Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየከተማ አስተዳደሩን የመንግሥት ተቋማት የሥራ ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት መቆሙ ተሰማ

የከተማ አስተዳደሩን የመንግሥት ተቋማት የሥራ ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት መቆሙ ተሰማ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሰዓት ከስምንት ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት መቆሙን፣ የከተማው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ጥናቱ የተጀመረው በከተማ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች የግል ገቢ እንዲኖራቸው፣ እንዲሁም የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ታስቦ መሆኑን ቢሮው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የከተማው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከዚህ በፊት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት ሙሉ ለሙሉ ቆሟል፡፡

- Advertisement -

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የሥራ ሰዓት ለማራዘም መነሻ ጥናት ተደርጎ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ አክለው ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው በጉዳዩ ላይ  ተጨማሪ ማብራሪያ እንደማይሰጡ ገልጸው፣ ወደፊት የታሰበው አሠራር ተግባራዊ ይደረጋል አይደረግም የሚለውን እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡

ጥናቱ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ መሥሪያ ቤቶችን የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 አስቀድሞ ለማስጀመርና ከ11፡30 በኋላ እስከ ምሽት ለማስቀጠል ታቅዶ ነበር፡፡

ዕቅዱ ይፋ የተደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የከተማዋ መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ መሆኑን፣ ቢሮው ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት  መግለጹ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...