Thursday, April 18, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

 • እኔ እምልህ …ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ?
 • ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው?
 • ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!?
 • አልገባኝም?
 • አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት?
 • አዎ።
 • ኤል ሲ ማለት እሱ ነዋ!
 • እ… እሱን ነው እንዴ?
 • አዎ።
 • አዎ። እሱማ ተከልክሏል፣ ግን ሙሉ በሙሉ አይደለም።
 • ሙሉ በሙሉ አይደለም ማለት?
 • በመንግሥት የተፈቀዱ ምርቶችን ለሚያስመጡ አልተከለከለም።
 • የቅንጦት ምርቶችን ለሚያስገቡት ግን ተከልክሏል አይደል?
 • አዎ፣ ምክንያቱም…
 • እ… ምንድነው ምክንያቱ?
 • አነስተኛ የዶላር ክምችታችንን ቼኮሌትና ሂውማን ሄር በማስገባት እንዲባክን መፍቀድ ትክክል አይደለም ብለን ስላመንን ነው።
 • ግን ለመኪና አስመጪዎችም ተከልክሏል ሲባል ሰምቻለሁ። ትክክል ነው?
 • አዎ። መኪና ለእኛ የቅንጦት ዕቃ ነው።
 • መኪና!?
 • አዎ!
 • ሰፊ የትራንስፖርት ችግር ባለበት አገር መኪና እንዴት የቅንጦት ዕቃ ይሆናል?
 • የትራንስፖርት ችግሩ መፍትሔ አለን።
 • የምን መፍትሔ?
 • ባለ ራዕይው መንግሥታችን የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት ያስቀመጠው ነገር አለ።
 • ምንድነው ያስቀመጠው?
 • አቅጣጫ!
 • የምን አቅጣጫ?
 • አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን የማስፋፋት።
 • መኪና እንዳይገባ ሲከለከል የትራንስፖርት አማራጭ ይጠባል እንጂ እንዴት ብሎ ይስፋፋል?
 • እኛ ተሽከርካሪ ሳናስገባ የትራንስፖርት አማራጮችን ማስፋፋት እንደምንችል ተረድተን አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል።
 • እስኪ አንደኛውን አማራጭ ንገረኝ?
 • ኧረ ሁሉንም እነግርሻሉ። ለምሳሌ አንደኛው አማራጭ…
 • እ….?
 • ማኅበረሰቡ በእግሩ እንዲጓዝ ማድረግ ነው።
 • በእግሩ ነው ያልከው?
 • አዎ።
 • ሌላኛው አማራጭስ?
 • በእንስሳት የሚሳቡ ጋሪዎችን መጠቀም ነው።
 • ይኼም አማራጭ ነው?
 • ጋሪዎችን በማዘመን ለትራንስፖርት መጠቀም እንደሚቻል አታውቂም?
 • ተወው እሱንና ሌላ አማራጭ ካለ ንገረኝ።
 • ሌላኛው በውኃ ሀብቶቻችን ላይ የጀልባ ትራንስፖርት አማራጭን ማስፋፋት ነው።
 • ይኼ ለአዲስ አበባ ከተማ አይሆንም።
 • ለምን አይሆንም?
 • ለጀልባ የሚሆን የውኃ ሀብት በአዲስ አበባ የለማ፡፡
 • ከእንጦጦ አባ ሳሙኤል ድረስ የተጀመረው ምንድነው?
 • ምን ተጀምሯል?
 • የወንዝ ዳር ልማት ነዋ?
 • እህ… ስለዚህ አዲስ አበባ የጀልባ ትራንስፖርት አማራጭ ታገኛለች ማለት ነው?
 • እንዴታ!
 • ሌላስ?
 • ለጊዜው የጠቀስኳቸው የትራንስፖርት አማራጮች ተግባራዊ እንዲሆኑ ነው የተወሰነው።
 • ግን አንድ ሌላ የትራንስፖርት አማራጭ መጨመር ትችሉ ነበር።
 • ምን?
 • ዋና!
 • እየቀለድሽ ነው?
 • ኧረ በፍጹም። ይልቅ ልጠይቅህ …
 • ምን?
 • ተሽከርካሪ ማስገባት ከተከለከለ እንዴት ነው አንዳንድ ሰዎች አዲስ መኪና የሚያስገቡት።
 • ማንም ማስገባት አይችልም።
 • ጎረቤታችን ያለው ባለሀብት ግን አሁንም እያስገባ ነው።
 • የትኛው ባለሀብት።
 • ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በድንገት ሀብታም የሆነው ስውዬ ነዋ?
 • አላወቀውም። ግን ምን መሰለሽ…?
 • እ…?
 • መኪና የሚገጣጥሙ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ግን አልተከለከሉም። እንዲያውም በዝቅተኛ ቀረጥ እንዲያስገቡ ይበረታታሉ።
 • ጎረቤታችን ያለው ባለሀብትም ይህንን ፈቃድ ተጠቅሞ ነዋ መኪና የሚያስገባው።
 • እንዴት?
 • መኪና መገጣጠሚያ እንዳለው ሰምቻለሁ።
 • እንደዚያ ከሆነ ይችላል።
 • ግን ምን ዓይነት መኪና እንደሚያስገባ ታውቃለህ?
 • ምን ዓይነት ነው?
 • ጎማው ብቻ ያልተገጠመለት መኪና።
 • እዚያው ነው የሚወድቀው።
 • ማለት?
 • የሚገጣጠም የመኪና ዓይነት ወስጥ ይወድቃል ማለቴ ነው።
 • እና ይኼንን ሰውዬም መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ አቋቁሟል ነው የምትሉት?
 • ታዲያ ምን አቋቋመ ልንለው እንችላለን?
 • እንትን ነዋ፡፡
 • ምን?
 • ጎሚስታ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተሉ አንዳንዴም በመገረም እየሳቁ አገኟቸው]

አንዴ? ምን አገኘሽ? ምን አገኘሽ ማለት? ለብቻሽ የሚያስቅሽ ማለቴ ነው? እ... ምን ላድርግ ብለህ ነው? ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው። እንዴት? ምንድነው ነገሩ? በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን እያዳመጥኩ ነዋ? አለቃ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር...