Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅሰሞንኛ

ሰሞንኛ

ቀን:

በእኔና በእናንተ መሀል ይቅርና ፒያሳ አካባቢ ቤት ሲፈርስ የሆነ ግርግር ጠብቄ ነበር፡፡ ወፍ የለም! ወፍ ብቻ ሳይሆን ወንጭፍም የለም! እኔ ቤት የለኝም እንጂ ቤት ቢኖረኝና እናፍርስ ብለው ቢመጡብኝ ጉድ ይፈላ ነበር፡፡ ከዶዘሩ ፊት ለፊት እንደ አብርሽ ዘጌት እግሮቼን አንፈራጥጨ ቆሜ መንገድ እዘጋ ነበር፡፡ ከዚያ ትቦዬን ይዘጉትና መንገዱን ይከፍቱታል፡፡

ስሙኝማ! በቀደም ዋናው የትራንስፖርቱ ሰውዬ በሚዲያ ላይ ቀርበው፣ በነዳጅ የሚሠራ መኪና እዚህ አገር ድርሽ እንደማይል ከተናገሩ በኋላ የሚከተለውን አስከተሉ፣

‹‹የሞተር አልባ የትራንስፖርት አማራጮች ላይ እንሠራለን፣ አንደኛው ሞተር አልባ ዜጎች በእግር እንዲሄዱ (እንፈልጋለን) አንደኛ ለጤናቸው ጥሩ ነው፣ ሁለተኛ ተሽከርካሪ መጠቀምን ይቀነሳል፣ አካባቢ ላይ ብክለት ይቀንሳል፣ ሌላው ሳይክል ነው፣ እሱን መጠቀም ነው፣ በእንስሳ የሚሠራ ጋሪ ማበረታት ነው ያለብን፡፡ ማዘመን እንችላለን፡፡ የአህያና የፈረስ ጋሪ እሱን እያዘመንን እንደ ትራንስፖርት አማራጭ ሥራ ላይ እንዲውሉ እያደረግን ነው፣ በዚህም ጥሩ ውጤት ተገኝተዋል፤››

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በእውነት ልማትን መንቆር ሱስ ካልሆነብን በቀር አሁን ይሄ ሐሳብ ምን ይወጣለታል? በበኩሌ ሐሳቡን ግጥም አድርጌ ደግፌ ጥቂት ማስተካከያ ብቻ አበረክታለሁ፡፡

ዜጎች በእግር እንዲሄዱ ማበረታታቱ ጥሩ ነው፡፡ ግን ከኮተቤ ወይራ ሠፈር እየተመላለሰ የሚሠራውን ሰውዬ በእግርህ ሂድ ማለቱ ትንሽ ሊከብድ ይችላል፡፡ ስለዚህ መሥሪያ ቤቱን ወደ ቤቱ ገፋ አድርጎ ማቅረብ ቢቻል? ወይም ዜጎች በእግራቸው እየሄዱ የሚሠሩትን ሥራ መፍጠር ቢቻል ሸጋ ነው! አለበለዚያ ብዙ ዜጎች ጤናቸውን ለመጠበቅ ሲሞክሩ ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡

በነዳጅ የሚሠሩ መኪኖች አካባቢ መበከላቸው ሀቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ዜጋ ከፒያሳ ቦሌ አራብሳ ድረስ በእግሩ ከሄደ የካልሲው ሽታ እንኳን አካባቢ ጋላክሲውን ሊበክል ይችላል፡፡ ይሄ እንግዲህ ከሚሊዮን ጭቁን ብብቶች የሚመነጨውን የላብ ጠረን ሳናነሳ ነው፡፡ ስለዚህ የትራንስፖርት ሚኒስተር በእግር ለሚሄዱ ዜጎች ተለዋጭ ካልሲና ዶዶራንት ቢያሰናዳ አሪፍ ይሆናል! በተጨማሪም በየሁለት ኪሎ ሜትሩም የሕዝብ ገላ መታጠቢያዎች ቢሰናዱ አይከፋም፡፡

ጋሪዎችን ማዘመን በሚለው ሐሳብም ሙልጭ አድርጌ እስማማለሁ፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን በፈረስ የሚጎተት ጋሪ አይነፋም፡፡ ስለዚህ የማይጎተት ‹‹wireless›› ጋሪ መሥራት ቢቻል ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ፡፡

በእንስሳ የሚሠሩ ጋሪዎች መኖር አለባቸው ከተባለም አይደብረኝም፡፡ ይሁን እንጂ የአህያና የፈረስ ፋንድያና ሽንት የሚፈጥረው አኅጉራዊ ብክለት ግን ይታሰብበት! ለዚህም የሚከተለውን መፍትሔ በነፃ አበረክታለሁ፡፡ የፈረሶች መቀመጫ ላይ (ለካ አይቀመጡም) በፈረሶች ጭስ ማስወጫ ዙርያ ሸብ የሚደረግ ምንጣፍ የሚያክል ዳይፐር ይዘጋጅ!

ፈረሶች ሲወጥራቸው ወደ ሕዝብ መፀዳጃ ጎራ ብለው ፋንድያቸውን እንዲጥሉ ማሠልጠን ሌላው መፍትሔ ነው፡፡

በቂ በጀት ካለ ተጨማሪ ሐሳቦች ይኖሩኛል

 – በዕውቀቱ ሥዩም በማኅበራዊ ገጹ እንደጻፈው

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...