Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየስፖርት አወራራጆች ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ ይሰጥበታል ተባለ

የስፖርት አወራራጆች ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ ይሰጥበታል ተባለ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ የስፖርት አወራራጆች መደብሮች (ቤቲንግ) እንደገና እንደማይከፈቱና በአገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙትን ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ውሳኔ እንደሚሰጥበት፣ የከተማው የሰላምና የፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከዚህ በፊት የስፖርት አወራራጆችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፣ በ3,241 የማወራረጃ ቤቶች ላይ የማሸግ ዕርምጃ መውሰዱ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በከተማዋ የስፖርት ውርርድ የሚያጫውቱ እንደገና ሥራቸውን መቀጠል እንደማይችሉ ቢሮው ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሰላምና የፀጥታ ቢሮ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፣ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርና ከቤቲንግ አጫዋቾች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት በማድረግ መሆኑን ገልጸው፣ ውሳኔው የተላለፈውን ጥናት መሠረት በማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የስፖርት ውርርድ ማጫወቻ ቦታዎች እንዲዘጉ ለፓርላማ መቅረቡን ያስታወሱት ኃላፊዋ፣ በወቅቱም ጉዳዩ ፓርላማ ሲቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች መኖራቸውን እንኳን እንደማያውቁ ተናግረው ነበር ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡

ማኅበረሰቡ የስፖርት ውርርድ ቤቶች እንደገና እንዳይከፈቱ ሐሳብ ማቅረባቸውን፣ ከተከፈቱም ትልቅ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያስከትላል ማለታቸውን አብራርተዋል፡፡

በተለይ ሕፃናት ልጆች ትምህርታቸውን ትተው ውሏቸው ቤቲንግ ቤት እንደነበር፣ በርካታ ሰዎች 24 ሰዓት ቁማር በመጫወት ጊዜያቸውን እንደሚያሳልፉ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩም በአገር ደረጃ ትልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ በመታየቱ፣ የማወራረጃ ቤቶቹ መዘጋታቸውን ጠቅሰው፣ የስፖርት ውርርድ ከሚያጫውቱ ግለሰቦች ጋርም ቢሮው ውይይት ባደረገበት ወቅት ‹‹ቨርቹዋል›› ወይም ‹‹ኬኖ›› የተባለ ውርርድ የሚያጫውቱ እንዲዘጉ፣ ቤቲንግ ቤቶች ግን ይከፈቱ የሚል አስተያየት መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

በወቅቱ በከተማው ውስጥ የቤቲንግ ቤቶች ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ቢሮው ለሁለት ወራት ጥናት ማድረጉንና በጥናቱም መሠረት መጠጥ፣ ጫት፣ ሺሻና ሌሎች ነገሮች ሲወሰድባቸው መታየቱን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊዋ፣ በአንዳንድ ቤቲንግ ቤቶች የሰው ሕይወት ማለፉን አስረድተዋል፡፡

በተለይ የከተማዋ ነዋሪዎች ሥራ ፈጣሪ ከመሆን ይልቅ ቁማር ቤት መዋልን አማራጭ ማድረጋቸውን ገልጸው፣ ብሔራዊ ሎተሪ ፈቃድ ከመስጠት ውጪ ምንም ዓይነት ቁጥጥር እንደማያደርግ አስታውሰዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ሙሉ በሙሉ ቤቲንግ ቤቶች መዘጋታቸውን፣ ነገር ግን የክልሎችን በተመለከተ ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ እንደሚሰጥበት ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በኋላ የስፖርት ውርርድ አጫዋቾች በሌላ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ቢሮው በግልጽ ማስቀመጡን አስታውቀው፣ የትኛውም በቤቲንግ ዘርፍ የተሰማራ አካል ዕቃውን አውጥቶ በሌላ ንግድ ዘርፍ መሰማራት ይችላል ብለዋል፡፡

በዚህ መሠረት ተግባራዊ አደርጋለሁ የሚል የስፖርት ውርርድ አጫዋቾች ዕቃውን ማውጣት እንደሚችል፣ ለዚህም ተግባራዊነት እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የስፖርት ውርርድ ጨዋታ ሲስተሙ የተዘረጋው ውጭ አገር በመሆኑ በኦንላይን የሚያጫውቱ ቤቲንግ ቤቶችን መቆጣጠር እንደማይቻል፣ ነገር ግን በአገር ደረጃ ውሳኔ ሲሰጥ ችግሩ ይፈታል ብለዋል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ከሕጋዊ 120 ቤቲንግ ቤቶች የተወሰኑት ብቻ ተዘግተዋል ብለዋል፡፡

የስፖርት ውርርድ ቤቶችን በተመለከተ ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ ሕጋዊ ፈቃድ የተሰጣቸው ቤቲንግ ቤቶች እንዲከፈቱ እየተጠበቀ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡ ይህም ከቢሮ ኃላፊዋ ንግግር ጋር የሚጋጭ ሐሳብ ስለመሆኑ የተጠየቁት ዳይሬክተሩ ምላሽ መስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፈቃድ ሳይወስዱ ኬኖ የሚያጫውቱ ግለሰቦች እንዳሉ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ እነዚህን ግለሰቦች ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር ውይይት በተደረገበት ወቅት ድርጊቱን ማመናቸውን አስረድተዋል፡፡   

ሕጋዊ ሆነው የተዘጉ ቤቲንግ ቤቶች እንዲከፈቱ በደብዳቤም ሆነ በአካል ከሰላምና ከፀጥታ ቢሮ ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን፣ አንዳንድ ቤቲንግ ቤቶች ቅርንጫፎቻቸው ብቻ እንደተዘጉ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...