Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የደረሰው ጥቃት ከውስጥ አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑኑ ከሲስተም ጋር በተያያዘ የገጠመው ችግር፣ በባንኩ የውስጥ አሠራር የዩዘር አካውንት ወይም ሎጊን በመጠቀም የደረሰ ጥቃት ለመሆኑ መገመት እንደሚቻል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ ከትናንት በስቲያ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. እንዳስታወቀው መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባንኪ ላይ የደረሰው የሲስተም ችግር ከሳይበር ጥቃት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውና ከውጭ ወደ ባንኩ የተደረገ ጥቃት ያለመሆኑንም ባደረገው ምርመራ ማረጋገጥ መቻሉንም አስታውቋ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግሥት ሃሚድ እንዳስታወቁት፣ ችግሩ ከውስጥ አሠራር ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህንንም ሲያብራሩ፣ የዩዘር አካውንት ወይም ሎጊን በመጠቀም የደረሰ ጥቃት ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት እንደሚቻል ያካሄዱት ምርመራ እንዳረጋገጠላቸው አመልክተዋል፡፡

በውስጥ ያለውን አሠራርና ተያያዥ ጉዳዮች አሁንም ከባንኩ ጋር በመሆን እየመሩ ሲሆን፣ ውጤቱም ይፋ እንደሚደረግ የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ የሞባይል ስሪት ማሻሻያው ሥርዓቱን ሳይጠብቅ ምናልባትም የፕሮግራሚንግ ቅደም ተከተሉን ሳይጠብቅ የተከናወነ በመሆኑ የተፈጠረ ችግር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች