አለማግኘቱ ተሰምቷል፡፡ ለውሳኔው መዘግየት በምርጫው የተካተቱ አትሌቶች ቁጥር መብዛት አንዱ ምክንያት እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡  

ከዚህ ጎን ለጎን ፌዴሬሽኑ የአትሌቶችን ዝርዝርና የሆቴል ምርጫ ከማድረጉ በፊት ከዝግጅትና መሰል ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ የዲሲፕሊን ጥሰቶች እንዳይደገሙ፣ በጥናት የተደገፈ የሥነ ምግባር መመርያ አውጥቶ ይፋ አድርጓል፡፡ መመርያው ቀደም ሲል በነበሩ የኦሊምፒክና መሰል ዝግጅቶች ላይ በተለይም አንዳንድ ብሔራዊ አትሌቶች ‹‹ሆቴል አንገባም በግል አሠልጣኞቻችን ካልሆነ አንሠለጥንም፤››  በማለት ሲያስቸግሩ የነበሩ በፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅት ላይ ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ጭምር የሚደነግግ አንቀጽ የያዘ መሆኑ ታውቋል፡፡

ብሔራዊ ተቋሙ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ዝርዝር መሠረት በ10,000 ሜትር ወንዶች፣ ለፓሪሱ 2024 ኦሊምፒክ መሳተፍ የሚያስችላቸውን ሰዓት (ሚኒማ) ካሟሉ አትሌቶች መካከል በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋና ዮሚፍ ቀጀልቻ ይገኙበታል፡፡ መግቢያ ሰዓት ያላሟሉ፣ ተብለው የተዘረዘሩት ይስማው ደሱ፣ ታደሰ ወርቁ፣ ቤኪ ድሪባና በረከት ዘለቀ ሆነዋል፡፡

- Advertisement -

በአምስት ሺሕ ሜትር ወንዶች የመግቢያ ሰዓት ካሟሉት ሐጎስ ገብረ ሕይወትና ኃይሌ በቀለ ሲጠቀሱ፣ የመግቢያ ሰዓት የሚቀራቸው ደግሞ ኩማ ግርማ፣ ገመቹ ዳዲ፣ አሊ አብዱልመና፣ አዲሱ ይሁኔ እና ዳዊት ወልዴ ሆነዋል፡፡

በ10,000 ሜትር ሴቶች ሁሉም የመግቢያ ሰዓት (ሚኒማ) ያሟሉ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት ጉዳፍ ፀጋይ፣ ጽጌ ገብረ ሰላማ፣ ሚዛን ዓለም፣ ግርማዊት ገብረ እግዚአብሔር፣ ቦሰና ሙላቱ፣ ያለምዘርፍ የኋላውና ሰምበሬ ተፈሪ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ በአምስት ሺሕ ሜትር ሴቶችም ሁሉም ለኦሊምፒክ መግቢያ ሰዓት ያሟሉ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት ለተሰንበት ግደይ፣ መዲና ኤልሳ፣ እጅጋየሁ ታዬ፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ለምለም ኃይሉ፣ አዊ ዳኛቸው፣ መልክናት ውዱና ሰናይት ጌታቸው መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በ3,000 ሜትር መሰናክል ወንዶች የመግቢያ ሰዓት ያሟሉ ለሜቻ ግርማ፣ አብርሃም ስሜና ጌትነት ዋለ ሲሆኑ፣ በቀጣይ ሰዓት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ደግሞ ሳሙኤል ድጉማና ኃይለ ማርያም አማረ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ ሴቶች የመግቢያ ሰዓት  ያሟሉ ሴምቦ ዓለማየሁና ሎሚ ሙላት ሲሆኑ፣ ሰዓት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ደግሞ ፍሬሕይወት ገሠሠ፣ ዓይናለም ደስታና እመቤት ከበደ ሆነዋል፡፡

በ1,500 ሜትር ሴቶች፣ የኦሊምፒክ መግቢያ ሰዓት ያሟሉ ድርቤ ወልተጂ፣ ሒሩት መሸሻ፣ ብርቄ ኃየሎምና ሳሮን በርሔ ሲሆኑ፣ የመግቢያ ሰዓት የሚቀራቸው ሀዊ አብርሃና አይናዲስ መብራቱ ሆነዋል፡፡ በወንዶች ምድብ ሁሉም የኦሊምፒክ መግቢያ ሰዓት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ናቸው፡፡ በምርጫ የተካተቱ ሳሙኤል ተፈራ፣ ቢኒያም መሐሪ፣ ታደሰ ለሚ፣ መለሰ በረከትና ወገኔ አዲስ ናቸው፡፡

በ800 ሜትር ሴቶች የመግቢያ ሰዓት (ሚኒማ) ያሟሉ ታዬ ድጉማ፣ ሀብታም ዓለምና ወርቅነሽ መለሰ ሲሆኑ፣ የመግቢያ ሰዓት የሚቀራቸው ደግሞ ትዕግሥት ግርማ፣ አዳም ነርኮና ነፃነት ደስታ ሆነዋል፡፡ በወንዶች ሁሉም የመግቢያ ሰዓት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሆኖ በምርጫ የተካተቱ ኤርምያስ ግርማ፣ ዮሐንስ ተፈራ፣ ሳሙኤል ቦቼ፣ ኤፍሬም መኮንንና ባጫ ሞርካ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...