Saturday, April 20, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አጀንዳ አድርጎ የያዘው ወቅታዊ የፀጥታና የደኅንነት ጉዳዮች ውይይት ከመጀመሩ በፊት ተጨማሪ አጀንዳ ማስያዝ የምትፈልጉ ሲባል በሙስና የሚጠረጠሩት ኃላፊ እጃቸውን አወጡ]

 • በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር …
 • እሺ …ቀጥል
 • አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ ሆኖ በልዩ ሁኔታ ልንወያይባቸው የሚገቡ ተያያዥ ጉዳዮች እንዲካተቱ ቢደረግ ለማለት ነው።
 • በልዩ ሁኔታ የሚነሳ ምን አጀንዳ አለ?
 • አለ ክቡር ሚኒስትር!
 • በልዩ ሁኔታ መታየት አለበት የምትለው ካለ መቀጠል ትችላለህ።
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ሠግቻለሁ!
 • ሠግቻለሁ?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር …እኔ ፍርኃት አለኝ።
 • ፍርኃቱን ተወውና አጀንዳህን ለምን አታስይዝም?
 • አጀንዳዬን ከነ ስሜቱ ለማስያዝ ፈልጌ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ለምን ወደ አጀንዳህ አትገባም?
 • ወደዚያ እየመጣሁ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • በል ቀጥል። ሌላ አጀንዳ ያልከው ምንድነው?
 • ትልቁ የአገሪቱ ባንክ ሰሞኑን ያጋጠመው ነገር ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ባንኩ ያጋጠመው ችግር ላይ ምን?
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ አስግቶኛል።
 • ችግሩ እንደተፈታ ተገልጾ የለ እንዴ?
 • ቢሆንም ክቡር ሚኒስትር ችግሩ ዳግም እንደማይከሰት ምን ማረጋገጫ አለን?
 • እህ… ዳግም እንዳይከሰት ነው ሥጋትህ?
 • አዎ፣ ክቡር ሚኒስትር።
 • ቆይ ምን ያህል ገንዘብ ብታስቀምጥ ነው ይህን ያህል የሠጋኸው?
 • ለእኔ አይደለም የሠጋሁት ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ ለማን ነው የሠጋኸው?
 • ለሕዝቡ ነው!

[በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ] 

 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ሠላም ሠላም… ተቀመጥ፡፡
 • አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር፣ ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት።
 • እንዴ አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም እንዴ?
 • ነኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ታዲያ በየትኛው ተቋም ሠራተኛ ነው የተወከልከው?
 • በዚሁ በእኛው ተቋም ሠራተኛ ነው የተወከልኩት ክቡር ሚኒስትር።
 • እንዴት? በቀጥታ ከሠራተኛው ጋር የምገናኝበት መድረክ እያለ አንተን መወከል ለምን አስፈለገ?
 • የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ የሚመለከት ስለሆነ በዕድሜም በልምድም አንተ ብታነጋግራቸው ይሻላል ብለው ስለወከሉኝ ነው።
 • ምንድነው ጉዳዩ?
 • ክቡር ሚኒስትር ሠራተኛው በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ነው።
 • እሱን የሁላችንም ችግር ነው… በአገር ጭምር የመጣ ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር የመንግሥት ሠራተኛው ግን የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው። በተለይ ተበቋማችን…
 • ለተቋማችን ተለይቶ የመጣ ችግር ነው እንዴ?
 • አይለደም። ግን የችግሩን ጥልቀት የሚረዳልን አጥተናል።
 • ምን ማለትህ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እኛ ተቋም ውስጥ ያለው ሁኔታ ቢያዩ የችግሩን ጥልቀት ይረዱታል። በቀን አንዴ ብቻ የሚመገቡ ባልደረቦቻችን እየተበራከቱ ነው።
 • እና ምን ይደረግ ነው የምትለው? ለዚህ ተቋም ብቻ የሚወሰን ነገር እንደማይኖር አታውቅም?
 • እሱን እገነዘባለሁ። በሠራተኛው የተወከልኩትም እርሱ መፍትሔ እንዲሰጡን አይደለም።
 • እና ለምንድነው?
 • ከፍተኛ የመንግሥት አመራር እንደ መሆንዎ መጠን የሚመሩት ተቋም ሠራተኞችን ችግር ለካቢኔ እንዲያቀርቡልን ወይም ጉዳዩ ሲነሳ እንዲያስረዱልን ነው።
 • ጉዳዩ እንዴት ይነሳል? ማን ያነሳዋል?
 • በሁሉም የመንግሥት ተቋማት ያሉ ሠራተኞች ተመሳሳይ ጥያቄ ይኖራቸዋል ወይም የዚህ ተቋም ሠራተኞች እኔን እንደወከሉት ሌሎቹም እንደዚያ ሊያደርጉ ይችላሉ ብዬ ነው።
 • እሺ ተነሳ እንበል…
 • ከተነሳማ በዚህ ተቋም ያሉ ሠራተኞች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ እንዲያስረዱልንና መፍትሔ እንዲጠይቁልን ነው፡፡
 • ምን ብዬ ነው መፍትሔ የምጠይቀው?
 • ሠራተኛው በሚያገኘው ደመወዝ የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም አልቻለም ይበሉልን።
 • እሺ… ከዚያስ?
 • ከዚያማ ሠራተኛው የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ እያቀረበ ነው ሊጨመርለት ይገባል ይበሉልን!
 • እሺ እንደዚያ አልኩ እንበል። ለደመወዝ ጭማሪ የሚሆነው በጀት ከየት እንደሚመጣ አመላክት ብባልስ?
 • እሱን በጋራ የምትመልሱት እንጂ ለእርስዎ ብቻ የሚተው አይመስለኝም።
 • በጋራ መፍትሔ ለመስጠትም እኮ ሐሳብ ማቅረብ ይጠይቃል።
 • ክቡር ሚኒስትር መንግሥት የሠራተኛውን ችግር በቅንነት ከተመለከተውና ካሰበበት መፍትሔ ይኖራል።
 • አይ አንተ …እስኪ መፍትሔ ጠቁም ብትባል አንድ መፍትሔ የለህም ለማማረር ግን…
 • ክቡር ሚኒስትር በእርስዎ ያምራል ብዬ እንጂ ጠቁም ካሉኝማ እጠቁማለሁ፡፡
 • እስኪ ጠቁም…?
 • መቼም የጫካ ቤተ መንግሥት ፕሮጀክት ይታጠፍ አልልም።
 • ብትልስ?
 • እኔም አልልም ግን…
 • እሺ ሌላ ምን ልትል ነው?
 • የኮሪደር ልማቱም እንዲቋረጥ አልጠይቅም።
 • ብትጠይቅስ ማን ይሰማሃል?
 • እኔም አልጠይቅም።
 • ታዲያ ለምን እነዚህን ፕሮጀክቶች ማንሳት አስፈለገህ?
 • መፍትሔ ያልኩትን ለማቅረብ ነው።
 • ምንድነው መፍትሔው?
 • እነዚህ ፕሮጀክቶች አዘግይቶ ሰው መታደግ ነው መፍትሔው!
 • ይኸው …ይህንኑ እንደምትል ገብቶኛል።
 • ክቡር ሚኒስትር በቀን አንዴ ብቻ ተመግበው የሚውሉ ባልደረቦቻችን ቁጥር እየጨመረ ነው። ጥያቄያችን ከፖለቲካ ንፁህ መሆኑንም እንዲረዱኝ እፈልጋለሁ።
 • እንዴት ነው ከፖለቲካ ንፁህ የሚሆነው?
 • እውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር!
 • እውነቱ ምንድነው?
 • የኑሮ እንጂ የፖለቲካ ጥያቄ የለንም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የቤተ መንግሥት ግንባታ ይቁም እያልክ?
 • መፍትሔ ጠቁም ስላሉኝ ነዋ!
 • ብልህስ? የቤተ መንግሥት ግንባታ ይቁም ትላለህ?
 • ተከራከር ካሉኝም ሠራተኛው እየተራበ ቤተ መንግሥት መገንባት ቅደም ተከተሉን የጠበቀ መሰሎ አይታየኝም።
 • ይኸው… ዋናው ጉዳይህ ቤተ መንግሥቱ ነው።
 • አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እየሰማሁህ?
 • ክቡር ሚኒስትር ጉዳዬ መንግሥት ችግሩን ተረድቶ ደመወዝ እንዲጨምር መጠየቃችንን እንዲያስረዱልን ነው። ካልሆነ ደግሞ…
 • ካልሆነ ምን?
 • መንግሥት ደመወዝ መጨመር ካልቻለ ደግሞ አንድ ነገር ያድርግልን?
 • ምን?
 • ለምንግሥት ሠራተኛውም ያጋራ
 • ምን?
 • ማዕድ!
 • ምን አልክ?
 • እውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። ለመንግሥት ሠራተኛውም ሊቋቋምለት ይገባል።
 • ምን?
 • የምገባ ማዕከል!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...