Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበሞስኮ የሙዚቃ ኮንሰርት የሽብር ጥቃትና የፑቲን ምላሽ

በሞስኮ የሙዚቃ ኮንሰርት የሽብር ጥቃትና የፑቲን ምላሽ

ቀን:

በሞስኮ ክሮከስ አዳራሽ የሮክ የሙዚቃ ድግስ ለመታደም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታድመው ነበር፡፡ ሆኖም የሙዚቃ ድግሱን ወደ ሞትና ጉዳት የሚቀይር የሽብር ጥቃት ተፈጸመ፡፡

የሞስኮው ክሮከስ አዳራሽ በእሳት ጋየ፣ ታጣቂዎች በአዳራሹ በከፈቱት የተኩስ እሩምታና በወረወሩት ቦምብ ከ137 ሰዎች አለቁ፡፡ ከ100 በላይ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡

የወታደር ዩኒፎርም የለበሱ ታጣቂዎች ፈጽመውታል የተባለውን ጥቃት ተከትሎ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬንን ሲኮንኑ፣ ምዕራባውያንና ራሷ ዩክሬን፣ ዩክሬን ከደሙ ንፁህ ናት ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከሽብር ጥቃቱ ጋር በተያያዘ አራት በጥቃቱ ቀጥታ ተሳትፈዋል የተባሉ ግለሰቦችን ጨምሮ 11 መያዛቸውን የሩሲያው ኢንተርፋክስ ዜና ወኪል ጥቃቱ በተፈጸመ ማግስት አስታውቋል፡፡

የአፍጋኒስታን ክንፍ የሆነው አይኤስአይኤል በሞስኮ የሙዚቃ ኮንሰርት ታዳሚዎች ላይ ለተፈጸመው የሽብር ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን፣ አሜሪካ በበኩሏ ሽብር ጥቃቱን የፈጸመው አይኤስአይኤስ ስለመሆኑ አረጋግጫለሁ ብላለች፡፡

አይኤስአይኤል ለምን በሩሲያ ውስጥ ጥቃት ፈጸመ?

አይኤስአይኤል በሞስኮ ለተፈጸመው የሽብር ጥቃት ኃላፊነት ቢወስድም፣ ከሩሲያ ወገን የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ ሆኖም የመከላከያና የደኅንነት ትንተናዎችን ጠቅሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፣ ቡድኑ በሩሲያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ያነሳሳው ሩሲያ በሙስሊሞች ላይ ጫና ታሳድራለች በሚል ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የሩሲያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲም አንዱ እንደሆነ መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው የሳውዝ ኤዥያ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ማይክል ኩግልማን ይገልጻሉ፡፡

እንደ እሳቸው፣ ሶቭየት ኅብረት በሚባልበት ዘመን የሶቭየት አፍጋኒስታንን መውረር፣ ሩሲያ በቺቺኒያ ላይ ያላት አቋም፣ ሞስኮ ከሶሪያና ኢራን መንግሥታት ጋር ያላት የጠበቃ ግንኙነት፣ በተለይ ሩሲያ በሶሪያ በአይኤስአይኤስ ተዋጊዎች ላይ የምታደርገው ዘመቻና በአፍሪካ በአንዳንድ አገሮች በዋግነር ቡድን አማካይነት የምትፈጽመው ዕርምጃ ዓርብ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ለደረሰባት ጥቃት ምክንያቶች ናቸው፡፡ ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አይኤስአይኤስን ለማጥፋት የሚደረገው ዘመቻ አካል መሆኗም ከምክንያቶቹ ይጠቀሳል፡፡

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለጥቃቱ ምን አሉ?

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከሽብር ጥቃቱ ጋር ዩክሬን የተወሰነ ግንኙነት እንዳላት አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ሊወሰዱ ስለሚገቡ ዕርምጃዎች አስመልክተው ከደኅንነት አካላት ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ከጥቃቱ ጀርባ ‹‹የሙስሊም አክራሪዎች›› አሉበት ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የእስልምና እምነት ተከታይ አገሮች ጭምር በሚቃወሟቸው አክራሪዎች ተፈጽሟል፣ የሽብር ጥቃቱም እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከገባችው ዩክሬን ጋር ግንኙነት አለው ብለዋል፡፡

ሽብር ፈጽመዋል ተብለው የተያዙት ሰዎች ወደ ዩክሬን ሊሸሹ ሲሉ እንደነበርም ጠቅሰዋል፡፡ አይኤስአይኤል ጥቃቱን ፈጽሜያለሁ ብሎ ኃላፊነት ቢወስድም፣ ፑቲን በንግግራቸው የአይኤአይኤልን ስም አላነሱም፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት ግን ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ገልጸዋል፡፡

ለደረሰው የሽብር ጥቃት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ አራት ግለሰቦች እሑድ መጋቢት 15 ቀን ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ድብደባ የተፈጸመባቸው ፍርደኞችም በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ታይተዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከ19 እስከ 32 የሆኑት ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ሰኞ መጋቢት 16 ተጨማሪ ሦስት ወንዶች ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ በቀጣይ ሌሎች ጥቃቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ በሚል በአሥር የንግድ ማዕከላትም የደኅንነት ማንቂያ መልዕክት መተላለፉ ተገልጿል፡፡

በሩሲያና ዩክሬን መካከል ያለውን ግጭት ያባባሰው የሞስኮ የሽብር ጥቃት

እስካሁን ባለው መረጃ ስለሽብር ጥቃቱ ፈጻሚዎች ጥርት ያለ ማስረጃ አልተገኘም፡፡ ሆኖም የሽብር ጥቃቱን ተከትሎ በተለይ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ጦርነት ሊያባብሰው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ጠቁመዋል፡፡

በሩሲያ የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ከሁለት ሳምንታት በፊት አሜሪካ አሳውቄያለሁ ማለቷን የሩሲያ ባለሥልጣናት ያስተባበሉትም፣ ጥቃቱን ከዩክሬን ጋር ለማያያዝና ከፍተኛ ጥቃት ለመፈጸም ታስቦ ነው የሚል አስተያየት ተሰንዝሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...