Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበፆታ እኩልነትና አካታችነት ላይ የሚያተኩረው የቀይ መስቀል ፕሮጀክት

በፆታ እኩልነትና አካታችነት ላይ የሚያተኩረው የቀይ መስቀል ፕሮጀክት

ቀን:

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚተገበርና በፆታ እኩልነትና አካታችነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ስካይ በርድ 2ኛ ምዕራፍ የተሰኘ ፕሮጀክቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ማኅበሩ ፕሮጀክቱን የሚያከናውነው ከኦስትሪያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ነው፡፡

የፕሮጀክቱን በይፋ መጀመር አስመልክቶ መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ እንደተናገሩት፣ ስካይ ቦርድ በውኃ፣ በጤናና በሴቶች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ፕሮጀክት ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በኦስትሪያ ቀይ መስቀልና በኦስትሪያ ኤምባሲ የአራት ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ፣ በዑጋንዳና በሩዋንዳ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን ነውም ብለዋል፡፡

የስካይ በርድ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በተከናወነባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የኦሮሚያ፣ የአማራና የደቡብ ክልሎች መልካም አፈጻጸም የታየባቸው በመሆኑና ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ መሆን በመቻሉ ሁለተኛው ፕሮግራም እንዲጀምር ሆኗል፡፡

እንደ ፕሬዚዳንቱ፣ የስካይ በርድ ምዕራፍ ሁለት የትግበራ ሁለት ፕሮግራም በአሊአባቡር፣ በአርሲና በሲዳማ አካባቢዎች ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ በተለይም ደግሞ የሴቶችን የውኃና የንፅህና ችግር ለመቅረፍ የታቀደ ነው፡፡    

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ጠሃ እንደገለጹት፣ የስካይ በርድ ፕሮጀክት በጤና፣ በውኃና በተለይም በሴቶች ሥነ ፆታ ንፅህና ላይ አተኩሮ ይሠራል፡፡

ፕሮግራሙ ከምሥራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን፣ ሩዋንዳንና ዑጋንዳን የሚያጠቃልል ሲሆን የሴቶችን የፆታ ብቃት፣ ሴቶች በሴትነታቸው ማግኘት የሚገባቸውን መሠረታዊ የንፅህናና ሳኒቴሼን አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡

አቶ ጌታቸው እንደሚሉት፣ አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ሴቶች ውኃ የሚቀዱት ከወንዝ ነው፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዓላማ ሴቶች በግቢያቸው ወይም በአቅራቢያቸው የውኃ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማስቻል በተጨማሪ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ የሚያመቻቸው ነው፡፡

‹‹ሴቶች በተለያዩ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ተሳትፎ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የጎላ ድርሻ ሊኖራቸው ይገባል፤›› የሚሉት አቶ ጌታቸው፣ ስካይ በርድ ፕሮጀክትም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ይሠራል ብለዋል፡፡

የኦስትሪያ ቀይ መስቀል ተወካይ የሆኑት አቶ ተመስገን አበበ እንደተናገሩት፣ ስካይ በርድ ፕሮጀክት በውኃ፣ በንፅህናና ድንገተኛ የሕክምና አገልግሎት (ኢመርጀንሲ ሜዲካል ሰርቪስ) ላይ ትኩረት አድርጎ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን ፕሮግራም ነው፡፡

በስካይ በርድ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ትግበራ ምዕራፍ ወደ 210 ሺሕ የሚጠጉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በ32 ትንንሽ ፕሮግራሞች ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ በመሆኑም እነዚህ የኅብረተሰቡን ችግር የቀረፉና ውጤት የተመዘገበባቸው ፕሮግራሞች መቀጠልና መስፋት ይገባቸዋል በሚል ታምኖበት ሁለተኛው የትግበራ ምዕራፍ እንዲተገበር ሆኗል፡፡

እንደ አቶ ተመስገን ገለጻ፣ በስካይ በርድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ትግበራ ፕሮጀክት በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአማራና በደቡብ ክልሎች በውኃ ተቋማት ግንባታ፣ በተፈጥሮ ሀብት ሥራዎች፣ በሥነ ንፅህናና በሌሎች ዘርፎች ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...