Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊወላጆቻቸውን ላጡና ጎዳና ለወጡ ሕፃናት የሚገነባው የእንክብካቤ ማዕከል

ወላጆቻቸውን ላጡና ጎዳና ለወጡ ሕፃናት የሚገነባው የእንክብካቤ ማዕከል

ቀን:

በኢትዮጵያ ወላጆቻቸውን ያጡና ጎዳና የወጡ ሕፃናት የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም መሰረታዊ እንክብካቤ የሚያገኙበት ማዕከል በአንድ ቢሊዮን ብር ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን፣ ‹‹መቅደስ የልጆች አድማስ›› የበጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ማዕከሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ፣ ለተጠቃሚዎች የትምህርት፣ የጤና፣ የአካል ብቃት ማጎልመሻ፣ የማኅበራዊ ሕይወት፣ የአዕምሮ ማበልፀጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሙሉ ጤንነታቸው የተረጋገጠ እንዲሁም በአካላዊ ዕድገታቸው የበቁ እንዲሆኑ እንደሚያግዝም አስታውቋል፡፡

የመቅደስ የልጆች አድማስ ድርጅት መሥራች አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ እንደገለጹት፣ ማዕከሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ፣ በመጀመሪያ ዙር 200 ሕፃናትን፣ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም 1,000 ሕፃናትን የሚቀበል ይሆናል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለማዕከሉ ግንባታ 21 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ ለመቀበል ሒደት ላይ መሆናቸውን የተናገሩት መሥራቿ፣ ለግንባታ ለሚሆነው ገንዘብ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የሚካሄድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ድርጅቱ የመጀመሪያ ሥራውን ተግባራዊ የሚያደርገው በአዲስ አበባ ቢሆንም፣ ቀስ በቀስ ወደ ክልሎች ቅርንጫፎቹን በማስፋት በርካታ ሕፃናትን ለመደገፍ የሚንቀሳቀስ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመቅደስ የልጆች አድማስ የሚያድጉ ልጆች በሁሉም ረገድ ኢትዮጵያዊ እሴቶችን የተላበሱና አዎንታዊ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ማድረግም የስራው ዋና ትኩረት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በቅርብ ጊዜ የሚጀመር መሆኑን ገልጸው፣ ድርጅቱም በዋናነት ልዩ ትኩረትና ጥበቃ ለሚያስፈልጋቸው ወላጅ ላጡ ሕፃናት አስፈላጊውንና ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ በመስጠት፣ በቀጣይ የሕይወት ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል፡፡

በማዕከሉ አገልግሎት የሚያገኙ ሕፃናት እስከ መጨረሻ ድረስ ትምህርታቸውን ተምረው ራሳቸውን እንዲያገኙና ለቁም ነገር እንዲበቁ የሚደረግ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ማዕከሉ የሚገነባበትን ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ ከተቀበሉ ወዲያውኑ ጊዜያዊ ቤት በመሥራት ሕፃናት ልጆችን የሚቀበሉ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ማዕከሉ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ዳራውን እንዲጠብቅና የታለመለትን ግብ እንዲመታ በብቁ የሰው ኃይል፣ በቁሳቁስና በቴክኖሎጂ ለማደራጀት ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግ የድርጅቱ አባል ጸሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ ተናግረዋል፡፡

የቅርብ ጊዜ ጥናቶችን ዋቢ አድርገው፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ወላጆቻቸውን ማጣታቸውን የተናገሩት ጸሐፊ ተውኔት ውድነህ፣ 600 ሺሕ የሚሆኑት በጎዳና ላይ እንደሚኖሩ አክለዋል፡፡

በስካይ ላይት ሆቴል የሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የኤምባሲ ተወካዮች፣ ሐሳቡን የሚደግፉ ግለሰቦች የሚታደሙበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ድርጅቱን ሙሉ ለሙሉ በመገንባትና በሙሉ አቅሙ ሥራውን እንዲጀምር ለማድረግ እስከ አንድ ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን፣ የዲዛይን ሥራው ያለቀለት ማዕከልም በ21 ሺሕ ካሬ ሜትር ስፍራ የሚያርፍ ይሆናል፡፡

‹‹መቅደስ የልጆች አድማስ›› ሕፃናትን ተንከባክቦ ከማሳደግ ባሻገር ኅብረተሰቡ ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት ያለው አመለካከት እንዲቀየር የሚሠራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...