Wednesday, April 17, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተሉ አንዳንዴም በመገረም እየሳቁ አገኟቸው]

 • አንዴ? ምን አገኘሽ?
 • ምን አገኘሽ ማለት?
 • ለብቻሽ የሚያስቅሽ ማለቴ ነው?
 • እ… ምን ላድርግ ብለህ ነው? ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው።
 • እንዴት? ምንድነው ነገሩ?
 • በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን እያዳመጥኩ ነዋ?
 • አለቃ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር የሚያደርገው ውይይት አይደለም አንዴ? 
 • ነው። 
 • ታዲያ ይህ ውይይት ምን የሚያስቅ ነገር አለው? 
 • ወይይቱ አይደለም። 
 • እ…?
 • ውይይቱ ላይ የሰማሁት ነገር አስገርሞኝ ነው። 
 • ምንድነው የሰማሽው? 
 • ከሰሜን የመጡት የሕዝብ ተወካዮች ያለአግባብ የታሰሩብን ሰዎች አሉ። ለምን አይፈቱም ብለው ይጠይቃሉ።
 • እሺ?
 • አወያዩ ደግሞ ሲመልሱ …
 • እ… ምን አሉ?
 • ስብሃትን እኔ አይደለሁም ወይ የፈታሁት ብለው እርፍ።
 • ታዲያ እንደዚያ ማለታቸው ያስቃል እንዴ? 
 • ማሳቅ ብቻ ሳይሆን…
 • እ…?
 • አስገርሞኛል።
 • ለምን?
 • ያኔ የተናገሩት ትዝ ብሎኝ ነዋ።
 • ያኔ ማለት መቼ ነው?
 • ሰውዬው የተፈቱ ጊዜ ነዋ።
 • ስለሰውዬው መፈታት ተናግረው ነበር እንዴ? ትዝ አላለኝም።
 • ሰውዬው የተፈቱ ጊዜ ተቃውሞ እንደነበር አታስታውስም?
 • አዎ። ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበር አስታውሳለሁ።
 • ታዲያ ያን ጊዜ ነዋ የተናገሩት።
 • ስለምንድነው የተናገሩት?
 • ስለሰውዬው መፈታት ነዋ።
 • ለምንድነው የፈታሁት አሉ?
 • መቼ እኔ ፈታሁት አሉ?
 • ታዲያ ምንድን ነበር ያሉት?
 • እኛም ስንሰማ ደንግጠናል! 
 • እየቀለድሽ ነው?
 • ኧረ በፍጹም… ይኸው እንደውም ቪዲዮውን ፈልጌ አግቼዋለሁ ተመልከት።
 • ወይ ጉድ!
 • ምነው?
 • አንቺም አታልፊንም …ዛሬ ደግሞ ጮማ ሳቅ ነው ያገኘሽው።
 • አዬ… እኔ መች መሳቅ ፈልጌ ሆነና ብለህ ነው? 
 • እና…?
 • በቴሌቭዥን የሚታየው ነገር ሁሉ ድራማ አይደል እንዴ የሚመስለው?
 • እንዴት? 
 • በሕዝብ ላይ ሰብዓዊ በደል አድርሰዋል ያላችኋቸውን ባለሥልጣናትን ስታስሩ ነበር።
 • አዎ።
 • የአገርና የሕዝብ ሀብት ዘርፈዋል ብላችሁም ስታስሩ ነበር። 
 • አዎ፡፡
 • ዛሬ ደግሞ ሌላ ነገር ብላችሁ ወሰናችሁ።
 • ምን ብለን ወሰንን?
 • ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ክሳቸው ተቋርጧል።
 • ታዲያ ምን ችግር አለው?
 • እንዴት?
 • ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የተደረገ ነዋ?
 • እንዲያው ነገሩ ሁሉ እንትን ሆነብኝ…
 • ምን?
 • መግባትና መውጣት።
 • እንዴት?
 • ሰሞኑን ያለመከሰስ መብት ስታስነሱ አልነበር።
 • አዎ።
 • ስለዚህ ተረኛው ደግሞ ይገባል ማለት ነው።
 • ካላጠፋ ለምን ተብሎ ይገባል?
 • ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...