Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትድንገት ያረፈው የዋሊያዎቹና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች አለልኝ አዘነ

ድንገት ያረፈው የዋሊያዎቹና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች አለልኝ አዘነ

ቀን:

‹‹እኔ ኮሜንታተር እያለሁ ያገባቸውን ሦስት ጎሎች አልረሳም። ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ አክርሮ የመታቸው ተመሳሳይነት ያላቸው ጎሎች ነበሩ። በጣም የሚገርም ተሰጥዖ የነበረው፣ አውሮፓ ሁሉ ሄዶ መጫወት የሚያስችል አቋምና ቁመና የነበረው ተጫዋች ነው። በጣም ደንግጫለሁ፡፡››

ድንገት ያረፈው የዋሊያዎቹና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች አለልኝ አዘነ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ነፍስ ኄር አለልኝ አዘነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) እና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት ዜና ዕረፍቱ መሰማቱን ተከትሎ ነው፡፡ ይህን ከላይ የተጠቀሰውን አስተያየት ለቢቢሲ የሰነዘረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮሜንታተር በመሆን ያገለገለው ጊልበርት ሴሌብዋል ነው፡፡

ፕሮፌሽናል ተጫዋች በመሆን ከፍ ያለ ደረጃ ይደርሳል ተብሎ በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው አለልኝ፣ በድንገት በትውልድ ከተማው በአርባ ምንጭ የሞተው መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ባህር ዳር ከተማ ተለይቶ ለዕረፍት ወደ አርባ ምንጭ ባቀናበት አጋጣሚ ማረፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹አለልኝ አዘነ በተደጋጋሚ ለብሔራዊ ቡድናችን ተመርጦ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝና በአሁኑ ወቅት በእግር ኳሳችን ላይ ምርጥ አቋማቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ ተጫዋች ነበር፤›› ብሎለታል፡፡

በቅርቡ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጎጆ የወጣው አለልኝ በተከላካይ አማካይ ቦታ ይጫወት እንደነበረ ከባህር ዳር ክለብ በፊት ለሐዋሳና ለመቀለ 70 እንደርታ መጫወቱ በገጸ ታሪኩ ተመልክቷል፡፡

የባህር ዳርና የአርባ ምንጭ ክለቦች የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሐዘናቸውን ከገለጹት መካከል ይገኙበታል።

የነፍስ ኄር አለልኝ አዘነ ሥርዓተ ቀብር ረቡዕ መጋቢት 18 ቀን በአርባ ምንጭ ከተማ ተፈጽሟል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...