Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናብልፅግና ፓርቲና ሕወሓት በመቀሌ ተገናኝተው መከሩ

ብልፅግና ፓርቲና ሕወሓት በመቀሌ ተገናኝተው መከሩ

ቀን:

በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ የፓርቲው ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ትናንት መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ መቀሌ በመጓዝ ከሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር መወያየቱ ታወቀ።

ሕወሓት ባወጣው አጭር መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የብልፅግና አመራሮች ወደ መቀሌ የተጓዙት ለሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የሆኑ መሠረታዊ ልዩነቶች፣ በፖለቲካዊ ውይይት እንዲፈቱ በፕሪቶሪያው ሰምምነት ላይ በተቀመጠው መሠረት ውይይቶችን ለማስጀመር ነው።

በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የፖለቲካ ውይይቱ ቀደም ብሎ መጀመር እንደነበረበት የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በመቀሌ በተገናኙበት መተማመናቸውን በሕወሓት በኩል የወጣው አጭር መግለጫ ያመለክታል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህ ክፍተት ላይ በመግበባትም መደበኛ ውይይቶችን በፍጥነት ለመጀመር እንደተስማሙ ሕወሓት በመግለጫው አስታውቋል።

ወደ መቀሌ የተጓዘውን የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን የመሩት የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ናቸው። በዚህ ልዑክ ውስጥ ከተካተቱት የብለፅግና ከፍተኛ አመራሮች መካከል፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል የቀድሞ የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ሰማ ጥሩነህ ይገኙበታል።

ሕወሓትን በመወከል በውይይቱ ላይ የተገኙት የፓርቲው ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል፣ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር፣ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) እና አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ገዥው ፓርቲና ሕወሓት በመካከላቸው ያሉ ልዩነቶችን በፖለቲካዊ ውይይት እንዲፈቱ ያስቀመጠ ቢሆንም፣ የልዩነት ጉዳዮችን አያመላክትም። ይሁን እንጂ፣ በሁለቱ መካከል ሰፋፊ ልዩነቶች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለመዳኘትና ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ተግባራዊ መሆን አለበት ተብሎ በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የተቀመጠው የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ጉዳይ አንዱ ነው። ሕወሓት በፌዴራል መንግሥት መሪነት የሚቀረፀው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ተጠያቂነትንና ፍትሕን፣ በተለይም በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸሙ ወንጀሎችን በመዳኘት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አያስችልም የሚል ቅሬታ አለው።

በተጨማሪም፣ የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል የተነሳው የአስተዳደር ወሰን ይገባኛል ውዝግብ፣ በሕዝበ ውሳኔ እንዲፈታ በፌዴራል መንግሥት በኩል የቀረበውን የመፍትሔ አማራጭ ሕወሓት ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደረገው በመሆኑ፣ ሁለቱን ፓርቲዎች የሚያገናኝ ሌላኛው ፖለቲካዊ አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...