Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአገሪቱ ባሉ ግጭቶች ሠራተኞቹ እየተገደሉበት መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአገሪቱ ባሉ ግጭቶች ሠራተኞቹ እየተገደሉበት መሆኑን አስታወቀ

ቀን:

  • ወጣቶችን በሰብዓዊነት ተግባር አሠልጥኖ የሚያስመርቅ ተቋም ለመክፈት ዝግጀት ማጠናቀቁም ተገልጿል

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ በተፈጠሩ ግጭቶች ሕይወት አድን ሥራዎችን ለመሥራ የተሰማሩ በአማራ፣ በትግራይና በኦሮሚያ ክልሎች ከ12 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች እንደተገደሉበት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል ሾፌሮች፣ የማኅበሩ ሠራተኞች በጎ ፈቃደኞችና አባላት ይገኙበታል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች በርካታ የማኅበሩ አምቡላንሶች በታጣቂዎች መወሰዳቸውን፣ በጥይት መመታታቸውንና መቃጠላቸውንም አክለው ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አቶ አበራ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ችግሮች ባሉበት አካባቢ ሕይወት አድን ሥራዎችን ለመሥራት በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሌላ ሕይወት እንዳያልፍ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡ የሠራተኞቹን ደኅንነት ባስጠበቀ መልኩ የሰብዓዊነት ሰውን የመርዳት ተልዕኮውን ለመወጣት ዘወትር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

‹‹ግጭቶች ባሉበት አካባቢ እንደልብ ተንቀሳቅሶ የሰብዓዊነት ተግባር ማከናወን መስዋዕትነትን ይጠይቃል›› ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹ብዙውን ጊዜ ባንዲራችንንና ምልክታችንን አይተው የሚያሳልፉን እንዳሉ ሁሉ የማይረዱን ደግሞ ጥቃት እያደረሱብን ይገኛሉ›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ስኩል ኦፍ ሁማኒቲ (School of Humanity) በሚል  ወጣቶችን በሰብዓዊነት፣ በአብሮነትና በመቻቻል እሴት አሠልጥኖ የሚያስመርቅ የትምህርት ተቋም ለመክፈት ዝግጅት ያጠናቀቀ መሆኑንም አቶ አበራ ተናግረዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሥርዓተ ትምህርቱ መዘጋጀቱንና በሥርዓተ ትምህርት ቀረፃው ከ12 በላይ በፕሮፌሰርነት ማዕረግ በዩኒቨርሲቲው የሚያገለግሉ ምሁራን መሳተፋቸውንም ተናግረዋል፡፡  

ከ2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎችን በዲፕሎማ መርሐ ግብር ተቀብሎ በራሱ ተቋም ማሠልጠን እንደሚጀምርና በቀጣይም ትምህርቱን ወደ ዲግሪ ደረጃ የማሳደግ ዕቅድ መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ላለፉት 89 ዓመታት በመላ አገሪቱ የሰብዓዊነት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱንና በአሁኑ ወቅትም ከ390 በላይ በሚሆኑ አምቡላንሶቹ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አቶ አበራ አክለው ገልጸዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...