Thursday, April 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየቅብብሎሽ ዜማ ያወጡት ዓይነ ሥውራን ድምፃውያን ስንቱና ባልክ

የቅብብሎሽ ዜማ ያወጡት ዓይነ ሥውራን ድምፃውያን ስንቱና ባልክ

ቀን:

በቀደመው ጊዜ ድምፃውያን በጋራ ዘፈኖቻቸውን ለአድማጮቻቸውም ሆነ ለተመልካቾቻቸው ሲያቀርቡ የብዙዎችን አድናቆትንም ያተርፉ ነበር፡፡ ለምሳሌም ዓይነ ሥውሩ ተሾመ አሰግድና ራሔል ዮሐንስ፣ ጥላሁን ገሠሠና ብዙነሽ በቀለ፣ ዓለማየሁ እሸቴና ሒሩት በቀለ፣ ዳምጠው አየለና ኩኩ ሰብስቤ፣ ሐመልማል አባተና ነዋይ ደበበ ቴዎድሮስ ታደሰና አሰፉ ደባልቄ ከብዙዎቹ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በቅብብሎሽ መዝፈኑ እንደቀደመው ጊዜ የጎላ ባይሆንም አልፎ አልፎ የሚታዩ ድምፃውያን ግን መታየታቸው አልቀረም፡፡

ሙዚቃዊ የተሰኘው የሙዚቃ ተቋም ለሪፖርተር በላከው መግለጫው፣ የዓይነ ሥውራኑን ድምፃውያን ስንታየሁ በላይና ባልከው ዓለሙ ‹‹ከሃሳቤ›› የተሰኘ የቅብብሎሽ ነጠላ ዜማን ሰሞኑን በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናልና በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች መልቀቁን ገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ቀደም ሲል ባወጡት ገሚስ አልበማቸው ተወዳጅነትን ማትረፋቸውን፣ በባላገሩ አይዶልና በፋና ላምሮት ውድድሮች በአብዛኞቹ ተከታታዮች የሚታወቁ መሆናቸውን ያስታወሰው ተቋሙ፣ አዲሱ ሥራቸው ‹‹ከሐሳቤ›› በዕውቁ ሙዚቀኛ ግሩም መዝሙር ፕሮዲውስ መደረጉን ጠቁሟል፡፡

ናፍቆትና ፍቅር ላይ የሚያጠነጥነው ይህ የሙዚቃ ሥራ ዓለማየሁ ደመቀ በግጥምና ዜማ፣ አበጋዙ ሺኦታ በሚክሲንግ፣ ግሩም መዝሙር በቅንብር እንዲሁም ሌሎች ስመጥር ሙዚቀኞች ተሳትፈውበታል፡፡ ባለሙያዎች ሥራው ለአድማጮች ልብ የቀረበ እንደሚሆን መመስከራቸውም ተነግሯል፡፡

በሙዚቃዊው ተቋም የፕሬስ መግለጫ አገላለጽ፣ በቅርቡ ‹‹የኔ ዓለም›› በተሰኘው ገሚስ አልበሙ የብዙዎችን ቀልብ የገዛው ባልከው በምትሀታዊ ድምፁ ከኢትዮጵያን አይዶል አሁን እስካለበት የመዝለቁ ምስጢር የዓመታት ልምድ መሰነቁ ነው። ከሙዚቃ ክህሎቱ ባሻገርም በተማሪዎቹ ተወዳጅ የእንግሊዝኛ መምህርም ነው። በተመሳሳይ ሁኔታም ‹‹ፀደይ›› በተሰኘው ገሚስ አልበሟ በጥሩ ብቃቷ አድናቆትን ያገኘችው ስንታየሁ በላይ በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ውስጥ ስሟን እየገነባች የምትገኝ ድምፃዊት ናት።

ስንታየሁ፣ እንደ አስቴር አወቀና ሐመልማል አባተ ዓይነት ዘመናዊ የአዘፋፈን ሥልት ያላት ድምፃዊት መሆኗ የሚወሳላት ስትሆን፣ የባህላዊ አዘማመር ሥልቶች መጠቀሟ ድምፅዋን የተለየ ውበት እንዲላበስ አድርጎታል ሲሉ ባለሙያዎች መስክረውላታል፡፡

ከሃሳቤ ለሙዚቃ ኢንዱስትሪው ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ለሚገኙት ስንቱና ባልክ የሁለተኛ ምዕራፍ ሥራቸው ሲሆን፣ ለአይነ ሥውራን እንዲሁም ለሌሎች አካል ጉዳተኞች ህልማቸውን በማሳካት ተምሳሌት የሚሆኑ አርቲስቶች መሆናቸውም እምነቱን አንፀባርቋል።

ስንታየሁና ባልከው ዓይነ ሥውራን የሆኑትንና ዝነኞቹን የማሊ ጥንድ ሙዚቀኞች አማዱና ማሪያምን እንደ አርዓያ በመውሰድ የሁሉንም አድማጮች ልብ የሚማርክ አጨዋወት በማቅረብ ለስማቸው የሚመጥን ሥራ መሥራታቸውም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...