Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ሰዎች ሰው መሆንን አልተማሩም››

ትኩስ ፅሁፎች

ጠያቂ፦ ‹‹ኧረ ለመኾኑ ሰዎች በመተማመንና በመተሳሰብ ፈንታ የተጠራጣሪነትንና ራስ የመውደድ ፍልስፍናን እየተማሩና እየተለያዩ የሚሄዱበት ምክንያት ምን ይመስልሃል?››

መላሽ፦ ‹‹የትምህርት ጉድለት ነው።››

ጠያቂ፦ ‹‹ከ ‹Kindergarten› ጀምሮ እስከ ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ድረስ በደረጃ የተከፋፈሉ ትምህርት ቤቶች በብዛት በተቋቋሙበት ጊዜ ችግሩ የትምህርት ችግር ነው ማለት እንዴት ይቻላል?››

መላሽ፦ ‹‹አዎ፣ በዛሬው ጊዜ የትምህርት ቤቶች ቁጥር እያደገ መሄዱ ጥርጥር የለውም። ሰዎች ‹ፓይሎት› ሆነው በሰማዩ ላይ ፈጣን ጄት አኤሮፕላን እንዲያበሩ፣ መሐንዲስ ሆነው ትልቅ ድልድይ እንዲሠሩ፣ ‹ማቲማቲሻን› ሆነው የቁጥር ፕሮብሌምን እንዲፈቱ፣ ‹አስትርኖመር› ሆነው የሰማይ ከዋክብትን አቀማመጥና እንቅስቃሴያቸውን እንዲመለከቱ … ለማስተማር ተችሏል። ግን አንድ መሠረታዊ የሆነ የትምህርት ጉድለት እንዳለ በግልጥ ይታያል።››

ጠያቂ፦ ‹‹ምንድን ነው?››

መላሽ፦ ‹‹ሰዎች ሰው መሆንን አልተማሩም።››

– ብርሃኑ ድንቄ  ‹‹አልቦ ዘመድ››

****

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች