Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየጋዜጠኞችና የደራስያን ሽልማት

የጋዜጠኞችና የደራስያን ሽልማት

ቀን:

በማኅበረሰብ ድምፅና በዳኞች ውሳኔ ጋዜጠኞችና ደራስያን ተሸላሚ የሚሆኑበት ‹‹ክብር›› የተሰኘ ሽልማት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን፣ የቃል መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቃልኪዳን ኃይሉ አስታወቁ፡፡

ለጋዜጠኞችና ደራስያን የሚበረከተውን ‹‹ክብር›› ሽልማት አስመልክቶ መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ፣ም. በተዘጋጀ መድረክ እንደተገለጸውም፣ ሽልማቱ በኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍና ጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በሥራዎቻቸው አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለሙያዎችን ከፍ ማድረግን ያለመ ነው፡፡

በግንቦት 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሥነ ሥርዓት ይከናወናል ተብሎ በሚጠበቀው ዓመታዊ የሽልማት ፕሮግራም፣ እጩዎች በ15 ዘርፎች የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በደራስያን ዘርፍ በልብ ወለድ የአጫጭር፣ የወግ፣ የግጥም መድብል፣ በፊልም ጽሑፎች፣ የቴአትር ጽሑፎች፣ የዘፈን ግጥሞች የሠሩ የሚሸለሙበት ሲሆን፣ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢዎችና የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅቶች ለውድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

በሬዲዮ ዘርፍ፣ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅትና አቅራቢ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ደግሞ ለዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሽልማት ይደረጋል፡፡

በሥነ ጽሑፍና በጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ አሻራ ያሳረፉም የሕይወት ዘመን ተሸላሚ እንደሚሆኑ አቶ ቃልኪዳን ተናግረዋል፡፡

በ11 የቦርድ አባላት ታግዞ ከዓመት በፊት በተጀመረው የሽልማት ዝግጅት፣ ውድድሩ የሚከናውነው በድረ ገጽ ሲሆን፣ የተወዳዳሪ ሥራዎችም ከመስከረም 1 እስከ ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ የወጡና ትርጉም ያልሆኑ እንደሚሆኑ አክለዋል፡፡

40 በመቶ ከማህበረሰብ በድረ ገጽ ከሚሰበሰብ ድምጽና 60 በመቶ በዳኞች ውሳኔ ለሚያሸንፉ ባለሙያዎች፣ የዋንጫና የክብር ዲፕሎማ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ዋንጫውም በሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ አዳነ ድልነሳው የተሠራ መሆኑን ተገልጿል፡፡

የሽልማት ዝግጅቱን አስመልክቶ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በሽልማቱ ለምን የኅትመት ጋዜጠኞች አልተካተቱም? ሽልማቱ ትኩረት ያደረገው መዝናኛው ላይ ነው የጋዜጠኝነት ሚና የሚገለጽበትን ዓምድ አልተዋችሁም ወይ? የዳኞች ብቃት፣ ጋዜጠኝነት በርካታ ሥራዎች ስላሉት በየዘርፉ ቢደረግ፣ ዘርፎቹ አልታጨቁም ወይ? የሚሉና ሌሎችም ተነስተዋል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የሽልማቱ አዘጋጆችና የቦርድ አባላትም፣ ይህ የመጀመሪያ እንደመሆኑ ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የኅትመት ሚዲያው በቀጣይ እንደሚካተት፣ ብቁና ልምድ ያላቸው ዳኞች በውሳኔው ላይ እንደሚሳተፉ፣ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናወን ከመሆኑ አንፃር፣ ከባለሙያዎች የሚገኙ ግብረ መልሶችና ሐሳቦችን በመወሰድ በቀጣይ እየዳበረ እንደሚሄድ ሰምተናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...